Israelnews

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኢራንን ጥቃት አወገዙ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኢራንን ጥቃት አወገዙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እሁድ ዕለት ኢራን በኩዌት ላይ የፈጸመችውን ጥቃት ተከትሎ ከኩዌት ልዑል አልጋ ወራሽ ሼክ ሳባህ ኻሊድ አል ሀማድ አል ሳባህ ጋር በስልክ መወያየታቸው ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከኩዌቱ ልዑል አልጋ ወራሽ ጋር ባደረጉት ውይይት በአገሪቱ ሉዓላዊ ግዛት እና የአየር ክልል ላይ የሚፈጸም ጥቃትን በጽኑ ማውገዛቸውን የኩዌት የዜና ወኪል ዘግቧል። ይህ በዚህ እንዳለም ኢራን በእስራኤል እና አሜሪካ በደረሰባት የአየር ላይ ጥቃት የአጸፋ እርምጃ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ላይ በምትወስዳቸው እርምጃዎች ኢትዮጵያዊን መጎዳታቸው እየተገለጸ ይገኛል፡፡ በመቶ ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊን እስራኤልን ጨምሮ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ተቀጥረው በመስራት ላይ ሲሆኑ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬት፣ ኳታር፣ ኩዌት እና ባህሬን ብዙ ኢትዮጵያዊያን ይኖራሉ፡፡ ኢራን…
Read More
የእስራኤል አምባሳደር ከአፍሪካ ህብረት ተባረሩ

የእስራኤል አምባሳደር ከአፍሪካ ህብረት ተባረሩ

የእስራኤል አምባሳደር ከሩዋንዳ የዘር ማጥፋት መታሰቢያ ላይ በአፍሪካ ህብረት ተባረሩ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር የሆኑት አብርሃም ንጉሴ፣ ዛሬ መጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም. በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ሰለባዎችን ለማስታወስ በተካሄደው 31ኛዉ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ከአፍሪካ ህብረት ዋና ጽህፈት ቤት እንዲወጡ ተደርጓል። ይህ የሆነው በርካታ የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት አምባሳደሩ በዚሁ የሐዘን ስነ-ስርዓት ላይ መገኘታቸውን በመቃወማቸው መሆኑ ተዘግቧል ። የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኦረን ማርሞርስቴይን ድርጊቱን "አሳፋሪ" እና "ተቀባይነት የሌለው" ሲሉ በጽኑ አውግዘዋል። "በአዲስ አበባ የሚገኘው የእስራኤል አምባሳደር በተጋበዙበት፣ በሩዋንዳ የቱትሲ የዘር ማጥፋት ሰለባዎችን ለማስታወስ በተዘጋጀ ዝግጅት ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ፀረ-እስራኤላዊ የፖለቲካ አመለካከቶችን ማስተዋወቃቸው እጅግ አሳፋሪ ነው" ሲሉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ማርሞርስቴይን…
Read More
ኢትዮጵያ በሊባኖስ የሚኖሩ ዜጎቿን አስጠነቀቀች

ኢትዮጵያ በሊባኖስ የሚኖሩ ዜጎቿን አስጠነቀቀች

በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በቤሩት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ አስታውቋል። እስራኤል የሃመስ መሪ ኢስማኤል ሃኒየህ እና የሊባሱ ሄዝቦላህ የጦር መሪ ፉአድ ችኩር መግደሏን ተከትሎ ኢራን በእስራኤል ላይ የበቀል እርምጃ እንደምትወስድ ዝታለች። የኢራንን ዛቻ ተከትሎ በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል ከፍተኛ ስጋት በመንገሱ ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚደረጉ በረራዎች የተሰረዙ ሲሆን ሀገራትም ዜጎቻቸውን በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው። በቤሩት የሚገኘው የኢትዮጵያ የቆንስላ ጄኔራል ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ፤ በሊባኖስ እና በቀጠናው ያለው ወቅታዊ የፀጥታ ስጋት እና ውጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ መምጣቱን አስታውቋል። ጽህፈት ቤቱ በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ደህንነት ለማስጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን በትኩረት እየተከታተለ መሆኑን ገልጿል። በዚህም መሰረት ኢትዮጵያውያን ጥንቃቄ እንዲያደርጉና…
Read More
በእስራኤልና ሃማስ ጦርነት ቤተ እስራኤላዊያንና ኢትዮጵያውያን መጎዳታቸው ተገለጸ

