18
May
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በ50 ሚልየን ዶላር ያስገነባውን አዲስ የአገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል ዛሬ አስመረቀ። በአየር መንገዱ ከአዲስ አበባ ወደ ሁሉም የአገር ውስጥ መዳረሻዎች እንዲሁም ከአገር ውስጥ ወደ አዲስ አበባ ለሚደረጉ በረራዎች በዚህ ተርሚናል አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው አዲሱ የአገር ውስጥ ተርሚናል አየር መንገዱ የሚሰጠውን የአገር ውስጥ በረራ አቅም በዕጥፍ እንደሚያሳድገው አስታውቀዋል። አየር መንገዱ 22 የአገር ውስጥ መዳረሻዎች አሉት። የቱሪዝም ሚኒስትሯ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ አዲስ የተገነባው የአገር ውስጥ ተርሚናል የቱሪዝም ዘርፍ በማሳደግ በኩል ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ገልጸዋል። አየር መንገዱ ከሁለት ወራት በፊት በ55 ሚሊዮን ዶላር ያስገነባውን የድጅታል ግብይት…