ስፖርት

የጣልያኑ ሊሞንታ ስፖርት ኩባንያ በኢትዮጵያ ስታዲየሞችን ለማልማት ድርድር ጀመረ

የጣልያኑ ሊሞንታ ስፖርት ኩባንያ በኢትዮጵያ ስታዲየሞችን ለማልማት ድርድር ጀመረ

በዓለም እና ስፔን እግር ኳስ ታሪክ ቀዳሚ የሆነው የሪያል ማድሪድን ስታዲየም ቤርናቢዩ ሜዳ የሰራው ግዙፍ ተቋም በአዲስ አበባ ይገኛል። ተቀማጭነቱን በጣልያን ያደረገው ሊሞንታ ስፖርት (Limonta Sport) ለስፖርት ሜዳዎች የሚሆኑ ሰው ሰራሽ (Artificial) እና ቅልቅል (Hybrid) ሳሮችን በማምረት እና በማንጠፍ ታዋቂነትን ያተረፈ የስፖርት መሰረተ ልማት ተቋም ነው። በፊፋ እውቅና ያለው ይህ ተቋም ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል። ኩባንያው በመላው ዓለም አርቴፊሻል እና ሃይብሪድ የስታዲየም ውስጥ ሳሮችን በማምረት ይታወቃል። ኩባንያው ከሚያመርታቸው የስታዲየም ውስጥ ሳር መካከል ድብልቁ ወይም ሀይብሪዱ 95 ከመቶው የተፈጥሮ ሳር ሲሆን 5 ከመቶው ደግሞ አርቲፊሻል ሴንቴቲክ ነው ። ሊሞንታ ኩባንያ የሚያነጥፈው እና የሚያበቅለው ሳሩ በዝናብ ወቅት ውሃን በ5 ደቂቃ ውስጥ የማፍሰስ ችሎታ…
Read More
ትዕግሥት አሰፋ እና ዮሚፍ ቀጄልቻ የዓመቱ ምርጥ አትሌት ዕጩ ሆኑ

ትዕግሥት አሰፋ እና ዮሚፍ ቀጄልቻ የዓመቱ ምርጥ አትሌት ዕጩ ሆኑ

የዓለም አትሌቲክስ በሁለቱም ፆታ የ2025 የዓመቱ የጎዳና ላይ ምርጥ አትሌት ዕጩዎችን ይፋ አድርጓል። በዚህም ኢትዮጵያ አትሌት ትዕግሥት አሰፋ እና ዮሚፍ ቀጄልቻን በዓመቱ በሁለቱም ፆታ ምርጥ ብቃት ካሳዩ አምስት አትሌቶች መካከል ተብለው እጩ ሆነዋል። በሴቶቹ አትሌት ትዕግሥት አሰፋ ከኬንያውያኑ አትሌቶች ፔሬስ ጄፕቺርቺር እና አግኔስ ንጌቲች፣ ለኔዘርላንድስ ከምትሮጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሲፈን ሀሰን እና ከስፔናዊቷ ማሪያ ፔሬዝ ጋር ምርጥ አምስት ውስጥ መግባት ችላለች። በወንዶቹ ደግሞ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ ከብራዚላዊው አትሌት ካይኦ ቦንፊን፣ ካናዳዊው አትሌት ኢቫን ዱንፊ፣ ኬንያዊው አትሌት ሳባስቲያን ሳዌና ከታንዛኒያዊው አልፎንስ ሲምቡ ጋር ምርጥ አምስት መግባት ችሏል። በለንደን ማራቶን አሸናፊ የነበረችው አትሌት ትዕግሥት አሰፋ በውድድር ዓመቱ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና 2ኛ…
Read More
ኢትዮጲያ ከ34 አመት በኋላ ያለ ወርቅ ሻምፒወናዉን አጠናቀቀች

