20
Mar
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ የማራቶን ውድድሮችን አሸነፉ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ የማራቶን ውድድሮች ድል ማስመዝገብ ችለዋል። በቻይና ሸንዤን በተደረገ ማራቶን በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያውያኑ ድል የቀናቸው ሲሆን፤በወንዶች አትሌት ባንታየሁ አዳነ በሴቶች አገሬ ታምር በአንደኝነት አጠናቀዋል። በአሜሪካ ሎሳንጀለስ በተካሄደ የወንዶች ማራቶን አትሌት ጀማል ይመር ቀዳሚ መሆን ሲችል ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት የማነ ጸጋዬ ደግሞ ሁለተኛ ሆኖ ውድድሩን ጨርሷል። በባርሴሎና በተደረገ የማራቶን ውድድርም ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ዘይነባ ይመር ውድድሩን በአንደኝነት ስታጠናቅቅ በአሜሪካ የኒዮርክ ግማሽ ማራቶን ውድድር ላይ ደግሞ በሴቶች አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ ሁለተኛ ሆና ውድድሯን አጠናቃለች። በታይዋን ታይፔ በተደረገው የሴቶች ማራቶን ውድድርም በቀለች ጉደታ፣ መሰረት ድንቄ እና ገበያነሽ አየለ ከአንድኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃን…