DigitalEthiopia

በኢትዮጵያ ዓመታዊ የድጅታል ገንዘብ ልውውጥ ከ18 ትሪሊዮን ብር በላይ ደረሰ

በኢትዮጵያ ዓመታዊ የድጅታል ገንዘብ ልውውጥ ከ18 ትሪሊዮን ብር በላይ ደረሰ

ብሔራዊ ባንክ እንዳስታወቀው በአንድ አመት ውስጥ በጂታል ክፍያ ስርአት 18 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር ዝውውር ተፈጽሟል። በኢትዮጵያ ዲጂታል ክፍያ ኮንፈረንስ 2.0. ላይ ለአምስት አመት የሚቆይ (2026-30) የብሔራዊ የዲጂታል ክፍያ ስትራቴጂ በብሔራዊ ባንክ ይፋ ሆኗል። የመጀመሪያው የ2021-24 ብሄራዊ የዲጂታል ክፍያ ስትራቴጂ ላይ ህግ ማውጣት፣ተቋማት አገልግሎቱን እንዲሰጡ ማስቻልና ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ እንዲሁም መሠረተ ልማት ዝርጋታ መከናወናቸው ተጠቁሟል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የክፍያ ስርአት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ዳምጠው ለቅዳሜ ገበያ እንደገለጹት በኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ ትልቁ ሚና የገንዘብ ዝውውር ፈጣን ቀልጣፋ ወጪ ቆጣቢ መሆን አለበት። ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የዲጂታል የክፍያ ስርአትን ማዘመን እና ለዚያ የሚያበቃ የድጅታል መሰረተ ልማት ግንባታ ጉልህ ሚና ይጫወታል። ባለፈው አንድ አመት…
Read More
ብሔራዊ ባንክ የባንክ አካውንት ከብሔራዊ መታወቂያ ጋር እንዲያስተሳስሩ አሳሰበ

ብሔራዊ ባንክ የባንክ አካውንት ከብሔራዊ መታወቂያ ጋር እንዲያስተሳስሩ አሳሰበ

ባንኮች የከፈቷቸውን አካውንቶች በሁለት ሳምንት ውስጥ ከብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ጋር የማስተሳሰር ሥራ እንዲያጠናቅቁ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል። ብሔራዊ ባንክ እና የብሔራዊ መታወቂያ በጋራ ባወጡት አዲስ የአተገባበር ሥርዓት መሰረት የፋይናንስ ተቋማት ብሄራዊ ኦፕሬተር በሆነው ኢት-ስዊች በኩል ከብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ጋር የማስተሳሰር ሥራ መስራት መጀመራቸው ተገልጿል። እስካሁን 10 የሚሆኑ የፋይናንስ ተቋማት ከብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ጋር የማስተሳሰሩን ሥራ ጨርሰዋል ሲባል ሌሎች ባንኮች በሙከራ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ይለበስ አዲስ ለኢትዮ ነጋሪ እንደገለጹት ይህ አሰራር ባንኮች አገልግሎታቸው ቀልጣፋ እንዲሆንና ማዕከላዊ የመረጃ አያያዝ እንዲኖር ያስችላል ሲሉ ገልጸዋል። አክለውም ትስስሩ ባንኮች ከደንበኞቻቸው ጋር ያላቸውን አገልግሎት ያሳልጥላቸዋል፤ ወጪንም ይቆጥብላቸዋል ብለዋል፡፡ የኢት-ስዊች ቺፍ ፖርት ፎልዮ ኦፊሰር…
Read More
ብሔራዊ መታወቂያ ተመዝጋቢዎችን ወደ 63 ሚሊዮን ለማድረስ መታቀዱ ተገለጸ

ብሔራዊ መታወቂያ ተመዝጋቢዎችን ወደ 63 ሚሊዮን ለማድረስ መታቀዱ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ሚያዝያ 2015 ላይ ነበር ብሔራዊ መታወቂያ በሙከራ ደረጃ መመዝገብ የጀመረችው፡፡ በ29 ከተሞች የተጀመረው ይህ ፕሮግራም ከታህሳስ 2014 ጀምሮ ከ70 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን በብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባ ለማካሄድ በይፋ ተጀምሯል፡፡ ኢትዮ ነጋሪ ይህ የብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባ ምን እንደሚመስል በሀገሪቱ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ነዋሪዎችን እና ጉዳዩ የሚመለከታቸውን አካላትን አነጋግሯል፡፡ አቶ አማረ አሰፋ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማ ነዋሪ ናቸው፡፡ አጣዬ ከተማ ከሀገሪቱ ዋና ከተማ አዲስ አበባ በ300 ኪሎ ሜትር በሰሜን ኢትዮጵያ በኩል የምትገኝ ከተማ ናት፡፡ የድጅታል መታወቂያ ካሳለፈነው ሚያዝያ ወር ጀምሮ መሰጠት መጀመሩን ገልጸው ከሁለት ወር በፊት የድጅታል አይዲው ታትሞ እጃቸው እንደገባ ነግረውናል፡፡ አሁን ላይ በአጣዬ ከተማ ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች…
Read More
አሸዋ ቴክኖሎጂ  ተጨማሪ የአክስዮን ሽያጭ ጀመረ

