ኪነ ጥበብ

ኢትዮጵያ በቴሌግራም መተግበሪያ ላይ ዳግም እገዳ ጣለች

ኢትዮጵያ በቴሌግራም መተግበሪያ ላይ ዳግም እገዳ ጣለች

በኢትዮጵያ የቴሌግራም መተግበሪያ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ከዛሬ ረቡዕ ሐምሌ 19 ቀን 2015ዓ.ም ጠዋት ጀምሮ እየሰራ አይደለም። ገደቡ የተጣለዉ ዛሬ ከሚጀመረዉ የ 2015 ዓ.ም የ 12ኛ ክፍል ፈተና ጋር በተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። ይሁንና መንግሥት ለምን በቴሌግራም ላይ እገዳ እንደጣለ እስካሁን መረጃ ያልሰጠ ሲሆን መተግበሪያው በቪፒኤን እየሰራ ይገኛል። ከወራት በፊት በኦሮሚያ ክልል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አጋጥሟት የነበረዉን የመከፋፈል ድርጊትና የጳጳሳት ሹመነትን በሚመለከት በተለያዩ አካባቢዎች የተነሳዉን ተቋዉሞ ተከትሎ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እግዱ ተጥሎ ለአምስት ወራት መቆየቱ ይታወሳል። በዚህም መሰረት እንደ ፌስቡክ ፣ ቲክቶክ ፣ ቴሌግራም ፣ ኢንስታግራም ፣ ዩቲዩብ እና ሌሎች የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን ሰዎች VPN ( virtual private network )…
Read More
አርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት እንዲሰጣት ተወሰነ

አርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት እንዲሰጣት ተወሰነ

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ሊሰጣት መወሰኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር) አስታውቀዋል። ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ሐምሌ 13/2015 እንደሚያስመርቅ የገለጹት ፕሬዘዳንቱ፤ በዕለቱ ለተወዳጇ አርቲስት እጅጋየው ሽባባው(ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። ድምፃዊት፣ ገጣሚ፣ የዜማ ደራሲ እና ተዋናይት የሆነችው ሁለገቧ አርቲስት ጂጂ፣ የአገሯን ባህልና ሙዚቃ ለዓለም በማስተዋወቅ እንዲሁም በኪነጥበብ የአዊን ህዝብ ቋንቋ እና ባህል በማሳደግ ላበረከተችው አስተዋፅኦ የክብር ዶክትሬቱ እንደሚበረከትላት ነው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት መግለጻቸውን ከዩንቨርስቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ለጂጂ የሚሰጠውን የክብር ዶክትሬት እና የተማሪዎቹን የምርቃት ሥነስርዓት በማስመልከት ረቡዕ ማለትም ሐምሌ 12/2015 ከቀኑ 8:00 ሰዓት ለመገናኛ ብዙሀን ዝርዝር መግለጫ እንደሚሰጥም ፕሬዘዳንቱ ገልጸዋል። ከሰሞኑ ለ15ተኛ ጊዜ በተካሄደዉ የአማራ…
Read More
አዲስ አበባ የሩሲያዊ ደራሲ አሌክሳንደር ፑሽኪንን ሐውልት ዳግም ወደ አደባባይ ልትመልስ መሆኗን ገለጸች