ኢትዮጲያ ከ34 አመት በኋላ ያለ ወርቅ ሻምፒወናዉን አጠናቀቀች

በጃፖን ቶኪዮ አስተናጋጅነት ሲካሄድ  የቆየዉ  የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጲያ በታሪክ ለሁለተኛ ጊዜ ያለ ምንም ወርቅ አጠናቃለች። ኢትዮጲያ በዚህ መድረክ በታሪክ ከ34 አመት በኅላ አንድም ወርቅ ሳታገኝ ያጠናቀቀችበት የአለም ሻምፒዮና ሆኖ ተመዝግቧል። በውድድሩ የመጨረሻ ቀናት በተደረገዉ የ5000 ሜትር የወንዶች ፍፃሜ ዉድድር ምን አልባት ወርቅ ይገኝበታል ተብሎ ቢጠበቅም ኢትዮጵያ ሜዳሊያ  ዉስጥ መግባት ሳትችል ቀርታለች። ኢትዮጲያን የወከሉት አትሌት ሀጎስ ገብረ ሂወት እና አትሌት ቢኒያም መሀሪ ዉድድራቸዉን 5ኛ እና 13ኛ  ደረጃን ይዘዉ አጠናቀዋል። ኢትዮጲያ እስካሁን ባደረገቻቸዉ ስምንት የፍፃሜ ዉድድሮች ሁለት ብር እና ሁለት ነሀስ ስታገኝ በድምሩ አራት ሜዳሊያዎችን ብቻ ሰብስባ በታሪኳ በእጅጉ ደካማ የሆነዉን የቶኪዮ አለም ሻምፒዮና ቆይታዋን ደምድማለች። አሜሪካ በውድድሩ 16 የወርቅ ሜዳሊያ…
Read More
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቹ ከነዓን ማርክነህ የኦማን ክለብን ተቀላቀለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቹ ከነዓን ማርክነህ የኦማን ክለብን ተቀላቀለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወይም (ዋልያዎቹ) የፊት መስመር እና የመሐል ሜዳ ተጫዋች ከንአን ማርክነህ ወደ አዲስ ክለብ ለማምራት መስማማቱ ተገልጿ። ከንአን ማርከነ በአዲሱ የውድድር ዘመን ወደ ኦማን ሊግ በማቅናት አል ሸባብ ክለብ ለመጫወት ከስምምነት መድረሱ ታውቋል። ከብሔራዊ ቡድን ጨዋታ መልስ ወደ ኦማን ያቀናው ከንአን ማርክነህ በትላንትናው ዕለት የህክምና ምርመራውን በተሳካ ሁኔታ አልፏል። ከንአን ከህክምና ምርመራ በኃላ በክለቡ የሚያቆየውን የአንድ አመት ኮንትራት ሲፈራረም ክለቡ በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጎታል። ከንአን ያለፈውን የውድድር ዓመት በሊቢያ ሊግ ስኬታማ ጊዜን ሲያሳልፍ ለአል መዲና እና ሸባብ አል ጋሂር እግር ኳስ ክለቦች መጫወቱ ይታወሳል። ከንአን ማርከነ በሊቢያ ቆይታው በ14 ጨዋታዎች ስድስት ጎሎችን አስቆጥሯል። የከንአን አዲሱ ክለብ አል ሸባብ…
Read More
ጃፓን ለአትሌት አበበ ቢቂላ የመታሰቢያ መንገድ ሰየመች

ጃፓን ለአትሌት አበበ ቢቂላ የመታሰቢያ መንገድ ሰየመች

በጃፓን ካሳማ ከተማ ለአትሌት አበበ ቢቂላ የመታሰቢያ መንገድ ተሰየመ በጃፓን ካሳማ ከተማ አትሌት አበበ ቢቂላን ለማስታወስ የግማሽ ማራቶን መንገድ በስሙ መሰየሙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። የስያሜ ስነ-ስርዓቱ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበልን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሃደራ አበራን፣ በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዳባ ደበሌን እና የካሳማ ከተማ ከንቲባን ጨምሮ በርካታ ባለስልጣናት በተገኙበት ተከናውኗል። በስነ-ስርዓቱ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ይህ የመታሰቢያ ስያሜ ለአትሌቱ ክብር ከመስጠት በተጨማሪ በኢትዮጵያ እና በጃፓን መካከል ያለውን ጥብቅ ወዳጅነት እና የባህል ትስስር የሚያሳይ እንደሆነ ገልጸዋል። አትሌት አበበ ቢቂላ በ1964ቱ የቶኪዮ ኦሎምፒክ ያገኘው ድል ኢትዮጵያን ያስጠራ ብቻ ሳይሆን በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግንኙነትም አጠናክሯል ብለዋል። በጃፓን…
Read More
ሴኔጋላዊው አል ሀጂ ዲዮፍ የዋናው ስፖርት ኩባንያ አምባሳደር ሆነ

