MoFAethiopia

ኢትዮጵያ የኤርትራ ፖሊሲዬ “ሙሉ በሙሉ ከሸፈ” አለች

ኢትዮጵያ የኤርትራ ፖሊሲዬ “ሙሉ በሙሉ ከሸፈ” አለች

ከኤርትራ ጋር በትብብር ላይ የተመሰረተ፣ አዎንታዊ እና ገንቢ የረጅም ጊዜ ግንኙነትን ለመመስረት የሚያስችል አካሄድን ወይም ፖሊሲን ስንከተል ነበር ያሉት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ፖሊሲው አሁን "ሙሉ በሙሉ ከሽፏል" ብለዋል። ለፖሊሲው መክሸፍ "አጋጣሚውን መጠቀም አልተቻለም" ያሉትን የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን የኤርትራ አገዛዝ ተጠያቂ አድርገዋል። አገዛዙ በኢትዮጵያ ላይ እየተከተለ ባለው 'የተሳሳተ' ፖሊሲ ምክንያት ዘላቂ ግንኙነት ለመመስረት የተደረጉ ሙከራዎች ሁሉ ሙሉ በሙሉ መክሸፋቸውንም ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ትኩረቱን በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲና በአፍሪካ ቀንድ ዙሪያ ባሉ ወቅታዊ የፖለቲካና የደህንነት ሁነቶች ላይአድርጎ ትናንት ሐሙስ ህዳር 4 ቀን 2018 ዓ/ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ በተካሄደ የውይይት መድረክ ላይ የተናገሩት። በመድረኩ ሁነቶችን…
Read More
ጌዲዮን ጥሞቲዮስ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው ተሾሙ

ጌዲዮን ጥሞቲዮስ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው ተሾሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለተለያዩ ተቋማት አዳዲስ ሚኒስትሮችን ሾመዋል። በዚህም መሰረት ጌዲዮን ጥሞቲዮስ (ዶ/ር) በቅርቡ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ተደርገው በተሾሙት ታዬ አጽቀስላሴ ምትክ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው ተሾመዋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሹመት በተጨማሪም ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ የፍትህ  ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል። ወ/ሮ ሃና አርዓያሥላሴ ፍትህ ሚኒስትር ተደርገው ከመሾማቸው በፊት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዲሁም ከዚያ በፊት የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ እንዲሁም የመንግስት ኮሙንኬሽን ምክትል ሚኒስትር የነበሩት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ የቱርዝም ሚንስትር ተደርገው መሾማቸውንም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ደኤታ በመሆን በማገልገል ላይ የነበሩት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ፤…
Read More
ኢትዮጵያ የአውሮፓ ሕብረትን መግለጫ እንደምትቀበል ገለጸች

ኢትዮጵያ የአውሮፓ ሕብረትን መግለጫ እንደምትቀበል ገለጸች

ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ሕብረት ጋር ያላትን ትብብር በአዲስ መልክ እንደገና ለማደስ አበክራ እየሰራች እንደምትገኝም ገልጿል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ ሕብረት ምክር ቤት ከትናንት በስቲያ ኢትዮጵያን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ዙሪያ ምላሽ አውጥቷል። ሚኒስቴሩ ምክር ቤቱ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ትግበራ ላይ የተገኙ ውጤቶችን ጨምሮ ለሌሎች ጉዳዮች እውቅና መስጠቱን ገልጿል። ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ሕብረት ጋር ያላትን ትብብር በአዲስ መልክ እንደገና ለማደስ አበክራ እየሰራች እንደምትገኝና የምክር ቤቱ መግለጫም ይሄንኑ ትብብር ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን አመልክቷል። ሕብረቱ በዘላቂ ግብርናና የምግብ ዋስትና ላይ ያተኮረውን ዓመታዊ የባለብዙ ዘርፍ የድጋፍ ፕሮግራም በድጋሚ ለመጀመር ያሳየውን ዝግጁነት፣ አበዳሪ አገራት ባቋቋሙት የጋራ ማዕቀፍ ስር የሚከናወነው የኢትዮጵያ የዕዳ ሽግሽግ የድርድር ሂደት በአፋጣኝ እንዲቋጭ ያቀረበው ጥሪና…
Read More