ስፖርት

ሻሸመኔ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ወደ ፕሪሜር ሊግ አደገ

ሻሸመኔ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ወደ ፕሪሜር ሊግ አደገ

በሳሙኤል አባተ በምድብ ለ ሀዋሳ ላይ እየተከናወነ በሚገኜው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ሻሸመኔ ከነማ ቀሪ 4 ጨዋታ እያለው ወደ ቤቲኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል ። በዕለተ ማክሰኞ ሚያዚያ 24 አዲስ አበባ ከነማ በቦዲቲ ከነማ 2ለ1 መሸነፉን ተከትሎ ሻሸመኔ ቀሪ 4 ጨዋታዎች እያሉት በ 47 ነጥብ ፕሪሜር ሊጉን ተቀላቅሏል ። አዲስ አበባ ከነማ በ35 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በቀጣይ ቀሪ 2 ክለቦች ሊጉን ይቀላቀላሉ ። በምድብ ሐ  ሀምበርቾ ዱራሜ በ 42 ነጥብ ገላን ከተማ በ 40 ነጥብ የምድቡ አንደኛ ሁኖ ለማለፍ የሚያደርጉት ፉክክር ይጠበቃል ። በተመሳሳይ በምድብ ሀ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ 50 ነጥብ ምድቡን ሲመራ ቤንቺ ማጅ በ…
Read More
አትሌት ደራርቱ ቱሉ የአፍሪካ አትሌቲክስ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆና ተመረጠች

አትሌት ደራርቱ ቱሉ የአፍሪካ አትሌቲክስ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆና ተመረጠች

አትሌት ደራርቱ ቱሉ የአፍሪካ አትሌቲክስ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆና ተመረጠች የኮንፌዴሬሽን ኦፍ አፍሪካ አትሌቲክስ ኮንግረስ በዛምቢያ መዲና ሉሳካ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የሆነችው አትሌት ደራርቱ ቱሉ የአፍሪካ አትሌቲክስን በምክትል ፕሬዚዳንትነት እንድትመራ ተመርጣለች፡፡ በዚህም ካውንስሉ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን የአፍሪካ አትሌቲክስን በምክትል ፕሬዝዳንትነት እንድትመራ በሙሉ ድምጽ መመረጧን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡ የ51 ዓመቷ አትሌት ደራርቱ ሀገሯን እና ራሷን ያስጠራችባቸው በርካታ ሜዳሊያዎችን ያሸነፈች ሲሆን በኦሎምፒክ የ10 ሺህ ሜትር ርቀት ውድድር ታሪክ የወርቅ ሜዳሊያ ያመጣች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊ ተብላለች፡፡ አትሌት ደራርቱ ከ2018 ጀምሮ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን ከቀድሞው ፕሬዝዳንት አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ተረክባ በመምራት ላይ ትገኛለች፡፡ አትሌቷ ባሳካቻቸው በርካታ ውድድሮች ለሌሎች ታዳጊ አትሌቶች…
Read More
ሲፋን ሀሰን የለንደን ሜራቶንን አሸነፈች

ሲፋን ሀሰን የለንደን ሜራቶንን አሸነፈች

የለንደን ማራቶች ከደቂቃዎች በፊት የሁለቱም ጾታ ተዉዳዳሪዎች ፍጻሜውን አግኝቷል። በዚህም ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ እና በዜግነት ሆላንዳዊ የሆነችው ሲፋን ሀሰን አንደኛ ወጥታለች። ለመጀመሪያ ጊዜ በማራቶን ውድድር ላይ የተሳተፈችው ሲፋን ርቀቱን በ2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ37 ማይክሮ ሰከንድ አጠናቃለች። ኢትዮጵያዊቷ መገርቱ አለሙ ሁለተኛ ጀፕችርችር ፒሬዝ ከኬንያ ሶስተኛ ወጥተዋል። በርቀቱ ተጠብቃ የነበረችው አልማዝ አያና ውድድሯን በሰባተኝነት አጠናቃለች። በወንዶች የማራቶን ውድድር ደግሞ ኬንያዊው ኬልቪን ኪፕቱም በ2 ሰዓት ከአንድ ደቂቃ ከ25 ማክሮ ሰከንድ አንደኛ ሲሆን ሌላኛው ኬንያዊ ጂዎፍሪ ካምዎሮር ሁለተኛ እንዲሁም ኢትዮጵያዊው ታምራት ቶላ ደግሞ ሶስተኛ ሆነው አጠናቀዋል። ልኡል ገብረስላሴ እና ሰይፉ ቱራ ደግሞ አራተኛ እና አምስተኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁ የኢትዮጵያ አትሌቶች ናቸው። በውድድሩ ተጠብቀው የነበሩት…
Read More
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ የበለጠ አጓጊ ሆኗል

