10
Nov
ከመስከረም ጀምሮ በሳዑዲ አረቢያ በተለያዩ እስር ቤቶችና ማቆያ ማዕከላት የሚገኙ ከ17 ሺሕ በላይ ዜጎች ወደ ሀገር መመለሳቸው ተገልጿል። በሳዑዲ አረቢያ በተለያዩ እስር ቤቶችና ማቆያ ማዕከላት የሚገኙ ዜጎችን ከ17 ሺሕ በላይ ዜጎችን ከመስከረም 05 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በተሰራ ሥራ መመለስ መቻሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ሚኒስቴሩ በተለያዩ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው የመመለሱ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል፡፡ "ከውጭ ግንኙነት ቁልፍ ሥራዎች አንዱ የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ነው" ያለው ሚኒስቴሩ ፖሊሲውን በአግባቡ ለመተግበር በውጭ ሀገር የሚኖሩ ዜጎችን መብት ማስከበር፣ ለዜጎች ተገቢ የቆንስላ አገልግሎት መስጠት፣ በሄዱበት ሀገር ሕጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ የሌላቸውና የሀገሩ መንግሥት ዜጎቻችን ሀገራቸውን እንዲለቁ ሲወስን መብታቸው፣ ክብራቸውና…