Amhara

በአማራ ክልል የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለአራት ወራት ተራዘመ

በአማራ ክልል የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለአራት ወራት ተራዘመ

በአማራ ክልል የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለአራት ወራት ተራዘመ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአማራ ክልል ባሳለፍነው ነሀሴ ለስድስት ወራት የታወጀው አስቸኳይ አዋጅ ለተጨማሪ አራት ወራት ተራዝሟል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ልዩ ስብሰባ በአማራ ክልል የታወጀውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ አራት ወራት  አራዝሟል። የምክር ቤቱ አባላት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዙሪያ አደረጉት በተባለው ውይይት ከዋጁ በሁለት ተቃውሞ በሶሰት ድምፅ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ለአራት ወራት እንዲራዘም መወሰኑ ተገልጿል፡፡ ባሳለፍነው ዓመት ሚያዚያ ወር የፌደራል መንግስት የክልል ልዩ ሀይሎችን መልሼ ለማደራጀት ወስኛለሁ ማለቱን ተከትሎ ነበር በአማራ ክልል ግጭት የተከሰተው፡፡ ይህ ግጭት ቀስ በቀስ እያደገ መጥቶ ወደ ጦርነት የተቀየረ ሲሆን የቀድሞው የክልሉ መንግስት በመደበኛ…
Read More
ላለፉት ሶስት ዓመት የትጥቅ ትግል ሲያካሂድ የነበረው የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የሰላም ስምምነት ፈረመ

ላለፉት ሶስት ዓመት የትጥቅ ትግል ሲያካሂድ የነበረው የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የሰላም ስምምነት ፈረመ

ላለፉት ሶስት ዓመት የትጥቅ ትግል ሲያካሂድ የነበረው የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ከአማራ ክልል አስተዳድር ጋር የሰላም ስምምነት ተፈራረመ የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ የንቅናቄው አመራሮች በተለያዩ የአመራር ቦታዎች ላይ ሹመት እንደሚሰጣቸው ተገልጿል፡፡ የአገው ዴሞክራሲ ንቅናቄ (አዴን) የጥቅምት 2013ቱን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ተከትሎ በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በተለይም በአበርገሌና ፃግብጂ ወረዳዎች ትጥቅ ትግል ሲያካሄድ ቆይቷል፡፡ ታጣቂ ኃይሉ በሁለቱ ወረዳዎች ቆላማ አካባቢዎች እስከ 19 የሚሆኑ ቀበሌዎችን ሲቆጣጠር እንደነበረም ንቅናቄውና የመንግስት አካላት አመልክተዋል፡፡ የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የመንግሰትን የሰላም ጥሪ ተቀብሎ ታህሳስ 13 ቀን 2016 ዓ ም በአዲስ አበባ ከተማ ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጋር የሰላም ስምምነት ማድረጉንና ትናንት ደግሞ በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ማዕከል ሰቆጣ ከተማ…
Read More
በአማራ ክልል የሚገኙ ዩንቨርሲቲዎች ከጥር አንድ ጀምሮ ተማሪዎቻቸውን ሊጠሩ ነው

በአማራ ክልል የሚገኙ ዩንቨርሲቲዎች ከጥር አንድ ጀምሮ ተማሪዎቻቸውን ሊጠሩ ነው

ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ትምህርት ይጀምራሉ ብሏል፡፡ ሚኒስቴሩ አክሎም በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል በተፈጠረው ወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች በ2016 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያዉ ወሰነ-ትምህርት ተማሪዎቻቸውን ለመጥራትና መደበኛ የመማር ማስተማር ስራቸዉን ሙሉ ለሙሉ ለመጀመር አልቻሉም ነበር። በመሆኑም የትምህርት ሚኒስቴር ከክልሉ ኮማንድፖስት፣ የጸጥታ አደረጃጀቶችና የሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ተከታታይ ውይይቶችን ሲያካሂድ መቆየቱን ገልጿል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ፣ የአስሩ ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዝዳንቶችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የክልሉ ጸጥታ አካላት ታህሳስ 18 ቀን 2016 ዓ.ም  በጉዳዩ ዙሪያ መክረዋልም ተብሏል፡፡ ሚኒስቴሩ በመግለጫው…
Read More
በአማራ ክልል ከሁለት ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸው ተገለጸ