በእስራኤልና ሃማስ ጦርነት ቤተ እስራኤላዊያንና ኢትዮጵያውያን መጎዳታቸው ተገለጸ

ሃማስ በእስራኤል ላይ መጠነ ሰፊ  ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ በሀገሪቱ የሚገኙ ቤተ እስራኤላዊያንና ኢትዮጵያዉያን ሰለባ መሆናቸዉን በኢትዮጵያ እስራኤል ኤምባሲ  አስታዉቋል፡፡ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለሊ አደማሱ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በወቅታዊ የጉዳቱን መጠን አሁን ላይ መግለጽ ባይቻልም ከተጎጂዎች መካከል ግን ቤተ እስራኤላዊያንና ኢትዮጵያዉያን እንደሚኖሩ ተናግረዋል፡፡ በጥቃቱ ከ700 በላይ እስራኤላዉያን መሞታቸዉን አምባሳደር አለሊ አስታዉቀዋል፡፡ በተጨማሪም ከ2 ሺህ በላይ ዜጎች ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዉ በሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኙ አምባሳደሩ ተናግረዋል፡፡ አሁን ላይ የእስራኤል ጦር ኃይል የሃማስን ጥቃት በመመከት  ጎን ለጎን የሞቱ ዜጎችን እየቀበረ እንደሚገኝ ኤምባሲዉ አስታዉቋል፡፡ ሃማስ የጀመረዉ ጥቃት በቀላሉ የሚታልፍ እንዳልሆነም አምባሳደር አለሊ ገልጸዋል፡፡ እስራኤል አንድ መቶ ሺህ ወታደሮቿን ወደ ጋዛ ማሰመራቷንም አስታዉቃለች፡፡…
Read More
እስራኤል ሁከት የፈጠሩ ኤርትራዊያንን ለማባረር ወሰነች

እስራኤል ሁከት የፈጠሩ ኤርትራዊያንን ለማባረር ወሰነች

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በቴላቪቭ በሃይለኛ ግጭት ውስጥ የተሳተፉ ኤርትራውያን በአስቸኳይ እንዲባረሩ እንደሚፈልጉ ገልፀዋል። የሀገሪቱን አፍሪካውያን ስደተኞች በሙሉ ለማስወገድ እቅድ ማውጣታቸውን አስታውቀዋል። ይህንን አስተያየት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰጡት በደቡባዊ ቴል አቪቭ በኤርትራ ተቀናቃኝ ቡድኖች መካከል በነበረ ደም አፋሳሽ ግጭት በርካታ ሰዎች ላይ ጉዳት ከደረሰ  ከአንድ ቀን በኋላ ነበር። ኔታንያሁ የተከሰተውን ሁከት ተከትሎ በትላንትናው እለት በተጠራው ልዩ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ “በሁከት ፈጣሪዎች ላይ ከባድ እርምጃዎችን እንፈልጋለን ፣ የተሳተፉትን ወዲያውኑ ወደ መጡበት መመለስ እንፈልጋለን” ብለዋል ። ሚኒስትሮቹ “ሌሎች ህገወጥ ሰርጎ ገቦችን ለማስወገድ” እቅድ እንዲያቀርቡላቸው የጠየቁ ሲሆን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ስደተኞቹን ለቀው እንዲወጡ ለማስገደድ የታቀዱ አንዳንድ እርምጃዎችን መተላለፉን በንግግራቸው አስታውቀዋል። በአለም አቀፍ ህግ…
Read More