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ የበለጠ አጓጊ ሆኗል

የፕሪሚየር ሊጉ መሪ አርሰናል ነጥብ ጣለ። በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ 31ኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል ከ ዌስትሀም ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ ውጤት ተጠናቋል። የአርሰናልን ግቦች ጋብሬል ጄሱስ እና ማርቲን ኦዴጋርድ ሲያስቆጥሩ የዌስትሀምን የአቻነት ግቦች ቤንራህማ እና ጃርድ ቦውን አግብተዋል። የአርሰናል የመሀል ሜዳ ተጨዋች ማርቲን ኦዴጋርድ በውድድር አመቱ አስራ አንደኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል። ከሜዳው ውጪ የተጫወተው አርሰናል በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ነጥቡን ሰባ አራት ያደረሰ ሲሆን ቀሪ ጨዋታ ካለው ተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ አራት ዝቅ ብሏል። ዌስትሀም በበኩሉ በ31 ነጥብ አስራ አምስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል። በቀጣይ የእንግሊዝ መርሀ ግብር አርሰናል ከ ሳውዝሀምፕተን እንዲሁም ዌስትሀም ከ በርንማውዝ…
Read More
የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከሀላፊነታቸው ለቀቁ

የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከሀላፊነታቸው ለቀቁ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከሰሞኑ የስራ የመልቀቂያ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ማስገባታቸው ሲገለጽ ነበር። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በድረገጹ እንደገለጸው ከአሰልጣኝ ውበቱ ጋር በስምምነት መለያየቱን አስታውቋል። ፌዴሬሽኑ ከአሰልጣኙ የቀረበለትን የስራ መልቀቂያ ተቀብሎ ማጽደቁን ገልጾ አሰልጣኙ እስካሁን ላደረጉት ስራ ምስጋናውን አቅርቧል። አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በኢትዮጵያ ልምድ ካላቸው አንጋፋ አሰልጣኞች መካከል አንዱ ሲሆኑ ከኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ጋር በመሆን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን አሸንፈዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ከ2020 ጀምሮ በማሰልጠን ላይ ያሉት አሰልጣኝ ውበቱ በኮትዲቯር አዘጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በጊኒ ብሔራዊ ቡድን ሁለት ጨዋታዎችን ተሸንፈዋል። የ45 ዓመቱ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የግብጽ ብሔራዊ ቡድንን 2 ለ 0 ማሸነፋቸውን ተከትሎ…
Read More
ሞ ፋራህ የፖርት-ጄንቲል 10 ኪሎ ሜትር ውድድርን በሰባተኛነት አጠናቀቀ

ሞ ፋራህ የፖርት-ጄንቲል 10 ኪሎ ሜትር ውድድርን በሰባተኛነት አጠናቀቀ

በሳሙኤል አባተ ሞ ፋራህ በፖርት-ጄንቲል 10 ኪሎ ሜትር ውድድርን በሰባተኛነት አጠናቀቀ። ሞ ፋራህ የጋቦን ፖርት-ጄንቲል 10 ኪሎ ሜትር ሩጫ በ30 ደቂቃ ከ41 ሰከንድ ሰባተኛ ሆኖ አጠናቋል። የአራት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮን የሆነው ሞ ፋራህ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ለሚካሄደው የለንደን ማራቶን ውድድር በኢትዮጵያ ልምምዱን አድርጓል ተብሏል። አትሌቱ 2023 ጡረታ ከመውጣቱ በፊት የመጨረሻው የውድድር ዓመቱ እንደሚሆን ባለፈው በጥር ወር አስታውቋል። ጋቦን ላይ ኬንያዊው ቪንሴንት ኪፕኬሞይ በ28 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ አንደኛ በመውጣት አሸንፏል። ፋራህ እ.ኤ.አ. በ2022 የለንደን ማራቶን በሽንጥ ጉዳት ምክንያት ያልተሳተፈ ሲሆን፤ የዘንድሮው ውድድር ከ2019 በኋላ የመጀመሪያው ሙሉ ማራቶን ይሆናል ተብሏል። ለብሪታኒያዊው የመጨረሻ የለንደን ማራቶን ውድድር እንደሚሆን የሚጠበቅ ሲሆን፤ ቀነኒሳ በቀለን ጨምሮ በታሪክ…
Read More
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የስራ መልቀቂያ ማስገባታቸው ተገለጸ።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የስራ መልቀቂያ ማስገባታቸው ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የመልቀቂያ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስገብተዋል ተብሏል። የአሰልጣኙን የመልቀቂያ ጥያቄ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እየተወያዩበት እንደሆነ ትርታ ስፖርት ዘግቧል። የስራ አስፈፃሚ አባላቱ በሁለት ሀሳብ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል። አንዳንዶቹ አሁኑኑ ይሰናበት ጥያቄውን እንቀበል ያሉ ሲሆን ሌሎች አባላት ደግሞ ቀሪ ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን ይጨርስ እያሉ ይገኛሉ ተብላል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በቅርቡ ከአሰልጣኙ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት ውሳኔውን የሚያሳውቅ ይሆናል። አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በኢትዮጵያ ልምድ ካላቸው አንጋፋ አሰልጣኞች መካከል አንዱ ሲሆኑ ከኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ጋር በመሆን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን አሸንፈዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ከ2020 ጀምሮ በማሰልጠን ላይ ያሉት አሰልጣኝ ውበቱ…
Read More
ሊዮኔል ሜሲ በእግር ኳስ ህይወቱ 800ኛ ጎሉን አስቆጠረ

