ስፖርት

አዲስ አበባ ዓለም-አቀፍ የቦክስ ውድድር ልታስተናግድ ነው

አዲስ አበባ ዓለም-አቀፍ የቦክስ ውድድር ልታስተናግድ ነው

የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌደሬሽን ዋና ቢሮውን በአዲስ አበባ የከፈተ ሲሆን፣ ቅዳሜ ነሐሴ 11 ቀን 2016 ዓ.ም በደማቅ ዝግጅት በይፋ ያስመርቃል፡፡ ፌዴሬሽኑ የቢሮውን መክፈት አስመልክቶ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ አለም አቀፍ የቦክስ ውድድር እንደሚዘጋክ ተገልጿል፡፡ ይህ አለም አቀፍ የቦክስ ውድድርን የአለም አቀፉ የቦክስ ማህበር ከአፍሪካ የቦክስ ኮንፌደሬሽን እንዲሁም ከኢትዮጵያ የቦክስ ፌደሬሽን ጋር በመተበበር በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ይዘጋጃል ተብሏል፡፡ 20 ዓለም አቀፍ ፕሮፌሽናል ቦክሰኞች ከሩሲያ፣ ሜክሲኮ፣ እንግሊዝ፣ ካዛኪስታን፣ ሞሮኮ፣ ናይጄሪያ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ ተገልጿል፡፡ ይህ ልዩ የቦክስ ውድድር ላይ የተሳተፉ ቦክሰኞች በአፍሪካ ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል የተባለ ሲሆን ውድድሩ በ10 ዘርች ይካሄዳል ተብሏል፡፡ ይህ አለም-አቀፍ የቦክስ ውድድርን ለመዘገብ…
Read More
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ የአፍሪካ ስፖርተኛ ተብሎ ተመረጠ

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ የአፍሪካ ስፖርተኛ ተብሎ ተመረጠ

የአሜሪካው አለምአቀፍ የስፓርት ቻናል (ኢኤስፒኤን) ቀነኒሳ በቀለን የ21ኛው ክፍለዘመን ምርጥ አትሌት ነው ሲል መርጦታል፡፡ የስፖርት ቻናሉ ከቀነኒሳ በቀለ በተጨማሪ ሌላኛዋ ኢትዮጵያት አትሌት ጥሩነሽ ዲባባን ጨምሮ በ21ኛው ክፍለዘመን ምርጥ ያላቸውን የአፍሪካ ስፓርተኞች ይፋ አድርጓል። ኢኤስፒኤን አህጉሪቱ ካላት ስፋት እና የስፖርት ብዛት አንጻር 25 ምርጥ አትሌቶችን መምረጥ ከባድ መሆኑን አስታውቋል። ዓለም ካየቻቸው ምርጥ የማራቶን ሯጭ አንዱ ከሆነው ኢሉድ ኪፕቾጌ እና ኦሎምፒክ እና በርካታ የአውሮፓ ሻሜፒዮን ሽፕ አሸናፊ ከሆነው ሳሙኤል ኢቶ ማንን ትመርጣላችሁ? ሲልም ኢኤስፒኤን ይጠይቃል። አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በቻናሉ ዘገባ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ የአፍሪካ ስፖርተኛ ተብሎ ስሙ በመካተቱ እንደተደሰተ በማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ላይ ጽፏል። አትሌት ቀነኒሳ በ2000ዎቹ በ10ሺ እና በ5ሺ ሜትር…
Read More
የቀድሞው ማንችስተር ዩናይትድ ኮኮብ ልዊስ ናኒ ኢትዮጵያን ሊጎበኝ ነው