አዲስ አበባ የሩሲያዊ ደራሲ አሌክሳንደር ፑሽኪንን ሐውልት ዳግም ወደ አደባባይ ልትመልስ መሆኗን ገለጸች

ኢትዮጵያ የታዋቂውን ሩሲያዊ ደራሲ ፑሽኪን ሐውልትን ወደ አደባባይ ልትመልስ መሆኗን ገለጸች የሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ በፈረንጆቹ 2002 ላይ ነበር የታዋቂውን የሩሲያዊ የስነ ጽሁፍ ሰው አሌክሳንደር ፑሽኪንን ሀውልት በስጦታ መልኩ ለአዲስ አበባ የሰጠችው። ይህ ሀውልት ለረጅም ዓመታት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ስር ባለ አንድ አደባባይን የፑሽኪን አደባባይ በሚል የሰየመችው። በዚህ አደባባይ ላይም የፑሽኪን ሐውልት ተተክሎ የቆየ ቢሆንም የትራፊክ መጨናነቅን ለማስቀረት በሚል አደባባዩ ፈርሷል። የአሌክሳንደር ፑሽኪን ሀውልትም ወደ ኢትዮጵያ ሙዚየም ግቢ ውስጥ እንዲቀመጥ ተደርጎ ቆይቷል። የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ እያሱ ሰለሞን ለአልዐይን እንዳሉት የፑሽኪን ሀውልት ወደ አደባባይ ወጥቶ ይተከላል ብለዋል። "ሀውልቱ የሩሲያን እና ኢትዮጵያን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ክብር…
Read More
ታላቅ የስኮላርሺፕ ዕድል ለወጣት የፊልም ባለሞያዎች!!

ታላቅ የስኮላርሺፕ ዕድል ለወጣት የፊልም ባለሞያዎች!!

የአፍሪካ ግዙፉ የመዝናኛና ስፖርት ይዘቶች አቅራቢው መልቲቾይስ አፍሪካ- ዲኤስቲቪ በየዓመቱ ለወጣት የፊልም ባለሙያዎች የ 1 ዓመት የፊልም ጥበብ ስኮላርሺፕ ይሰጣል፡፡ 👉 የስኮላርሺፕ ቆይታቸውን በከፍተኛ ውጤት ለሚያጠናቅቁ ተመራቂዎች ደግሞ በኒውዮርክ፣ በሕንድ እና በደቡብ አፍሪካ የፊልም አካዳሚዎችና የፊልም ኢንዱስትሪ መንደሮች ተጨማሪ ስልጠና የሚያገኙ ይሆናል፡፡ 👉 በመሆኑም ይህንን ታላቅ የመልቲቾይስ ታለንት ፋክተሪ የ2024 እ.ኤ.አ ስኮላርሺፕ ዕድል በማግኘት ኬንያ በሚገኘው የመልቲቾይስ አካዳሚ የፊልም ጥበብ ዕውቀታችሁን ማጎልበት የምትፈልጉ ዕድሜያችሁ ከ18-26 ዓመት የሆናችሁ ወጣት የፊልም ባለሙያዎች እስከ ሐምሌ 7 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ www.multichoicetalentfactory.com ላይ እንድታመለክቱ ተጋብዛችኋል፡፡ ማሳሰቢያአመልካቾች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታና ጊዜው ያላለፈበት ፓስፖርት ሊኖራችሁ ይገባል!! Miss it not!! 💥 A great opportunity to connect with…
Read More
ኢትዮጵያን የጉዛራ ቤተ መንግሥት በ35 ነጥብ ስምንት ሚሊየን ብር ጥገና ሊደረግለት ነው

ኢትዮጵያን የጉዛራ ቤተ መንግሥት በ35 ነጥብ ስምንት ሚሊየን ብር ጥገና ሊደረግለት ነው

በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሚገኘው የጉዛራ ቤተመንግሥት ከተደቀነበት የመፍረስ አደጋ ለመታደግ፤ ከፌደራል መንግሥት በተበጀተ 35 ሚሊዮን 800 ሺሕ ብር በጀት የጥገና ሥራው በዛሬው ዕለት እንደሚጀመር ተገልጿል። የጥገና ሥራው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት የቅርስ ጥበቃና ቱሪዝም ልማት ቡድን መሪ ግርማቸው ሙሉጌታ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። ጉዛራ ቤተመንግሥት በጣና ተፋሰስ አካባቢዎች የሚገኝ የመጀመሪያው ቤተመንግሥት እንደሆነ ይነገራል። ጉዛራ ቃሉ የግዕዝ ሲሆን፤ ትርጉሙም ምቹ ማለት ነው። በጎንደር የነገሥታት ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን የጉዛራን ቤተመንግሥት የመሰረቱትም ያሳነፁትም ኢትዮጵያን ከ1556-1589 ድረስ በመሩት በአፄ ሰርፀ ድንግል መሆናቸው በፁሁፍ የሰፈሩ ማስረጃዎች ያሳያሉ። የጉዛራ ቤተመንግሥት ከእንፍራንዝ በስተደቡብ 5 ኪሎሜትር ወጣ ብሎ የተሰራ…
Read More
ሩሲያ እና ቻይና አማርኛ ቋንቋን ለዜጎቻቸው ለማስተማር ወሰኑ

