NBE

አንድ የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ወደ 156 ብር ከፍ ማለቱ ተገለጸ

አንድ የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ወደ 156 ብር ከፍ ማለቱ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባከናወነው 20ኛው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ፣ አንድ የአሜሪካ ዶላርን አማካይ በ155 ነጥብ 4 ብር መድረሱን ይፋ አድርጓል። ብሔራዊ ባንክ ለገበያ ያቀረበው የውጭ ምንዛሬ መጠን 70 ሚሊዮን ዶላር ቢሆንም፣ ከንግድ ባንኮች በኩል የቀረበው የፍላጎት መጠን ግን 177 ነጥብ 12 ሚሊዮን ዶላር ሆኖ ሆኗል። ይህም አቅርቦቱ ከፍላጎቱ ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ልዩነት እንዳለው ያሳያል። ከፍተኛው የማሸነፊያ ዋጋ 156 ነጥብ 05 ብር ሲሆን ዝቅተኛው የጨረታ ዋጋ ደግሞ 153 ነጥብ 8805 ብር ሆኗል። ባንኩ በዚህ ጨረታ አንድ ዶላርን 155 ነጥብ 88 ብር መሸጡን አስታውቋል። በዚሁ ጨረታ ላይ በአጠቃላይ 20 የንግድ ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን፣ ካቀረቡት የዋጋ ተወዳዳሪነት አንጻር 9 ባንኮች ብቻ የቀረበውን የውጭ…
Read More
በኢትዮጵያ ዓመታዊ የድጅታል ገንዘብ ልውውጥ ከ18 ትሪሊዮን ብር በላይ ደረሰ

በኢትዮጵያ ዓመታዊ የድጅታል ገንዘብ ልውውጥ ከ18 ትሪሊዮን ብር በላይ ደረሰ

ብሔራዊ ባንክ እንዳስታወቀው በአንድ አመት ውስጥ በጂታል ክፍያ ስርአት 18 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር ዝውውር ተፈጽሟል። በኢትዮጵያ ዲጂታል ክፍያ ኮንፈረንስ 2.0. ላይ ለአምስት አመት የሚቆይ (2026-30) የብሔራዊ የዲጂታል ክፍያ ስትራቴጂ በብሔራዊ ባንክ ይፋ ሆኗል። የመጀመሪያው የ2021-24 ብሄራዊ የዲጂታል ክፍያ ስትራቴጂ ላይ ህግ ማውጣት፣ተቋማት አገልግሎቱን እንዲሰጡ ማስቻልና ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ እንዲሁም መሠረተ ልማት ዝርጋታ መከናወናቸው ተጠቁሟል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የክፍያ ስርአት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ዳምጠው ለቅዳሜ ገበያ እንደገለጹት በኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ ትልቁ ሚና የገንዘብ ዝውውር ፈጣን ቀልጣፋ ወጪ ቆጣቢ መሆን አለበት። ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የዲጂታል የክፍያ ስርአትን ማዘመን እና ለዚያ የሚያበቃ የድጅታል መሰረተ ልማት ግንባታ ጉልህ ሚና ይጫወታል። ባለፈው አንድ አመት…
Read More
ብሔራዊ ባንክ የባንክ አካውንት ከብሔራዊ መታወቂያ ጋር እንዲያስተሳስሩ አሳሰበ