ሊዮኔል ሜሲ በእግር ኳስ ህይወቱ 800ኛ ጎሉን አስቆጠረ

አርጀንቲናዊው የዓለም ኮኮብ ሊዮኔል ሜሲ በእግር ኳስ ህይወቱ 800ኛ ጎሉን ከመረብ አገናኝቷል። በኳታር አዘጋጅነት የተካሄደው የዓለም ዋንጫን ያሸነፈው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አምበል ሊዮኔል ሜሲ በህይወት ዘመኑ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ወደ 800 ከፍ አድርጓል። የሰባት ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊው ሜሲ ሀገሩ አርጀንቲና ከፓናማ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ተጫውታ 2ለ0 አሸንፋለች። የአርጀንቲናን የማሸነፊያ ጎሎች ቲያጎ አልማዳ በ11ኛው ደቂቃ እንዲሁም ሊዮኔል ሜሲ ደግሞ በ89ኛው ደቂቃ አስቆጥራል። ሊዮኔል ሜሲ ለአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተሰልፎ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ወደ 99 ከፍ ሲያደርግ በቀጣይ የማጣሪያ ጨዋታቆች 100ኛ ግቡን እንደሚያስቆጥር ይጠበቃል። የቀድሞው የባርሴሎና እግር ኳስ ክለብ ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲ ለባርሳ 672 እንዲሁም አሁን እየተጫወተበት ላለው ፒኤስጂ ደግሞ 29 ጎሎችን አስቆጥሯል። ሊዮኔል ሜሲ…
Read More
ዋሊያዎቹ ከጊኒ ጋር ለሚያደርጉት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ ሞሮኮ አቀኑ

ዋሊያዎቹ ከጊኒ ጋር ለሚያደርጉት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ ሞሮኮ አቀኑ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ አቻው ጋር ለሚያደርገው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ ሞሮኮ አቅንቷል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን በኮትዲቯር አስተናጋጅነት በሚካሄደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ ከጊኒ ብሔራዊ ቡድን ጋር የምድብ ማጣሪያ ጨዋታውን መጋቢት 15 እና 18 ቀን 2015 ዓ.ም በሞሮኮ ያደርጋል። የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ ከመጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ልምምዳቸውን ሲያደርጉ ቆይተዋል። ዋልያዎቹ ከትናንት በስቲያ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከሩዋንዳ አቻቸው ጋር ባደረጉት የአቋም መለኪያ ጨዋታ በከነዓን ማርክነህ ግብ 1 ለ 0 ማሸነፋቸው ይታወቃል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ አራት ከግብጽ፣ ከማላዊና ከጊኒ ጋር ተደልድሏል፡፡ እስከአሁን…
Read More
የሎስ አንጀለስ ማራቶን በኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊነት ተጠናቀቀ

የሎስ አንጀለስ ማራቶን በኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊነት ተጠናቀቀ

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ የማራቶን ውድድሮችን አሸነፉ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ የማራቶን ውድድሮች ድል ማስመዝገብ ችለዋል። በቻይና ሸንዤን በተደረገ ማራቶን በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያውያኑ ድል የቀናቸው ሲሆን፤በወንዶች አትሌት ባንታየሁ አዳነ በሴቶች አገሬ ታምር በአንደኝነት አጠናቀዋል። በአሜሪካ ሎሳንጀለስ በተካሄደ የወንዶች ማራቶን አትሌት ጀማል ይመር ቀዳሚ መሆን ሲችል ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት የማነ ጸጋዬ ደግሞ ሁለተኛ ሆኖ ውድድሩን ጨርሷል። በባርሴሎና በተደረገ የማራቶን ውድድርም ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ዘይነባ ይመር ውድድሩን በአንደኝነት ስታጠናቅቅ በአሜሪካ የኒዮርክ ግማሽ ማራቶን ውድድር ላይ ደግሞ በሴቶች አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ ሁለተኛ ሆና ውድድሯን አጠናቃለች። በታይዋን ታይፔ በተደረገው የሴቶች ማራቶን ውድድርም በቀለች ጉደታ፣ መሰረት ድንቄ እና ገበያነሽ አየለ ከአንድኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃን…
Read More