Amhara

የባህር ሀይል ወታደሮች በአማራ ክልል ውጊያ እየተሳተፉ መሆኑን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ገለጸ

የባህር ሀይል ወታደሮች በአማራ ክልል ውጊያ እየተሳተፉ መሆኑን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ገለጸ

የሀገር መከላከያ ሰራዊት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ እንዳለው "የኢትዮጵያ ባህር ሀይል ማሪን ኮማንዶ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ተሰማርቷል" ብሏል። ተቋሙ የባህር ሀይል ዋና አዛዥ ተወካይ ሬር አድሚራል ናስር አባዲጋን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው "ጽንፈኛ" ባላቸው ቡድን አባላት ላይ እርምጃ እንደወሰደ ገልጿል። የኢትዮጵያ ባህር ሀይል ማሪን ኮማንዶዎች በሰሜን ሸዋ ዞን ባሉ ወረዳዎች እንደተሰማሩ እና ግዳጃቸውን እየተወጡ እንደሆነም አዛዡ መናገራቸው ተገልጿል። እንዲሁም ማሪን ኮማንዶ በመርከብ ላይ በባህር ከሚሰጠው ተልዕኮ በተጨማሪ በማንኛውም ጊዜ ግዳጁን የሚወጣ ሀይል እንደሆነም ሬር አድሚራል ናስር አባድጋ ተናግረዋል ተብሏል። ማሪን ኮማንዶ ከአማራ ክልል የጸጥታ ሀይሎች ጋር በመሆን በወሰዳቸው እርምጃዎች የክልሉ ሰላም እየተሻሻለ መምጣቱንም በዚሁ ዘገባ ላይ ተጠቅሷል። የፌደራል መንግሥት…
Read More
አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ለምን በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ላለው ጦርነት ትኩረት ነፈጉ?

አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ለምን በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ላለው ጦርነት ትኩረት ነፈጉ?

በፌደራል መንግስት እና የትግራይ ታጣቂዎች መካከል የተካሄደው እና ለሁለት ዓመት የዘለቀው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በደቡብ አፍሪካ መዲና ፕሪቶሪያ በተፈረመ የሰላም ስምምነት መቆሙ ይታወሳል፡፡ ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 2015 ዓ.ም የተካሄደው ይህ ጦርነት ተፋላሚዎች ወደ ተኩስ አቁም እንዲሄዱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጨምሮ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት ቡድን ሰባት፣ ብሪታንያ እና ሌሎችም ተጽዕኖ ፈጣሪ ሀገራት በጋራ እና በተናጠል የተለያዩ ጫናዎችን ሲያደርጉ ነበር፡፡ ጦርነቱ በፍጥነት ባለመቆሙ ምክንያትም ሀገራት በኢትዮጵያ ያላቸውን ፕሮግራሞች ማቋረጥ፣ ቢሮ መዝጋት፣ እንደ አግዋ ኤነት ለኢትዮጵያ ተሰጥተው የነበሩ የገበያ እድሎችን መከልከል፣ ተፈቅደው የነበሩ ብድሮችን መከልከል  እና የቀጥታ በጀት ድጋፎችን ማቋረጥ በኢትዮጵያ ላይ ከተደረጉ ጫናዎች ዋነኞቹ ነበሩ፡፡…
Read More
የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከአንድ ዓመት በኋላ ዳግም ተቀሰቀሰ