ብሔራዊ ባንክ የባንክ አካውንት ከብሔራዊ መታወቂያ ጋር እንዲያስተሳስሩ አሳሰበ

ባንኮች የከፈቷቸውን አካውንቶች በሁለት ሳምንት ውስጥ ከብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ጋር የማስተሳሰር ሥራ እንዲያጠናቅቁ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል። ብሔራዊ ባንክ እና የብሔራዊ መታወቂያ በጋራ ባወጡት አዲስ የአተገባበር ሥርዓት መሰረት የፋይናንስ ተቋማት ብሄራዊ ኦፕሬተር በሆነው ኢት-ስዊች በኩል ከብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ጋር የማስተሳሰር ሥራ መስራት መጀመራቸው ተገልጿል። እስካሁን 10 የሚሆኑ የፋይናንስ ተቋማት ከብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ጋር የማስተሳሰሩን ሥራ ጨርሰዋል ሲባል ሌሎች ባንኮች በሙከራ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ይለበስ አዲስ ለኢትዮ ነጋሪ እንደገለጹት ይህ አሰራር ባንኮች አገልግሎታቸው ቀልጣፋ እንዲሆንና ማዕከላዊ የመረጃ አያያዝ እንዲኖር ያስችላል ሲሉ ገልጸዋል። አክለውም ትስስሩ ባንኮች ከደንበኞቻቸው ጋር ያላቸውን አገልግሎት ያሳልጥላቸዋል፤ ወጪንም ይቆጥብላቸዋል ብለዋል፡፡ የኢት-ስዊች ቺፍ ፖርት ፎልዮ ኦፊሰር…
Read More
ኢትዮጵያ ከቻይና ያለባትን ዕዳ ወደ ዩዋን እንዲቀየር ጠየቀች

ኢትዮጵያ ከቻይና ያለባትን ዕዳ ወደ ዩዋን እንዲቀየር ጠየቀች

ኢትዮጵያ ለቻይና መንግሥት የምትከፍለውን ቢያንስ 5.38 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ በከፊል ወደ ቻይና ገንዘብ (ዩዋን) ለመቀየር ከቤጂንግ ጋር ውይይት መጀመሯ ተዘግቧል። ይህ እርምጃ ቀደም ሲል ኬንያ ያደረገችውን በመከተል፣ ቻይና የገንዘብ ምንዛሪዋን ዓለም አቀፋዊ የማድረግ ጥረቷን የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል። ብሉምበርግ እንደዘገበው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ እዮብ ተካለኝ ባለፈው ወር ወደ ቤጂንግ ባደረጉት ጉብኝት ከቻይና ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ እና ከቻይና ሕዝብ ባንክ ጋር ለዚህ እምቅ የዕዳ ልውውጥ ውይይት መጀመራቸውን አስታውቀዋል። ገዥው ይህንን የገለጹት አርብ ጥቅምት 07 ቀን 2018 ዓ.ም. በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም (IMF) ዓመታዊ ስብሰባ ላይ በሰጡት ቃለ ምልልስ ነው። ሀገሪቷ ዕዳውን በዩዋን መክፈል የውጭ ምንዛሪ ክምችት ላይ ያለውን…
Read More
የባንኮች ብድር ዕድገት ጣሪያ ወደ 24 በመቶ አደገ

የባንኮች ብድር ዕድገት ጣሪያ ወደ 24 በመቶ አደገ

ብሔራዊ ባንክ አሁን ያለውን የዋጋ ግሽበት የመርገብ አዝማሚያ ለማስቀጠል እና የፋይናንስ ዘርፉን ጤናማነት ለመጠበቅ በመስከረም ወር ላይ ሊነሣ ይችላል ተብሎ የተገመተዉ የባንኮች ዓመታዊ የብድር ዕድገት ጣሪያን ሙሉ ለሙሉ ከማንሳት ይልቅ ገደቡ ለጊዜው ከ18 በመቶ ወደ 24 በመቶ ከፍ እንዲል ወስኗል፡፡ የባንኮች የብድር ዕድገት ገደብ መነሣት የብሔራዊ ባንክን የገንዘብ ፖሊሲ አቋም ለማመልከትና የገንዘብ ፖሊሲ መዋቅሩን የተሻለ ለማድረግ እንደሚረዳ ይታመናል ሲል ኮሚቴው አስረድቷል፡፡ ኮሚቴው  በጉዳዩ ላይ በወደፊት ስብሰባዎቹ ገምግሞ የውሳኔ ሐሳብ አንደሚያቀርብም ጠቅሷል፡፡ የብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ተመን አሁን ባለበት 15 በመቶ እንዲቆይም ወስኗል፡፡ ብሔራዊ ባንክ ለሚሰጣቸው የተቀማጭ ሂሳብ አገልግሎት እና የብድር አገልግሎት የሚከፈሉ የወለድ ተመኖች ባሉበት እንዲቀጥሉ፤ እንዲሁም ባንኮች በብሔራዊ ባንክ የሚያስቀምጡት…
Read More
ብሔራዊ ባንክ በባንኮች ላይ የጣለውን አስገዳጅ የቦንድ ግዥ አነሳ