በአማራ ክልል ከሁለት ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸው ተገለጸ

በአማራ ክልል ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ከሁለት ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለጸ። የቢሮው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን በክልሉ ያለው የጸጥታ ችግር በተማሪዎች ምዝገባ ሥራ ላይ ከፍተኛ ጫና አሳድሯል ብለዋል። ክልሉ 6.2 ሚሊዮን ተማሪዎችን መዝግቦ ማስተማር ሲገባው ያን ማድረግ አለመቻሉን ኃላፊው ተናግረዋል። ከሁለት ሚሊዮን በላይ ያልተመዘገቡ ተማሪዎች መኖራቸውን የገለፁት ኃላፊው ፤ መማር የሚገባቸው ተማሪዎች የትምህርት ዕድል እንዳያገኙ መደረጉን አመልክተዋል። በጸጥታው ችግር ምክንያት ሁለት ሺህ በሚጠጉ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራን ከመማር ማስተማር ሥራ ውጪ መሆናቸውን ገልፀዋል። ይሁን እንጂ መምህራኑ ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ የማድረግ ሥራ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል። በክልሉ ባለው ግጭት "ወደ 42 ትምህርት ቤቶች…
Read More
የኢትዮጵያ እና አረብ ኢምሬት የጦር ጄቶች የጋራ አየር ትርኢት አካሄዱ

የኢትዮጵያ እና አረብ ኢምሬት የጦር ጄቶች የጋራ አየር ትርኢት አካሄዱ

የኢትዮጵያ አየር ሀይል የተመሰረተበትን 88ኛ ዓመት በማክበር ላይ ስትሆን በዛሬው ዕለት ከተባበሩት አረብ ኢምሬት የጦር ጄቶች ጋር በመሆን የአየር ላይ ትርዒት አድርገዋል፡፡ በአዲስ አበባ በተካሄደው በዚህ የጦር አውሮፕላኖች ትርዒት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ጨምሮ በርካታ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ የሁለቱ ሀገራት የጦር አውሮፕላኖች ያካሄዱት የአየር ላይ ትርዒት “የጥቁር አንበሳ የአየር ትርዒት” የሚል ስያሜ እንደተሰጠው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አስታውቋል፡፡ ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ ወታደራዊ አታሼዎች ባሳለፍነው ሳምንት ቢሾፍቱ የሚገኘውን የኢትዮጵያን አየር ሀይል ዋና ማዘዣን የጎበኙ ሲሆን በዛሬው በዓል ላይም ተገኝተዋል፡፡ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በ1928 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን በአፍሪካ ካሉ አየር ሀይሎች በእድሜ ትልቁ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ ወታደራዊ ትርዒቶችን በአደባባይ ላይ ማክበር እየጨመረ የመጣ…
Read More
በኦሮሚያ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ 11 ሰዎች ተገደሉ

በኦሮሚያ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ 11 ሰዎች ተገደሉ

በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መቀጠላቸውን ኢሰመኮ ገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ፣ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል፡፡ እንደ ኢሰመኮ ሪፖርት ከሆነ በአማራ ክልል በአዊ ብሔረሰብ ዞን፣ በአየሁ ጓጉሳ ወረዳ እና በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ቡሬ ዙሪያ ወረዳ፤ እንዲሁም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ አሶሳ ዞን፣ ኦዳ ብልድግሉ ወረዳ፤ በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል፣ በአርሲ ዞን፣ ሸርካ ወረዳ እና በቄለም ወለጋ ዞን፣ ጊዳሚ ወረዳ በሲቪል ሰዎች ላይ ጥቃቶች መፈጸማቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡ በአማራ ክልል፣ በአዊ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር፣ በአየሁ ጓጉሳ ወረዳ፣ አምበላ ቀበሌ እና በዚገም ወረዳ ሶሪት ቀበሌ ከጥቅምት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ…
Read More
አሜሪካ በኢትዮጵያ ያቋረጠችውን እርዳታ ልትጀምር መሆኗን ገለጸች

አሜሪካ በኢትዮጵያ ያቋረጠችውን እርዳታ ልትጀምር መሆኗን ገለጸች

የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ከመጪው ወር ጀምሮ በመላው ኢትዮጵያ የምግብ እርዳታ አጀምራለሁ ብሏል፡፡ የአሜሪካ  መንግስት የዓለም አቀፍ ልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) ካሳለፍነው ሰኔ ወር ጀምሮ በምግብ እርዳታ ስርቆት ምክንያት እርዳታ መስጠቱን ማቆሙ ይታወሳል፡፡ በለጋሾች የተገዛ የምግብ እርዳታ ለገበያ መቅረቡና ወደ ውጪ አገራት ጭምር መላኩን የጠቀሰው የተራድኦ ድርጅቱ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የእርዳታ ስርጭቱን በተመለከተ ተከታታይ ውይይት ማድረጉን ገልጿል። በዚህም ባለፈው ወር በሀገሪቱ ለሚገኙ ስደተኞች የምግብ እርዳታ ማቅረብ የጀመረ ሲሆን ከመጪው ወር ጀምሮ ደግሞ በመላው ኢትዮጵያ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች እርዳታ ማቅረብ እንደሚጀምር ገልጿል። ኢትዮጵያ የምግብ ድጋፍ ስርጭት ስርአቷን በመሰረታዊነት የሚያስተካክል ስራ መከወኗንና ለጋሽ ድርጅቶች እርዳታው ለተገቢው አካል መድረሱን እንዲከታተሉ መስማማቷን ድርጅቱ አስታውቋል። ለጋሽ…
Read More
የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ከተፈረመ አንድ ዓመት ሞላው

የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ከተፈረመ አንድ ዓመት ሞላው

ህወሀት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝን ማጥቃቱን ተከትሎ ነበር በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የተቀሰቀሰው። ለሁለት ዓመት የዘለቀው ይህ ጦርነት 800 ሺህ ገደማ ኢትዮጵያዊያን ህይወታቸውን እንዲያጡ ሲያደርግ 26 ቢሊዮን ዶላር የኢኮኖሚ ኪሳራም አድርሷል። ለዚህ ጦርነት መቆም ምክንያት የሆነው የሰላም ስምምነት ከአንድ ዓመት በፊት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተፈርሟል። የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ስለ ስምምነቱ እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በፌደራል መንግሥት እና ትግራይ ሀይሎች መካከል የተካሄደው የሰላም ስምምነት ለኢትዮጵያ ምን ጥቅም አስገኘ? በሚል ከጋዜጠኞች ጥያቄ ለቃል አቀባዩ ተነስቶላቸዋል። አምባሳደር መለስ በምላሻቸውም " ስምምነቱ በሁለቱ ወገኖች መካከል ጦርነት እንዲቆም ከማድረግ በተጨማሪ ኢትዮጵያ ላይ…
Read More
በአማራ ክልል በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች የሚፈጸሙ ግድያዎች መቀጠላቸውን ኢሰመኮ ገለጸ

በአማራ ክልል በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች የሚፈጸሙ ግድያዎች መቀጠላቸውን ኢሰመኮ ገለጸ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል በቀጠለው ጦርነት ዙሪያ ያደረገውን የምርመራ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡ ኮሚሽኑ እንዳለው በአማራ ክልል ባለው ጦርነት የደረሱ ጉዳቶችን ለመመርመር መንግሥታዊ ኃላፊዎችን፣ በግጭቱ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎችን፣ የዐይን ምስክሮችን፣ ተጎጂዎችንና የተጎጂዎች ቤተሰቦችን በማነጋገር መረጃዎችንና ማስረጃዎችን ማሰባባቡን ገልጿል፡፡ ከሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ባለው ጊዜ ውስጥ በአማራ ክልል ሁሉም ዞኖች በመንግስት የጸጽታ ሀይሎች እና በተለምዶ ፋኖ በመባል ከሚታወቀው አካል ጋር ጦርነት እየተካሄደ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡ ይህ ጦርነት በአንዳንድ አካባቢዎች በከባድ መሣሪያ እና አልፎ አልፎ በአየር/ድሮን ድብደባ ጭምር የታገዘ ነው ያለ ሲሆን በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት እና የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡ በሰሜን ሸዋ ዞን፣ በረኸት ወረዳ፣ መጥተህ ብላ ከተማ፣…
Read More
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ቻይና አመሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ቻይና አመሩ

የቻይና ቤልት ኤንድ ሮድ ዓመታዊ ጉባኤ ከሁለት ቀናት በኋላ በቤጂንግ ይካሄዳል፡፡ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ጨምሮ በርካታ የዓለማችን መሪዎች በዚህ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ቤጂንግ በማምራት ላይ ናቸው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በዚሁ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ቻይና ማምራታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ ቻይና ለኢትዮጵያ ብድር ከሚሰጡ ሀገራት መካከል ዋነኛዋ ስትሆን በተለይም ለኤርፖርት ማስፋፊያ፣ ለመንገድ እና ለደረቅ ወደብ ልማት ግንባታዎች በቻይና ብድር ተገንብተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በጦርነት እና በኮሮና ቫይረስ መጎዳቱን ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስት የብድር ጫና ውስጥ በመግባቱ የብድር መክፈያ ጊዜ እንዲራዘምለት በመጠየቅ ላይ ነው፡፡ ቻይና የኢትዮጵያን የብድር መክፈያ ጊዜ በአንድ ዓመት ማራዘሟ የተገለጸ ሲሆን ከዓለም ባንክ…
Read More