የቀድሞው ማንችስተር ዩናይትድ ኮኮብ ልዊስ ናኒ ኢትዮጵያን ሊጎበኝ ነው

ፖርቹጋላዊው እግር ኳስ ተጫዋች ልዊስ ናኒ ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ መሆኑ ገልጿል፡፡ ፖርቹጋላዊው የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች ተጨዋች ሉዊስ ናኒ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ላይ ባሰራጨው ቪዲዮ አስታውቋል፡፡ ናኒ ወደ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ የሚመጣው የሰማንያኛ አመት ክብረ በዓሉን በማክበር ላይ ለሚገኘው መቻል እግርኳስ ክለብ የክብር እንግዳ ሆኖ እንደሚሆን ተገልጿል። ናኒ ባስተላለፈው አጭር የቪዲዮ መልዕክትም " ሰላም ኢትዮጵያውያን ሰማንያኛ አመቱን ከሚያከብረው መቻል ግብዣ ስለቀረበልኝ ኩራት እና ደስታ ተሰምቶኛል። ለእኔ ልዩ ቦታ ያላትን ኢትዮጵያ ለመጎብኘት ጓጉቻለሁ በቅርቡ እንገናኝ" ሲል ተደምጧል። መቻል እግር ኳስ ክለብ በሀገር መከላከያ ሰራዊት ስር የተቋቋመ ቡድን ሲሆን በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እየተወዳደረ ይገኛል፡፡ ክለቡ…
Read More
ኢትዮጵያ በመላው አፍሪካ አትሌቲክስ ውድድር አራተኛ ሆና አጠናቀቀች

ኢትዮጵያ በመላው አፍሪካ አትሌቲክስ ውድድር አራተኛ ሆና አጠናቀቀች

በካሜሩን አስተናጋጅነት የተካሄደው የመላው አፍሪካ አትሌቲክስ ውድድር ተጠናቋል፡፡ በካሜሩን ዋና ከተማ ዱዋላ አስተናጋጅነት ከ27 ሃገራት በላይ የተውጣጡ 2500 አትሌቶች ላለፉበት 6 ቀናት ሲሳተፉበት የነበረው 23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ተጠናቋል። በዚህ ውድድር ለይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አራተኛ ሆኖ አጠናቋል፡፡ ኢትዮጵያ በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና 5 ወርቅ፣ 4 የብር እና አንድ የነሐስ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን አግኝቷል፡፡ ኢትዮጵያጵያ በውድድሩ ላይ 68 አትሌቶችን በ19 የአትሌቲክስ የውድድር አይነቶች ላይ የተሳተፈች ሲሆን ከናይጀሪያ በመቀጠል አራተኛ ሆና አጠናቃለች፡፡ የወርቅ ሜዳልያ ለኢትዮጵያ ያስገኙ አትሌቶች ፋንታዬ በላይነህ በ5ሺ ሜትር ሴቶች ፣ንብረት መላክ በ10ሺ ሜትር ወንዶች ፣ምስጋና ዋቁማ በወንዶች በ20 ኪሎ ሜትር እርምጃ፣    ስንታየሁ ማስሬ በሴቶች በ20 ኪሎ ሜትር…
Read More
ኢትዮጵያ በፓሪስ ኦሎምፒክ የሚወክሏትን አትሌቶች መረጠች

ኢትዮጵያ በፓሪስ ኦሎምፒክ የሚወክሏትን አትሌቶች መረጠች

በየአራት ዓመቱ አንዴ የሚካሄደው የመላው ስፖርታዊ ውድድር ወይም ኦሊምፒክ የዘንድሮው ውድድር በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ ይካሄዳል። ውድድሩ ከሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን ኢትዮጵያ በውድድሩ ከሚሳተፉ ሀገራት መካከል ናት። በአትሌቲክስ ዘርፍ ኢትዮጵያን በውድድሩ ላይ የሚወክሉ አትሌቶች ምርጫ በስፔን ኔርሀ ትናንት ምሽት ተደርጓል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንዳስታወቀው በ10 ሺህ ሜትር ሁለቱም ጾታ፣ በ1 ሺህ 500 ሜትር ወንዶች እንዲሁም በ800 ሜትር ወንዶች የማጣሪያ ውድድሮች ተካሂደዋል። ኢትዮጵያ ለፓሪስ ኦሎምፒክ በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች ውድድር ለመሳተፍ የማጣሪያውን ውድድርን በትንሹ በ27 ደቂቃ ማጠናቀቅን እንደ መስፈርት አስቀምጣለች። በዚህም መሰረት በማጣሪያው ውድድር ከተሳተፉ 16 አትሌቶች ተሳትፈው ዮሚፍ ቀጄልቻ በ26፡31.01 1ኛ በሪሁ አረጋዊ 26፡31.13 2ኛ ፣ሰለሞን…
Read More
ኢትዮጵያ ከ6 ሺህ በላይ የስፖርት ውርርድ ቤቶችን ዘጋች