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከአንድ ዓመት በኋላ ዳግም ተቀሰቀሰ

የትግራይ ታጣቂዎች ወደ አማራ ክልል ዘልቀው ወረዳዎን እና ቀበሌዎችን በሀይል እንደተቆጣጠሩ ተገልጿል፡፡ የአማራ ክልል መንግስት ባወጣው መግለጫ ህወሓት በፕሪቶሪያ የተፈረመውን የዘላቂ የሰላም ስምምነት በመጣስ ለአራተኛ ጊዜ ወረራ ፈጽሞብኛል ሲል ከሷል። በፌደራል መንግስት በኩል ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ውይይት ለማድረግ መጣሩን የገለጸው ክልሉ፣ ህወሓት የሰላም አማራጮችን ወደ ጎን በመተው በስምምነት አወዛጋቢ ተብለው የተለዩትን የራያ አላማጣ፣ የራያ ባላ፣ የኦፍላ፣ የኮረም እና ዛታ አካባቢዎችን ወርሯል ብሏል። የክልሉ መንግስት እንዳለው ህወሓት ለአራተኛ ዙር ወረራ በመፈጸም በህወሓት እና በፌደራል መንግስት መካከል ከተካሄዱት "ከባለፉት ሶስት ዙር ደም አፋሳሽ ጦርነቶች" አለመማሩን የሚያሳይ ነው። የአማራ ክልል ወረራ ተፈጽሞባቸዋል ያላቸው ቦታዎች እና የወልቃይት፣ ጠገዴ እና ጠለምት በ2013 ጦርነት ከመቀስቀሱ…
Read More
ኢትዮጵያ ኢንተርኔት በመዝጋቷ ምክንያት 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማጣቷ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ኢንተርኔት በመዝጋቷ ምክንያት 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማጣቷ ተገለጸ

ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን በመከታተል እና ሪፖርቶችን በማውጣት የሚታወቀው ኔት ብሎክስ የ2023 ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህ ተቋም ሪፖርት መሰረት ኢትዮጵያ ከኢንተርኔት በመዝጋት ገቢ ካጡ ሀገራት መካከል ከሩሲያ በመቀጠል ከፍተኛ ገቢ ያጣች ሀገር ተብላለች፡፡ ሩሲያ 113 ሚሊዮን ዜጎቿን ከኢንተርኔት ውጪ በማድረጓ አራት ቢሊዮን ዶላር ገቢ ስታጣ ኢትዮጵያ ደግሞ 30 ሚሊዮን ገደማ ዜጎች ከኢንተርኔት አገልግሎት ውጪ ተደርገዋል፡፡ ሆን ተብሎ በመንግስት እንደተወሰደ የተገለጸው ይህ ኢንተርኔት ማቋረጥ ኢትዮጵያ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አሳጥቷታል ተብሏል፡፡ ሀገራት ኢንተርኔት አገልግሎቶችን የሚያቋርጡት በሶስት ምክንያት ነው የተባለ ሲሆን ተቃውሞዎችን ለማፈን፣ የሀሳብ ነጻነትን ለመገደብ እና የምርጫ ስራዎች እንዳይታወኩ በሚል እንደሆነም ተገልጿል፡፡ 25 የዓለማችን ሀገራት ኢንተርኔት አቋርጠዋል የተባለ ሲሆን…
Read More
በእነ ክርስቲያን ታደለ መዝገብ የተከሰሱ ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

በእነ ክርስቲያን ታደለ መዝገብ የተከሰሱ ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

የፍትህ ሚኒስቴር በእነ ክርስቲያን ታደለ መዝገብ ባሉ 52 ተጠርጣሪዎች ላይ የፖለቲካ ርዕዮትን በሀይል ለማስፈጸም ተንቀሳቅሰዋል፣ በ1996 ዓም የወጣውን የወንጀል ህግ እንዲሁም የሽብር ወንጀሎችን ለመከላከል የወጣውን ህግ ጥሰዋል በሚል ክስ መስርቷል፡፡ በዚህ ክስ መዝገብ ስርም ክርስቲያን ታደለ፣ ዮሀንስ ቧያለው፣ ካሳ ተሸገር (ዶ/ር) ጫኔ ከበደ፣ እስክንድር ነጋ፣ ዘመነ ካሴ፣ አበበ ፈንታው፣ አሰግድ መኮንን፣ መከታው ማሞ፣ ፈንታሁን ሙሃባ እና ሌሎችም ተካተዋል፡፡ ከ52ቱ ተከሳሾች መካከል 14ቱ ተጠርጣሪዎች ልደታ በሚገኘው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህገ መንግስት እና ሽብር ወንጀሎች ችሎት የቀረቡ ሲሆን የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ እና ቤተሰቦች መገኘታቸው ተገልጿል፡፡ የተጠርጣሪዎች ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ለአልዐይን እንዳሉት በችሎቱ መገኘታቸውን ገልጸው ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን ማንነት ካረጋገጠ በኋላ የተለያዩ ትዕዛዞችን…
Read More
በአማራ ክልል ባለው ጦርነት ምክንያት ከስድስት ሺሕ በላይ ሠራተኞች ሥራ ማቆማቸው ተገለጸ

