30
Apr
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ሴት ሰራተኞች የሚከፈላቸው ደመወዝ ኑሮን ለማሸነፍ ስላላስቻላቸው ማታ ማታ በወሲብ ንግድ የተሰማሩ መኖራቸውን በጥናት መለየቱን የጨርቃ ጨርቅ ፌዴሬሽን ገልጿል፡፡ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ሴት ሰራተኞች የሚከፈላቸው ደመወዝ ለኑሮ ስለማይበቃቸው ማታ ማታ ከሆቴሎች ትርፍራፊ ምግቦችን ይዘው ወደ ቤታቸው የሚገቡ እንዳሉም ፌደሬሽኑ ጠቁሟል፡፡ አምራች ስራተኛ፣ ምቹ ስራ ለወጣቶች እና ሴቶች በጨርቃ ጨርቅ አምራች ኢንዱስትሪዎች ውስጥ መፍጠር በሚል ርዕስ የፖሊሲ አቅጣጫ ጠቋሚ ጥናት ለማድረግ የማህበራት ጥናት መድረክ (Forum For Social Studies) በጠራው የሁለተኛ ዙር የባለድርሻ አካላት ወይይት ላይ የተገኙት የጨርቃ ጨርቅ ፌዴሬሽን ተወካይ አቶ ተስፋዬ አብዲሳ ‘’የሚከፈላቸው ደመወዝ ለኑሮ ስለማይበቃቸው ማታ ማታ ከሆቴሎች ተመላሽ ምግቦችን ይዘው የሚገቡ እንዳሉም በጥናት…