ብሔራዊ ባንክ በባንኮች ላይ የጣለውን አስገዳጅ የቦንድ ግዥ አነሳ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ በሁሉም ንግድ ባንኮች ላይ የተጣለው አስገዳጅ የቦንድ ግዥ እንዲነሳ መወሰኑን ገልጿል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው ባደረገው ውይይት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል። ከእነዚህም ውስጥ አንዱ ሁሉም ንግድ ባንኮች የረጅም ጊዜ የግምጃ ቤት ቦንድ (Treasury Bond) እንዲገዙ የሚያስገድደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ (MFAD/TRBO/001/2022) እንዲነሳ ያሳለፈው ወሳኔ ተጠቃሽ ነው። "አሁን ላይ የመንግሥት ገቢ የማሰባሰብ አቅም በእጅጉ በመሻሻሉ፣ እንዲሁም መንግሥት የበጀት ጉድለቱን ለሟሟላት የውጭና ገበያ መር የሆኑ የሀገር ውስጥ የመበደሪያ አማራጮችን እየተጠቀመ በመሆኑ በባንኮች ላይ ተጥሎ የቆየውን ይህ አስገዳጅ መመሪያ አሁን ላይ ማንሣቱ ተገቢ መሆኑን ኮሚቴው አምኖበታል" ሲል መግለጫው ጠቅሷል። ኮሚቴው ያመነበት ይህ የገንዘብ…
Read More
በኢትዮጵያ የውጭ ባንኮች እንዲሰሩ ተፈቀደ

በኢትዮጵያ የውጭ ባንኮች እንዲሰሩ ተፈቀደ

የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ከዛሬ ጀምሮ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የባንክ ዘርፍ ለውጭ ተሳትፎ ክፍት የሚያደርግ አዲስ መመሪያን ዛሬ ይፋ አድርጓል። ይህ እርምጃ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት ለማድረግ ሲደረግ የቆየው ጥረት የመጨረሻው ምዕራፍ ተደርጎ እንደሚወሰዱ ተገልጿል። መመሪያ ቁጥር SBB/94/2025 ባለፉት አንድ ዓመት በተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተደረጉ ሰፊ ውይይቶች እና ምክክሮች ግብዓት ተደርጎበት የተዘጋጀ መሆኑ ታውቋል። ይህ መመሪያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፀደቀው የባንክ ሥራ አዋጅ መሰረት የወጣ ሲሆን፣ የሚያስፈልገውን የሕግ ማዕቀፍ ማሟላቱ ተገልጿል። ይህ አዲሱ የፈቃድ አሰጣጥ መመሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ ባለሀብቶች፣ ባንኮችን እና ሌሎች ስትራቴጂካዊ ባለሀብቶችን ጨምሮ፣ በኢትዮጵያ የባንክ ሥርዓት ውስጥ እንዲሳተፉ ያስችላል ተብሏል። ብሔራዊ…
Read More
ኢትዮጵያ በውጭ ባንኮች ላይ የአምስት ቢሊዮን ብር ግዴታ ጣለች