በአማራ ክልል ባለው ጦርነት ምክንያት ከስድስት ሺሕ በላይ ሠራተኞች ሥራ ማቆማቸው ተገለጸ

ባሳለፍነው ዓመት ሚያዚያ ወር የፌደራል መንግስት የክልል ልዩ ሀይሎችን መልሼ ለማደራጀት ወስኛለሁ ማለቱን ተከትሎ ነበር በአማራ ክልል ግጭት የተከሰተው፡፡ ይህ ግጭት ቀስ በቀስ እያደገ መጥቶ ወደ ጦርነት የተቀየረ ሲሆን የቀድሞው የክልሉ መንግስት በመደበኛ የክልሉ የጸጥታ ሀይል ህግ ማስከበር እንደማይችል እና የፌደራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ በይፋ በደብዳቤ ጠይቋል፡፡ ይህን ተከትሎም ከሀምሌ 2015 ዓ.ም መጨረሻ ቀናት ጀምሮ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአማራ ክልል ለስድስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጆ የነበረ ሲሆን አዋጁ ለተጨማሪ አራት ወራት መራዘሙ አይዘነጋም፡፡ በዚህ ጦርነት ምክንትም ከስድስት ሺህ በላይ የሆኑ ሰራተኞች ስራ ማቆም እና ቤተሰቦቻቸውን መመገብ አለመቻላቸው ተገልጿል፡፡ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ከሥራ ውጭ የኾኑ ዜጎች፣ በግጭቱ ምክንያት…
Read More
ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ጀነራል ክንፈ ዳኘው እና አብዲ ኢሌ ከእስር ተፈቱ

ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ጀነራል ክንፈ ዳኘው እና አብዲ ኢሌ ከእስር ተፈቱ

በ2013 በተካሄደው ስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በባህርዳር ከተማ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲን ወክለው ተወዳድረው የተመረጡት እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ታህሳስ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ታስረው ነበር፡፡ ጠበቃቸው ሰለሞን ገዛኸኝ እንዳሉት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት በመታወቂያ ዋስትና ከእስር ተለቀዋል። የፓርላማ አባሉ ደሳለኝ ጫኔ ያለመከሰስ መብታቸው ሳይነሳ ከሁለት ወራት በፊት በጸጥታ ሀይሎች ተይዘው የታሰሩ ቢሆንም ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቆይተው ዛሬ ከእስር ተለቀው ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀላቸውን ጠበቃቸው ተናግረዋል። ባሳለፍነው ሀምሌ ወር ላይ በተመሳሳይ ከመኖሪያ ቤታቸው በጸጽታ ሀይሎች ተወስደው በእስር ላይ የነበሩት ሌላኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ ያለመከሰስ መብታቸው ከታሰሩ ከሰባት…
Read More
በእስር ላይ የነበሩት አቶ ክርስቲያን ታደለ ያለመከሰስ መብት ተነሳ

