africaboxconfederation

አዲስ አበባ ዓለም-አቀፍ የቦክስ ውድድር ልታስተናግድ ነው

አዲስ አበባ ዓለም-አቀፍ የቦክስ ውድድር ልታስተናግድ ነው

የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌደሬሽን ዋና ቢሮውን በአዲስ አበባ የከፈተ ሲሆን፣ ቅዳሜ ነሐሴ 11 ቀን 2016 ዓ.ም በደማቅ ዝግጅት በይፋ ያስመርቃል፡፡ ፌዴሬሽኑ የቢሮውን መክፈት አስመልክቶ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ አለም አቀፍ የቦክስ ውድድር እንደሚዘጋክ ተገልጿል፡፡ ይህ አለም አቀፍ የቦክስ ውድድርን የአለም አቀፉ የቦክስ ማህበር ከአፍሪካ የቦክስ ኮንፌደሬሽን እንዲሁም ከኢትዮጵያ የቦክስ ፌደሬሽን ጋር በመተበበር በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ይዘጋጃል ተብሏል፡፡ 20 ዓለም አቀፍ ፕሮፌሽናል ቦክሰኞች ከሩሲያ፣ ሜክሲኮ፣ እንግሊዝ፣ ካዛኪስታን፣ ሞሮኮ፣ ናይጄሪያ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ ተገልጿል፡፡ ይህ ልዩ የቦክስ ውድድር ላይ የተሳተፉ ቦክሰኞች በአፍሪካ ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል የተባለ ሲሆን ውድድሩ በ10 ዘርች ይካሄዳል ተብሏል፡፡ ይህ አለም-አቀፍ የቦክስ ውድድርን ለመዘገብ…
Read More