Railwaytransport

ኢትዮጵያ ከሁሉም ጎረቤት ሀገራት ጋር የባቡር ትራንስፖርት የመገንባት እቅድ እንዳላት ገለጸች

ኢትዮጵያ ከሁሉም ጎረቤት ሀገራት ጋር የባቡር ትራንስፖርት የመገንባት እቅድ እንዳላት ገለጸች

የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠናን ታሳቢ ያደረገ የባቡር መስመር ትስስር ወደ ሁሉም የጎረቤት ሀገራት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል። የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠናን ታሳቢ ያደረገ እና ኢትዮጵያን ከሁሉም የጎረቤት ሀገራት ጋር የሚያስተሳስር የባቡር መስመር እየተሰራ እንደሚገኝ የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል። የባቡር ትራንስፖርት ኢንቨስትመንት ከፍተኛ በመሆኑ ረዥም ርቀትን፣ መሰረተ ልማትን እንዲሁም ንግድና ቀጠናዊ ትስስርን ታሳቢ አድርጎ እንደሚሰራ የገለፁት የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ናቸው። በመሆኑም የባቡር መስመር ዝርጋታ በሀገር ውስጥ የሚቆም ሳይሆን፤ በሁሉም አቅጣጫ ከሚገኙ ጎረቤት ሀገራትና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር በጋራ ለመነገድና ለመስራት የሚያስችል እንደሆነ ተናግረዋል። ከጎረቤት ሀገራት ባሻገር ደግሞ የአፍሪካን አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ከማስፋፋት አንፃር ታሳቢ ያደረገ…
Read More
ጣልያን በኢትዮጵያ የባቡር መስመር ግንባታ ለማድረግ ተስማማች

ጣልያን በኢትዮጵያ የባቡር መስመር ግንባታ ለማድረግ ተስማማች

የጣልያን ባቡር ኮርፖሬሽን ከኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል። መንግሥት በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት የተቋረጠውን የአዋሽ- ኮምቦልቻ እና ሐራ ገበያ የባቡር መስመርን ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ቁርጠኝነት አለኝ ብሏል። የአዋሽ- ኮምቦልቻ እና ሐራ ገበያ  የባቡር መስመርን ለማጠናቀቅ ከፍተኛ የመንግስት ቁርጠኝነት ምኖሩን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታወቀ። የኮርፖሬሽኑ የህግ አገልግሎት ሃላፊ አቶ ካሳሁን ሙላቱ እንደገልፁት ኮርፖሬሽኑ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎትን ለማጠናከር ከኮይፓ ኢጣሊያ ጋር ስምምነት አድርጓል። ስምምነቱ አዳዲስ የባቡር መስመሮችን መዘርጋትን እንዲሁም እየተገነቡ ያሉ የባቡር መስመሮችን በፍጥነት አጠናቆ ወደ ስራ ማስገባትን የሚያካትት ነው ብለዋል። ከዛም ባለፈ በጋራ ድርጅቶችን ማቋቋም እንዲሁም ትላልቅ ዎርክ ሾፖሽን ማሻሻል ጨምሮ በርካታ ስትራቴጂካዊ ስራዎች የሚሰራበት የጋራ ስምምነት መሆኑን…
Read More
ኢትዮጵያ በቱርኩ ያፒ መርከዚ የባቡር ግንባታ ኩባንያ ላይ ክስ መሰረተች

ኢትዮጵያ በቱርኩ ያፒ መርከዚ የባቡር ግንባታ ኩባንያ ላይ ክስ መሰረተች

የቱርኩ ያፒ መርከዚ ኩባንያ በኢትዮጵያ የጀመረውን የባቡር መስመር ግንባታ ሳያጠናቅቅ ከሀገር ወጥቷል ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ የቱርኩ ተቋራጭ ያፒ መርከዚ ኩባንያ የአዋሽ-ወልድያ-መቀሌ የባቡር ሐዲድ ግንባታን ሳያጠናቅቅ በመውጣቱ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፍለው ክስ መመስረቱ ተገልጿል፡፡ ያፒ መርከዚ የተሰኘው የቱርክ ስራ ተቋራጭ ኩባንያ በ2007 ዓ.ም 392 ኪሎ ሜትር የሚረዝም የባቡር መስመር ግንባታ በማካሄድ ላይ ነበር፡፡ ይህ የባቡር መስመር የመካከለኛ እና ሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች ከጅቡቲ ወደብ ጋር የተሳለጠ የትራንስፖርት እንቅስቀሴ እንዲኖራቸው ታስቦ በመገንባት ላይ ነበር፡፡ ከቱርኩ ኤግዚም ባንክ በተገኘ 1 ነትብ 9 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ግንባታው እየተካሄደ የነበረው ይህ የባቡር መስመር ሊጠናቀቅ ጥቂት መሰረተ ልማቶች ሲቀሩት በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት…
Read More
ከኬንያ ላሙ ወደብ ሞያሌ- አዲስ አበባ የባቡር መስመር ሊገነባ እንደሆነ ተገለጸ

ከኬንያ ላሙ ወደብ ሞያሌ- አዲስ አበባ የባቡር መስመር ሊገነባ እንደሆነ ተገለጸ

ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኛትን የባቡር መስመር በ14 ቢሊዮን ዶላር ልትዘረጋ መሆኑን አስታውቃለች፡፡ ኬንያ የምትዘረጋው ይህ ፈጣን የባቡር መስመር በኤሌክትሪክ የሚሰራ ሲሆን፤ መነሻውን ከህንድ ውቅያኖስ ላሙ ወደብ በማድረግ ኢትዮጵያን እና ደቡብ ሱዳንን እንደሚያገናኝ ብሉምበርግ ዘግቧል። በዓይነቱ ልዩ ነው የተባለው ይህ የባቡር መስመር በፈረንጆቹ 2025 ሥራ እንደሚጀመር እና 3 ሺሕ ከሎ ሜትር እንደሚረዝም ታውቋል፡፡ የባቡር መስመሩ መነሻውን ከህንድ ውቅያኖስ አድርጎ፣ በኬንያዋ ማዕከላዊ ከተማ ኦሲዮሎን በኩል፣ ናይሮቢን እና አዲስ አበባን በማገናኘት የመጨረሻም መዳረሻውን ደቡብ ሱዳን ጁባ እንደሚያደርግ ተነግሯል፡፡ ይህ ፈጣን የባቡር መስመር “ኢትዮጵያ በአሰብ እና ምጽዋ እንዲሁም ጅቡቲ ወደቦች ላይ ያላትን ጥገኝነት የሚቀንስ ነው” የተባለ ሲሆን፤ ሌሎች በርካታ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች…
Read More