EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላሊበላ እና ጎንደር የነበረውን በረራ ሰረዘ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላሊበላ እና ጎንደር የነበረውን በረራ ሰረዘ

በአማራ ክልል በርካታ ከተሞች በሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ እየተካሄደ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ ከተጀመረ ሳምንታትን ያስቆጠረ ሲሆን ንጹሃን የጉዳት ሰለባ እየሆኑ እንደሆነም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ ተናግረዋል፡፡ አቶ ክርስቲያን አክለውም የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስተዳድር በአማራ ክልል የተለያዩ ቦታዎች በህዝብ ላይ ተኩስ ከፍቷል ብለዋል፡፡ የግጭቱ መነሻ የአማራ ክልል ልዩ ሀይል ለምን ይፈርሳል በሚል እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን የቀድሞ ልዩ ሀይል አባላት እና የፋኖ ታጣቂዎች ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር ውጊያ ውስጥ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡ የፋኖ ታጣቂዎች ቀስ በቀስ ወረዳዎችን እና ከተሞችን እየተቆጣጠሩ መምጣታቸውን ተከትሎ በታጣቂዎቹ…
Read More
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና መብረር የጀመረበትን 50ኛ ዓመት አከበረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና መብረር የጀመረበትን 50ኛ ዓመት አከበረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና መብረር የጀመረበትን 50ኛ ዓመት አከበረ። አየር መንገዱ ወደ ሻንግሀይ ከተማ የካቲት 1973 የመጀመሪያ የቻይና በረራውን በማድረግ አገልግሎቱን የጀመረ ሲሆን ከጥቅምት 1973 ጀምሮ ደግሞ መዳረሻውን ወደ ቤጂንግ ከተማ በመቀየር አገልግሎን ቀጥሏል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት በ5 የመንገደኛ እና 9 የእቃ ጭነት መደበኛ በረራዎች በአጠቃላይ 66 ሳምንታዊ በረራዎችን ወደ 10 የቻይና ከተሞች በማድረግ ላይ ይገናል። ቤጂንግ፣ ጓንዡ፣ ሼንጁ፣ሻንግሀይ፣ ሸንዘን ፣ ውሀን፣ቻንግሻ፣ዢያመን፣ቸንዱ እና ሆንግ ኮንግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚበርባቸው የቻይና ከተሞች ናቸው። የአፍሪካ ግዙፍ የአቪዬሽን ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ200 በላይ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች አሉት። በ1945 የተመሰረተው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 70ኛ የምስረታ በዓሉን ከአንድ ዓመት በፊት…
Read More
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኮፐንሀገን ወደ አዲስ አበባ የካርጎ አገልግሎት ጀመረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኮፐንሀገን ወደ አዲስ አበባ የካርጎ አገልግሎት ጀመረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኮፐንሀገን ወደ አዲስ አበባ የካርጎ አገልግሎት ጀመረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዴንማርክ  ኮፐንሀገን ወደ አዲስ አበባ ሳምንታዊ  የእቃ ጭነት አገልግሎት በረራ ጀመረ።  የእቃ ጭነት በረራው  የሚደረገው  በቅርቡ ከመንገደኛ ወደ እቃ ጭነት አገልግሎት በተቀየረው ቦይንግ 767-300F አውሮፕላን እንደሆነ ተገልጿል። በዚህ ሳምንታዊ እያንዳንዱ በረራ እስከ 45 ቶን ያህል ጭነት እንደሚጓጓዝ አየር መንገዱ ለኢትዮ ነጋሪ ገልጿል። ይህ አዲስ የእቃ ጭነት  አገልግሎት በአውሮፓ  እና በተቀረው  ዓለም መካከል  ያለውን የንግድ  እንቅስቃሴ የሚያሳልጥ ይሆናል ተብሏል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመጪው ግንቦት ወር  ጀምሮ ወደ ኮፐንሀገን  የመንገደኛ በረራ  አገልግሎት እጀምራለሁ ብሏል። ይህ የመንገደኞች በረራ መጀመርም ተጨማሪ  የካርጎ  አገልግሎት አቅም ይፈጥርልኛል ብሏል። ይህ በዚህ እንዳለ የኢትዮጵያ አየር መንገድ  ወደ  ኢንዶኔዢያ ዋና ከተማ ኩዋላላፑር ከተማ አዲስ በረራ እንደሚጀምር አስታውቋል። አየር መንገዱ ከመጋቢት 24,…
Read More
የኢትዮጵያ አቪየሽን አካዳሚ ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ አደገ

የኢትዮጵያ አቪየሽን አካዳሚ ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ አደገ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚ ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ በማደግ በኤሮስፔስ እና በተለያዩ የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፎች በቅድመ ምረቃ እና ድሕረ ምረቃ ፕሮግራሞች ማስተማር ጀመረ። የአቪዬሽን አካዳሚ የአቪዬሽን ስልጠና ፕሮግራሞችን በአብራሪነት፣ የአውሮፕላን ቴክኒሻን፣ የካቢን ሰራተኛ፣ የአየር መንገድ ሽያጭ እና አገልግሎት እና ሌሎች ስልጠናዎችን ሲሰጥ ቆይቷል።  ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ካደገ በኋላ በኤሮኖቲካል ኢንጂነሪንግ በቢኤስሲ ዲግሪ፣ በአውሮፕላን ጥገና ኢንጂነሪንግ በቢኤስሲ ዲግሪ፣ በአቪዬሽን ማኔጅመንት ቢኤስሲ ዲግሪ፣ በቱሪዝም እና ሆስፒታሊቲ ማኔጅመንት ቢኤ ዲግሪ እና ኤምቢኤ በአቪዬሽን ማኔጅመንት የመሳሰሉ የዲግሪ መርሃ ግብሮችን ጀምሯል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው እንደተናገሩት "ከቀጣይ እድገትና ኢንቨስትመንት በኋላ 65 ዓመት ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ አቪዬሽን አካዳሚ ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ማደጉ…
Read More