በእስር ላይ የነበሩት አቶ ክርስቲያን ታደለ ያለመከሰስ መብት ተነሳ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባ የአቶ ክርስቲያን ታደለን ያለመከሰስ መብትን  በሁለት ተቃውሞ እና በሁለት ድምጸ ተዐቅቦ አንስቷል። አቶ ክርስቲያን ታደለ ከሶስት ዓመት በፊት በተካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲን ወክለው ከቋሪት ወረዳ ተመርጠዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሪፖርታቸውን ለምክር ቤቱ በሚያቀርቡበት ወቅት ጠንካራ ጥያቄዎችን በማንሳት እና ትችቶችን በመሰንዘር የሚታወቁት አቶ ክርስቲያን ታደለ ከስድስት ወራት በፊት ታስረዋል፡፡ ያለመከሰስ መብታቸው ሳይነሳ ላለፉት ስድስት ወራት በእስር ላይ የቆዩት አቶ ክርስቲያን ታደለ በዛሬው ዕለት ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቷል፡፡ ሌላኛው የምክር ቤት አባል አቶ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ከሁለት ወራት በፊት ያለ መከሰስ መብታቸው ሳይነሳ በተመሳሳይ በእስር ላይ ያሉ ሲሆን እስካሁን ክስ ሳይመሰረትባቸው…
Read More
በአማራ ክልል ባለው ጦርነት ምክንያት 15 ቢሊዮን ብር የሚያወጣ ንብረት መውደሙ ተገለጸ

በአማራ ክልል ባለው ጦርነት ምክንያት 15 ቢሊዮን ብር የሚያወጣ ንብረት መውደሙ ተገለጸ

ባሳለፍነው ዓመት ሚያዚያ ወር የፌደራል መንግስት የክልል ልዩ ሀይሎችን መልሼ ለማደራጀት ወስኛለሁ ማለቱን ተከትሎ ነበር በአማራ ክልል ግጭት የተከሰተው፡፡ ይህ ግጭት ቀስ በቀስ እያደገ መጥቶ ወደ ጦርነት የተቀየረ ሲሆን የቀድሞው የክልሉ መንግስት በመደበኛ የክልሉ የጸጥታ ሀይል ህግ ማስከበር እንደማይችል እና የፌደራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ በይፋ በደብዳቤ ጠይቋል፡፡ ይህን ተከትሎም ከሀምሌ 2015 ዓ.ም መጨረሻ ቀናት ጀምሮ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአማራ ክልል ለስድስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጆ የነበረ ሲሆን አዋጁ ለተጨማሪ አራት ወራት መራዘሙ አይዘነጋም፡፡ የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊና የኮማንድ ፖስት ምክትል ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ጣሰው በዚህ ጦርነት ዙሪያ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በክልሉ እየተካሄደ…
Read More
በአማራ ክልል በጦርነት እና ድርቅ ምክንያት 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸው ተገለጸ

በአማራ ክልል በጦርነት እና ድርቅ ምክንያት 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸው ተገለጸ

በአማራ ክልል ባለው የጸጥታ ችግር እና ድርቅ ምክንያት 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል። የቢሮው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን በክልሉ ያለው የጸጥታ እና ድርቅ ችግሮች በተማሪዎች ምዝገባ ሥራ ላይ ከፍተኛ ጫና አሳድሯል ብለዋል። ክልሉ 6 ነጥብ 2 ሚሊዮን ተማሪዎችን መዝግቦ ማስተማር ሲገባው ያን ማድረግ አለመቻሉን ኃላፊው ተናግረዋል። ከሁለት ነጥብ 6 ሚሊዮን ያልተመዘገቡ ተማሪዎች መኖራቸውን የገለፁት ኃላፊው ፤ መማር የሚገባቸው ተማሪዎች የትምህርት ዕድል እንዳያገኙ መደረጉን አመልክተዋል። ከ2015 ዓ/ም ሚያዚያ ወር ጀምሮ የፌደራል መንግስት የክልል ልዩ ሀይሎችን መልሼ አደራጃለሁ የሚል ውሳኔ ካሳለፈበት ጊዜ ጀምሮ በአማራ ክልል በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና ፋኖ ታጣቂዎች መካከል…
Read More