ሩሲያ እና ቻይና አማርኛ ቋንቋን ለዜጎቻቸው ለማስተማር ወሰኑ

ሩሲያ እና ቻይና አማርኛ ቋንቋን ለዜጎቻቸው ለማስተማር ወሰኑ የዓለማችን ባለ ግዙፍ ኢኮኖሚ እና ብዙ ህዝብ ያላቸው ሩሲያ እና ቻይና የኢትዮጵያ የስራ ቋንቋ የሆነው አማርኛ ቋንቋ ለዜጎቻቸው እንዲሰጥ መወሰናቸውን አስታውቀዋል፡፡ ሩሲያ ከቀጣዩ መስከረም ወር ጀምሮ በሞስኮ በሚገኙ አራት ትምህርት ቤቶች ውስጥ እንደሚሰጥ ገልጻለች፡፡ ትምህርቱ ከቀጣዩ መስከረም 2016 ዓ.ም ጀምሮ ይሰጣል የተባለ ሲሆን በሳምንት ሁለት ክፍለ ጊዜ እንደሚሰጥ በሞስኮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የእስያ እና አፍሪካ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አሌክሲ ማስሎቭ ገልጸዋል፡፡ ሌላኛዋ አማርኛ ቋንቋን ለዜጎቿ ለማስተማር የወሰነችው ሀገር ቻይና ስትሆን ትምህርቱ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) ከሚሰጡ 101 የውጭ ቋንቋ ትምህርቶች አንዱ ይሆናል ተብሏል፡፡ ለዚህ እንዲረዳም አማርኛን ለቻይናዊያን ተማሪዎች ለማስተማር የሚያግዘው መጽሀፍ በቤጂንግ…
Read More
የአዲስ አበባ የ70 ዓመት ባለውለታ አረፉ

የአዲስ አበባ የ70 ዓመት ባለውለታ አረፉ

በአዲስ አበባ ከተማ ላለፉት 70 ዓመት ዳቦ በማቅረብ የሚታወቁት የ'ሸዋ ዳቦ' መሥራቹ ዘሙይ ተክሉ ማረፋቸው ተሰምቷል። የአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ሥያሜውን የተዋሱት የሸዋ ዳቦ መሥራቹ አቶ ዘሙይ ተክሉ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ታውቋል። የኤርትራ መሠረት ያላቸው ዘሙይ ወደ አዲስ አበባ ዘልቀው ያቋቋሙት ሸዋ ዳቦ ለ70 ዓመታት ለአዲስ አበቤዎች ዳቦ ሲያቀርብ ቆይቷል። የአምስት ልጆች አባት የሆኑት አቶ ዘሙይ አንደኛዋ ልጃቸው በአዲስ አበባ ሥማቸው ከሚጠራ ኬክ ቤቶች መካከል የሆነው የ'ቤሎስ ኬክ' ቤት መስራች ሆናለች። በደርግ አስተዳድር ዘመን ለኤርትራ መገንጠል የሚዋጉ አማጽያንን በመደገፍ ታስረው የነበሩት ዘሙይ ተክሉ፣ በከተማዋ የሌላኛው ሥመ ጥር ኬክ ቤት መሥራች የበላይ ተክሉ ወንድምም ናቸው። ሸዋ ዳቦ ቤት በስንዴ መወደድ…
Read More