25
Dec
የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) የጥቅምት 2025 ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ በኢትዮጵያ በሚገኙ ስድስት የድንበር ፍሰት መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ የታየው የሰዎች እንቅስቃሴ ካለፈው መስከረም ወር ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል። በወሩ ውስጥ በአጠቃላይ 45,150 የሰዎች ዝውውር የተመዘገበ ሲሆን፣ ይህም በቀን በአማካይ 1,456 ሰዎች ድንበር እንደሚያቋርጡ ያሳያል ነው የተባለው። ከእነዚህ እንቅስቃሴዎች ውስጥ አብዛኛው ማለትም 78.3 በመቶው (35,341 ሰዎች) ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ የሚወጡ ሲሆን፣ ቀሪው 21.7 በመቶው (9,809 ሰዎች) ደግሞ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ናቸው። በጥቅምት ወር ድንበር አቋርጠው የሚወጡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ካለፈው የመስከረም ጋር ሲነጻጸር የ38 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ሪፖርቱ አመላክቷል። ይህ የፍልሰት መጨመር በተለይ በሱዳን ድንበር በሚገኘው በመተማ በኩል በከፍተኛ ሁኔታ የታየ…