24
May
የተባበሩት መንግስታት የህጻናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) ባወጣው ሪፖርት በኢትዮጵያ 8 ነጥብ 85 ሚሊየን ህጻናት በትምህርት ገበታ ላይ አይገኙም ብሏል። የሀገሪቱ የትምህርት ሁኔታ አሁንም በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ይገኛል ያለው ዩኒሴፍ ለዚህም ዋነኛው ምክንያት በሀገሪቱ በበርካታ ቦታዎች እየተባባሰ የመጣው ግጭት ነው ሲል ጠቁሟል። በተያዘው የፈረንጆቹ አመት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት (ጥር፣ የካቲትና መጋቢት) በሀገሪቱ የተዘጉ ትምህርት ቤቶች ቁጥር በ18 በመቶ ጨምሯል ያለው ዩኒሴፍ ጉዳት የደረሰባቸው የትምህርት ቤቶችን ቁጥር በ5 ነጥብ 5 በመቶ መጨመሩንም ጠቁሟል። በሀገሪቱ 6 ሺ 770 ትምህርት ቤቶች ጉዳት ሲደርስባቸው 6 ሺ 410 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ተዘግተዋል ሲል በየሶስት ወሩ በትምህር ዙሪያ በሚያሳትመው ኒውስሌተር ላይ ባሰፈረው ሪፖርት አስታውቋል። በትምህርት ገበታ ላይ…