ሴኔጋላዊው አል ሀጂ ዲዮፍ የዋናው ስፖርት ኩባንያ አምባሳደር ሆነ

የሴኔጋሉ የእግር ኳስ ኮኮብ አልሀጂ ዲዩፍ በኢትዮጵያ ላለ አንድ የስፖርት ትጥቅ አልባሳት አምራች ኩባንያ አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል። ስምምነቱ በአዲስ አበባ የተካሄደ ሲሆን "ከአፍሪካ ምርጡ ትጥቅ አምራች ጋር ስምምነት ፈፅሜያለሁ “ ብሏል ዲዩፍ። ሴኔጋላዊው የቀድሞ ታሪካዊ ተጨዋች ኤል ሀጂ ዲዩፍ የኢትዮጵያው ትጥቅ አምራች ብራንድ ዋናው አምባሳደር በመሆን መሾሙን ኩባንያው ገልጿል። ታሪካዊው ተጫዋች የዋናው ስፖርት አልባሳት በሚመረትበት አዲስ አበባ ሀብቴ ጋርመንት እና ህትመትን ከጎበኘ በኋላ ስምምነት ፈፅሟል። “ ከአፍሪካ ምርጡ ትጥቅ አምራች ጋር ስምምነት ፈፅሜያለሁ “ ሲል ዲዩፍ ከጉብኝቱ በኋላ ተናግሯል። አክሎም  "በቀጣይ ከትልልቅ ታሪካዊ ተጫዋቾች ጄጄ ኦኮቻ ፣ ኑዋንኩ ካኑ ፣ አዲባየር እና ካሊዱ ፋዲጋን በማምጣት ዋናውን በአለም ገናነቱን እናሳየለን "…
Read More
የለንደን ማራቶን በኢትዮጵያዊያን እና ኬንያዊያን የበላይነት ተጠናቀቀ

የለንደን ማራቶን በኢትዮጵያዊያን እና ኬንያዊያን የበላይነት ተጠናቀቀ

ዛሬ ፍጻሜውን ባገኘው የለንደን ማራቶን ኢትዮጵያዊያን እና ኬንያዊያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል። በ2025 በሴቶች ውድድር ትግስት አሰፋ በአንደኝነት ስታጠናቅቅ በወንዶች ደግሞ ኬንያዊው ሴባስቲያን አሸንፏል። አትሌት ትግስት አሰፋ በሴቶች ብቻ የአለም የማራቶን ሪከርድን ( 2:16:16 ) 2:15:50 በሆነ ሰዓት መስበር ችላለች። ታሪካዊቷ ብሪታንያዊት የማራቶን ሯጭ ፓውላ ራድክሊፍ በሰጠችው አስተያየት አትሌት ትዕግስት አሰፋ ውድድሩን የጨረሰችበትን መንገድ አድንቃ ጀግና አትሌት ነሽ ብላታለች፡፡ አትሌት ትግስት አሰፋ ውድድሯን 2:15:50 በሆነ ሰዓት በአንደኝነት ማጠናቀቋን ተከትሎ በሴቶች ብቻ የአለም የማራቶን ሪከርድን (2:16:16 ) 2:15:50 በሆነ ሰዓት መስበር ችላለች። ኬንያዊቷ አትሌት ጄፕኮስፔ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ስታጠናቅቅ በውድድሩ ስትጠበቅ የነበረችው ኔዘርላንዳዊቷ አትሌት ሲፋን ሀሰን ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አተናቃለች። በተመሳሳይ የወንዶች…
Read More
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከለንደን ማራቶን ውድድር ውጪ ሆነ