ኢትዮጵያ ከ6 ሺህ በላይ የስፖርት ውርርድ ቤቶችን ዘጋች

በአዲስ አበባ ባለፉት 9 ወራት ውስጥ ከ6 ሺህ በላይ የስፖርታዊ ውርርድ ቤቶች መታሸጋቸው ተገልጿል፡፡ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ባለፉት 9 ወራት የህብረተሰቡን ሰላም አውከዋል ባላቸው የተለያዩ ስራዎች ላይ እርምጃ ወስጃለሁ ብሏል፡፡ የቢሮው ሀላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ የውርርድ ቤቶችን ጨምሮ ጫት ማስቃም፣ ሽሻ ማስጨስና የመሳሰሉ ጉዳዮች ይፈፀሙባቸው የነበሩና የወንጀል ድርጊት የሚታይባቸው ተግባራት ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል፡፡ እነዚህ ድርጊቶች ትምህርት ቤቶች አካባቢ የመማር ማስተማር ሂደትን እያስተጓጉሉ የነበሩ ናቸውም ተብሏል። የከተማዋ አስተዳድር ከዘጋቸው ተቋማት መካከል 6 ሺህ 726 የሚሆኑ የስፖርታዊ ውርርድ  ቤቶች መታሸጋቸውን አስታውቋል፡፡ በዚህ ዘርፍ ተሰማርተው የነበሩ የንግድ ድርጅቶች ወደ ሌላ የስራ ዘርፍ እንዲቀይሩ እየተደረገ መሆኑን ሃላፊዋ አክለው ተናግረዋል፡፡ ፍርድ…
Read More
ኢትዮጵያ የ2029 የአፍሪካ ዋንጫን የማዘጋጀት እቅድ እንዳላት ገለጸች

ኢትዮጵያ የ2029 የአፍሪካ ዋንጫን የማዘጋጀት እቅድ እንዳላት ገለጸች

ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አመታት የአፍሪካ ዋንጫ ውድድርን እንድታዘጋጅ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ ተናግረዋል። የአፍሪካ ዋንጫን እ.ኤ.አ በ2029 ወይም በ2031 ለማዘጋጀት እየሰራን ነው ያሉት ሚኒስትሩ ለእቅዱ መሳካትም ቢያንስ ስድስት ደረጃቸውን የጠበቁ ስታዲየሞች አስፈላጊ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ካፍ ከዚህ በፊት ያልነበሩ አዳዲስ መስፈርቶችን በማስቀመጡ ኢትዮጵያ አንድም ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም እንዳይኖራት አድርጓል ሲሉም አቶ ቀጀላ መርዳሳ አስረድተዋል። ኢትዮጵያ የካፍን ደረጃ የሚመጥኑ ስታዲየሞች የሌላት በመሆኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ረዘም ላሉ ጊዜያት ከሀገሩ ዉጪ ለመጫወት ተገድዶ የነበረ መሆኑ ይታወቃል። የዉድድሩ አዘጋጅ ሀገራት ቢያንስ ስድስት ስታዲየሞችን እንዲያዘጋጁ ካፍ ቢያዝም ኢትዮጵያ እስካሁን የካፍን ደረጃ ያሟላ ስታዲየም የሌላት ሲሆን ውድድሩን ለማዘጋጀት እያደረገች ስላለው ዝግጅት የተባለ…
Read More
ኢትዮጵያ በግላስኮው የዓለም ቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድርን በአምስተኛነት አጠናቀቀች

ኢትዮጵያ በግላስኮው የዓለም ቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድርን በአምስተኛነት አጠናቀቀች

