Humanrightsviolations

የጸጥታ ሀይሎች በአማራ ክልል ሰላማዊ ዜጎችን መግደላቸው ተገለጸ

የጸጥታ ሀይሎች በአማራ ክልል ሰላማዊ ዜጎችን መግደላቸው ተገለጸ

በአማራ ክልል ሰላማዊ ዜጎች ከፍርድ ቤት ውጪ በአደባባዮች ላይ መገደላቸውን ኢሰመኮ ገለጸ። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ መግለጫ አውጥታል። ኮሚሽኑ በሪፖርቱ በአማራ ክልል ጎንደርና ሸዋሮቢት በርካታ አካባቢዎች ከፍርድ ቤት ትዕዛዘው ውጪ ሰላማዊ ሰዎች በፀጥታ ሀይሎች መገደላቸውን የሚያመላክቱ መረጃዎች እንደደረሱት ገልጻል። ተፋላሚ ሀይሎች ያለምንም ቅደመ ሁኔታ ግጭቶችን እንዲያቆሙ፣ ለሰላማዊ ንግግር ስፍራ እንዲያመቻቹና ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡ ኮሚሽኑ አክኖም በአማራ ክልል ያለው ግጭት በሰብዓዊ መብቶች ላይ እያሳደረ ያለውን ተፅዕኖ እየተከታተለ መሆኑን ገልጾ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከመደንገጉ በፊትና በኋላ ከአዲስ አበባና ከሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች መረጃዎችን እከተቀበለ እንደሆነም አስታውቋል። በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች…
Read More
በኢትዮጵያ የተቀበሩ ፈንጂዎች ፈንድተው 23 ህጻናት መገደላቸው ተገለጸ

በኢትዮጵያ የተቀበሩ ፈንጂዎች ፈንድተው 23 ህጻናት መገደላቸው ተገለጸ

በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመት የነበረው ጦርነት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በተፈረመ ስምምነት መሰረት ማብቃቱ ይታወቃል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እንዳለው ሲቪል ሰዎች በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ፣ በእርሻ ፣ በውሃ መቅጃ እና በገበያ ቦታዎች እንዲሁም የትምህርት ወይም የጤና ተቋማትን የመሳሰሉ የዕለት ተዕለት መሠረታዊ ሕይወት ወደሚከወኑባቸው ሥፍራዎች በሚወስዱ መንገዶች አካባቢ የተቀበሩ ፈንጂዎች ፣ የተጣሉ ቦምቦች ፣ የከባድ መሣሪያ ቅሪቶች እና በቀላል ንክኪ የሚፈነዱ ሌሎች መሣሪያዎች በሰዎች ሕይወት ፣ አካልና ንብረት ላይ ጉዳት እያደረሱ ይገኛል ብላል። ኮሚሽኑ ይህን በተመለከተ ባደረገው ክትትል በአፋር ክልል ፣ ካሳጊታ ከተማ በአንድ መኖሪያ አካባቢ በድንገት በፈነዳው የሞርታር ጥይት ምክንያት 4 ሰዎች ወዲያው ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን በከፍተኛ ደረጃ የአካል ጉዳት…
Read More
ኢትዮጵያ የሂዩማን ራይትስ ዋች ሪፖርትን ውድቅ አደረገች

ኢትዮጵያ የሂዩማን ራይትስ ዋች ሪፖርትን ውድቅ አደረገች

ኢትዮጵያ ሂዩማን ራይትስ ዋች በትግራይ ክልል ተፈጸመ በሚል ያወጣውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሪፖርት እንደማትቀበለው አስታውቃለች። በፌደራል መንግስቱ እና በትግራይ ሀይሎች መካከል የሰላም ስምምነት ቢፈረምም አሁንም በትግራይ ምዕራባዊ አካባቢዎች የሚካሄደው የዘር ማጽዳት ወንጀል መቀጠሉንና የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ አካላትም ለፈጸሙት ግፍ ተጠያቂ አልተደረጉም በማለት ሂዩማን ራይት ወች ከሰሞኑ ያወጣውን ሪፖርት አስመልክቶ መንግስት ምላሽ ሰጥቷል፡፡ መንግስት በምላሹም ሪፖርቱ በአንዳንድ አካባቢዎች ጉልህ የሆኑ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን የሚገልጽ መሰረተ ቢስ ሪፖርት ነው ሲል ተችቷል። አክሎም በሰሜኑ ኢትዮጵያ ክፍል የነበረው ግጭት በርካታ አካባቢዎችን ለጉዳት ያጋለጠ ቢሆንም በልዩ ሁኔታ የተወሰነ አካባቢን መርጦ ደጋግሞ ሪፖርት በማዘጋጀት በሰብዓዊ መብት አጀንዳ ሽፋን የተለየ የፖለቲካ ተልዕኮዉን ለማሳካት ዓላማ ያደረገ…
Read More