አሸዋ ቴክኖሎጂ ተጨማሪ የአክስዮን ሽያጭ ጀመረ

አክስዮን ገዢዎች  በ500 ሺ ብር  አክስዮን በስድስት አመት ውስጥ ከስድስት ሚልየን ብር በላይ እንደሚያገኙ ተገልጿል። አሸዋ ቴክኖሎጂ በሰው ሃብት አስተዳደር ፣ በሂሳብ መዝገብ አያያዝ  እና የቢዝነስ  ክንውኖችን ማቀላጠፊያ ሶፍትዌሮችን በማበልጸግ ወደ ስራ የገባ አገር በቀል ድርጅት ነው። የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዳንኤል በቀለ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ግለሰቦች እና ድርጅቶች አክስዮን  ገዝተው ትርፍ የሚጋሩበትን ለሶስት ወራት የሚቆይ የአክስዮን ሽያጭ መጀመሩን ተናግረዋል። የአንድ አክስዮን ዋጋ 2 ሺህ 500 ብር እየሸጠ ያለው አሸዋ ቴክኖሎጂ  ትንሹ አክስዮን 500 ሺህ ብር ሲሆን  ትልቁ አክስዮን ደግሞ 100 ሚልየን ብር እንደሆነ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተጠቅሷል። የአክስዮን ገዢዎች የገዙትን አክስዮን መጠን 50 በመቶውን ቅድሚያ መክፈል ይጠበቅባቸዋል የተባለ ሲሆን ቀሪ የአክስዮን ድርሻዎችን ደግሞ…
Read More
ኢትዮጵያ ከሞባይል ክፍያ ሥርዓት ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ የማግኘት አቅም እንዳላት ተገለጸ

ኢትዮጵያ ከሞባይል ክፍያ ሥርዓት ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ የማግኘት አቅም እንዳላት ተገለጸ

በኢትዮጵያ የሞባይል ክፍያ ሥርዓት በስፋት ጥቅም ላይ ከዋለ የአገር ዉስጥ እድገት 5 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር እንደሚጨምር ዓለም አቀፍ የሞባይል ግንኙነት ስርዓት ማኅበር አስታውቋል። ይህም የሚሆነው በፈረንጆች 2030 ከአጠቃላይ የአገሪቱ ሕዝብ 60 በመቶ ያህሉ የሞባይል ክፍያ ሥርዓት ተጠቃሚ ከሆኑ ነው ያለው ማኅበሩ፤ በተጨማሪም 700 ሺሕ ሰዎችን ከአስከፊ ድህነት እንደሚያወጣና የታክስ ገቢን በ300 ሚሊዮን ዶላር እንደሚጨምር አመላክቷል፡፡ ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ በአንፃራዊነት 99 በመቶ የኔትወርክ ሽፋን ተደራሽነት ቢኖርም፤ የኔትዎርክ ጥራት አስተማማኝ አለመሆን፣ የዲጂታል ስርዓቱ ግንዛቤ ጉድለት፣ የዕምነትና የመረጃ ግላዊነትና ደህንነት ጥያቄ እንዲሁም የግብይቶች በተደጋጋሚ መስተጓጎል የሞባይል ገንዘብ ክፍያን እና አጠቃቀም ላይ እንቅፋት እየሆነ እንደሚገኝ ተጠቅሷል። በተጨማሪም በ2021 የኤሌክትሪክ ኃይል ያላቸው ኢትዮጵያውያን 51…
Read More
ብሔራዊ ባንክ ለኤምፔሳ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት ፈቀድ ሰጠ

ብሔራዊ ባንክ ለኤምፔሳ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት ፈቀድ ሰጠ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ፈቃድ ከብሔራዊ ባንክ አግኝቷል። ከሁለት ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ የገባው ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ የቴሌኮም ኩባንያ አሁን ደግሞ ተጨማሪ ፈቃድ ማግኘቱን አስታውቋል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በኤምፔሳ አማካኝነት የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ፈቃድ ከብሔራዊ ባንክ አግኝቷል። የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ባንኩ የዲጅታል ፋይናንስ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለው የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት ፈቃድን ለሳፋሪ ኮም መስጠቱን አስታውቀዋል፡፡ ይህም ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት ፈቃድ ያገኘ የመጀመሪያው የውጭ አገር ኩባንያ እንደሚያደርገው የብሔራዊ ባንክ መረጃ ያመለክታል፡፡ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከሰሞኑ በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አምባሳደር ሔኖክ ተፈራን አዲስ ሀላፊነት መስጠቱ ይታወሳል። አምባሳደር ሔኖክ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳዮች…
Read More