በስኮትላንድ ግላስጎ ሲካሄድ የቆየው የ2024 የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ፍጻሜውን አግኝቷል። ከየካቲት 22 እስክ 24 2016 ዓ.ም ሲካሄድ በነበረው የ19ኛው የዓለም የቤት ዉስጥ ሻምፒዮና ከ130 በላይ ሀገራት  የተውጣጡ ከ650 በላይ አትሌቶቸ  መሳተፋቸው ተነግሯል። ኢትዮጵያ በ800 ሜትር፣ በ1500 ሜትር እና በ3000 ሜትር  በሴትና በወንድ  በአጠቃላይ  በ8 ሴቶች እና በ5 ወንዶች በድምሩ በ13 አትሌቶች መሳተፏን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በሻምፒዮናው በሴቶች 800 ሜትር ፅጌ ዱጉማ እና በሴቶች 1500 ሜትር ፍሬወይኒ ሀይሉ የወርቅ፣ በሴቶች 3000 ሜትር ጉዳፍ ፀጋዬ የብር እንዲሁም በወንዶች 3000 ሜትር ሰለሞን ባረጋ የነሃስ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ያስገኙ አትሌቶች ሆነዋል። በዚህ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ  ሁለት ወርቅ አንድ ነሀስ በአንድ ብር…
Read More
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከ4 ዓመታት በኋላ ወደ አዲስ አበባ ሊመለስ ነው

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከ4 ዓመታት በኋላ ወደ አዲስ አበባ ሊመለስ ነው

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2016 እግር ኳስ ውድድር የጨዋታ ፕሮግራም ባሳለፍነው ነሀሴ ከወጣ በኋላ መስከረም 20 ቀን 2016 ዓም መጀመሩ ይታወሳል፡፡ የፕሪሚየር ሊጉ የመክፈቻ ጨዋታን ባለሜዳው አዳማ ከነማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መካከል ተደርጎም ነበር፡፡ የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች ላለፉት አራት ዓመታት በአዳማ፣ ድሬዳዋ፣ሐዋሳ እና ባህርዳር ስታዲየሞች ሲካሄዱ ቆይተዋል፡፡ የአዲስ አበባ ስታዲየም በእድሳት ምክንያት የፕሪሚየር ሊግ እና የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎችን ወደ ክልል ከተሞች እንዲዞሩ የግድ ሆኖ ቆይቶም ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ እንደገለጸው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጨረሻዎቹ ሶስት ሳምንታት በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚደረግ ገልጿል። የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ዙር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር መርሃ ግብርና የውድድር ሜዳዎች ይፋ ተደርገዋል። በዚህም በስታዲየሞች…
Read More
የ2023 አፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ በኮቲዲቯር አሸናፊነት ተጠናቀቀ

የ2023 አፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ በኮቲዲቯር አሸናፊነት ተጠናቀቀ

37ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር በውድድሩ አዘጋጅ ሀገር ኮቲዲቯር አሸናፊነት ተጠናቋል። ጥር 3 ቀን ተጀምሮ የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ፍጻሜውን ያገኘው ይህ ውድድር ናይጀሪያ እና ኮቲዲቯር ለዋንጫ ተጫውተዋል። ናይጀሪያ በመጀመሪያው አጋማሽ በአምበሏ ኢኮንግ ጎል ቀድማ ጎል ያስቆጠረች ቢሆንም ኬሲ እና ሀለር ኮቲዲቯርን የዋንጫ ባለቤት ያደረጉ ጎሎችን አስቆጥረዋል። ይህን ውድድር ደቡብ አፍሪካ ሶስተኛ እንዲሁም ዲሞክራቲክ ኮንጎ አራተኛ ሆነው አጠናቀዋል። በዚህ ውድድር ላይ የኮቲዲቯር አሰልጣኝ ኤምሬ ፋኤ ኮከብ አሰልጣኝ፣ ሲሞን አዲንጋራ ምርጥ ኮከብ ወጣት ተጫዋች ናይጀሪያዊው ዊሊያም ኢኮንግ የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች፣ የ34 ዓመቱ የኢኳቶሪያል ጊኒው ኤምሊያኖ ኑስ በአምስት ጎሎች ኮከብ ግብ አግቢ እንዲሁም ሮንውን ዊሊያምስ ኮከብ ግብ ጠባቂ በመሆን ተመርጠዋል።…
Read More