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከለንደን ማራቶን ውድድር ውጪ ሆነ

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከእሁዱ የ2025 ለንደን ማራቶን ውድድር ውጪ መሆኑን አዘጋጆቹ ይፋ አድርገዋል። አትሌቲ ቀነኒሳ በቀለ በጉዳት ምክንያት በለንደን ማራቶን ውድድር መሳተፍ እንደማይችል አስታውቋል። አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በፌስቡክ ገጹ እንዳለው “በእሁዱ የለንደን ማራቶን ወደ ውድድር ለመመለስ ጓጉቼ ነበር ባለመሳካቱ በጣም ተበሳጭቻለሁ“ ብሏል። ከውድድሩ ውጪ የሆነው በጉዳት መሆኑን ያረጋገጠው ቀነኒሳ በውድድሩ ለሚካፈሉ አትሌቶች መልካም ምኞቱን ገልጿል። በለንደን ማራቶን ውድድር አንደኛ ሆኖ ለሚያጠናቅቅ ተወዳዳሪ 55 ሺህ ዶላር ሁለተኛ 33 ሺህ እንዲሁም ሶስተኛ ለሚወጣ ተወዳዳሪ ደግሞ 22 ሺህ ዶላር ሽልማት ያገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያዊ የረጅም ርቀት ንጉስ የሆነው ቀነኒሳ በቀለ የፊታችን እሁድ በሚደረገው የለንደን ማራቶን እንደማይሳተፍ ይፋ አድርጓል ። ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ላይ የአሜሪካው አለምአቀፍ…
Read More
አደይ አበባ ስታዲየም ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ 18.6 ቢሊየን ብር ተመደበ

አደይ አበባ ስታዲየም ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ 18.6 ቢሊየን ብር ተመደበ

ኢትዮጵያ የብሔራዊ ስታድየሟን ግንባታ በሁለት ዓመት ውስጥ ለማጠናቀቅ ማቀዷ ተገለጸ 62 ሺህ ተመልካች የመያዝ አቅም ያለው አደይ አበባ ስታዲየም ግንባታው ከተጀመረ 10 ዓመት አልፎታል በአዲስ አበባ እየተገነባ የሚገኘውን አደይ አበባ ስቴዲየም ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ 18 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልገው ተገልጿል፡፡ አሁን የአደይ አበባ ስቴዲየም ቀሪ ስራዎችን ከሁለት አመት ባነሰ ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ተብሏል። የስታዲየሙን የማጠናቀቂያ ሥራዎች ለማከናወን 18 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ውል መገባቱን የባህልና ስፖርት ሚንስቴር አስታውቋል። ኢትዮጵያ በሁሉም ክልሎች አንድ ስታዲየም ያላት ቢህንም ከዚህ ውስጥ አንዱም የካፍን ደረጃ የማያሟላ ሲሆን በአዲስ አበባ እየተገነባ ያለው እና 62 ሺህ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ያለው አደይ አበባ ስታዲየም ግንባታው በተለያዩ ምክንያቶች መጠናቀቅ…
Read More
አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ የሮጠበት ማልያ በ2400 ዶላር ተሸጠ

አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ የሮጠበት ማልያ በ2400 ዶላር ተሸጠ

በበርካታ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ስኬታማ አትሌት የሆነው ሀይሌ ገብረስላሴ የሮጠበት አንድ ማልያ በ2 ሺህ 400 ዶላር ተሸጧል፡፡ በአዲስ አበባ በተካሄደ በዚህ ጨረታ ላይ የቀረበው ይህ ማልያ አትሌት ሀይሌ በ1992 በደቡብ ኮሪያ ሴኡል ከተማ በተካሄደው የ10 ሺህ ሜትር ውድድርን ያሸነፈበት ማልያ ነበር፡፡ ይህ ውድድር ለአትሌት ሀይሌ ገብረ ስላሴ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን የጀመረበት ወቅት እንደነበርም ተገልጿል፡፡ የታላቁ ሩጫ መስራች እና ባለቤት አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ለጨረታ ቀርቦ 2 ሺሕ 400 ዶላር የተሸጠው ማልያ የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን ለማጠናከር ይውላልም ተብሏል፡፡ በጨረታው የታላቁ ሩጫ ባዘጋጀው የእራት ግብዣ ፕሮግራም ላይ የኃይሌ ገ/ሥላሴ የሮጠበት ማልያ፤ በእንግሊዛዊ ተጋባዥ እንግዳ አሸንፏል። ይህንን የማልያ ጨረታ እንግሊዛዊ ዜግነት ያለው…
Read More