ኢትዮጵያ በውጭ ባንኮች ላይ የአምስት ቢሊዮን ብር ግዴታ ጣለች

ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የውጪ ባንኮች አምስት ቢሊዮን ብር ዝቅተኛ ካፒታል ሟሟላት እንደሚኖርባቸው ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያወጣው አዲስ መመሪያ ጥብቅ ቅደመ ሁኔታዎችን ያስቀመጠ ነው ተብሏል። መመሪያው በባንኩ ዘርፍ የውጭ ሀገራት ተሳትፎን የውጭ ባንክ ተቀጥላ፣ የውጭ ባንክ ቅርንጫፍ እና የእንደራሴ ቢሮ ብሎ የሚከፍል ሲሆን ወደ ሥራ ከመግባታቸው በፊት የወንጀል እና የታክስ ማጣራትን ጨምሮ ጥብቅ ምርምራዎችን ማለፍ እንደሚጠበቅባቸው አስቀምጧል። የውጭ ባንኮች የደንበኞቻቸውን መረጃ በኢትዮጵያ ድንበር ውስጥ ብቻ ለማስቀመጥ እና ለመጠቀም ይገደዳሉ የተባለ ሲሆን ክፍያን በተመለከተ ከውጭ የሚገቡ ባንኮች ለምርመራ 200 ሺህ፣ ለፈቃድ 400 ሺህ እና ለእድሳት 400 ሺህ ብር መክፈል እንዳለባቸው ተቀምጧል። መመሪያው የሀገር ውስጥ ባንኮች ካፒታላቸውን መጨመር፣ የመረጃ አጠቃቀም ሕጋቸውን ከሀገሪቱ…
Read More
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የ50 ሚሊዮን ዶላር ጨረታ እንደሚያወጣ ገለጸ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የ50 ሚሊዮን ዶላር ጨረታ እንደሚያወጣ ገለጸ

ብሔራዊ ባንክ የዶላር ጨረታ በየ15 ቀኑ በተከታታይ አወጣለሁም ብሏል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በየሁለት ሳምንት መደበኛ የውጭ ምንዛሪ ሽያጭ ጨረታ ማካሄድ እንደሚጀምር አስታወቀ። ጨረታዎቹ ለሚቀጥሉት በርካታ ወራት የሚካሄዱ ሲሆን፣ ዓላማውም የማዕከላዊ ባንኩን የተረጋጋ የውጭ ምንዛሬ ስርዓት ግብን ለማሳካት ነው ብሏል። የማዕከላዊ ባንኩ የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት በታሪኩ ከፍተኛው እንደሆነ ገልጾ በተለይ ከቅርብ ወራት ወዲህ፣ በሀገሪቱ ውስጥ ብቸኛው የወርቅ ገዥ ለሆነው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የቀረበው የወርቅ መጠን ከፍተኛ መሆን የሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት ከተገመተው በላይ እንዲጨምር እንዳደረገው ጠቁሟል። ከዚህ ከተጠበቀው በላይ ከሆነው የውጭ ምንዛሪ ግኝት አንጻር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቀጣይ ወራት በመደበኛነት በየሁለት ሳምንቱ የውጭ ምንዛሪ ሽያጭ ጨረታዎችን ለማካሄድ መወሰኑን አሳውቋል።…
Read More
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 60 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አቀረበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 60 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አቀረበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ነገ እንደሚያካሂድ ገልጿል፡፡ 60 ሚሊየን ዶላር በነገው ዕለት በሁሉም ባንኮች ለጨረታ እንደሚቀርብ ባንኩ አስታውቋል። ባንኩ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ፕሮግራምን ተከትሎ የኢትዮጵያ የውጭ ክፍያ ሚዛን በተለይም የወጪ ንግድ፣ ሐዋላና የካፒታል ፍሰት በከፍተኛ ደረጃ መሻሻል ማሳየቱን ጠቅሷል። በተለይም ከቅርብ ወራት ወዲህ ወርቅን ወደ ውጭ የመላክ ብቸኛ ሥልጣን ላለው ብሔራዊ ባንክ የሚቀርበው የወርቅ መጠን በመጨመሩ ምክንያት የባንኩ ዓለም አቀፍ የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት መጨመሩን ገልጿል። በመሆኑም ከባንኩ የወርቅ ግዥ ጋር በተያያዘ የሚከሰተውን የገንዘብ አቅርቦት ዕድገት ለማገናዘብና በማዕከላዊ ባንኩ እጅ ካለው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ከፊሉን ለግሉ ዘርፍ በመስጠት በገበያው ላይ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦትን ለማሻሻል ባንኩ የተወሰነ…
Read More