01
Jan
ለውጭ ገበያ የማይውሉ ና የተመለሱ ምርቶች ግብይት በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ብቻ በኩል እንዲሸጡ አስገዳጅ አሰራር ቢዘረጋም ምርቶቹ መዳረሻቸዉ እየታወቀ አይደለም ተብሏል። ከዉጪ ገበያ የሚመለሱት ምርቶች ግብይት በኢትዮጵያ ምርት ገበያ አማካኝነት መሆን እንዳለበት ቢቀመጥም ይህ ተግባራዊ እየተደረገ እንዳልሆነ ተገልጿል። የፌደራል ዋና ኦዲተር እንዳስታወቀው ቡናን ጨምሮ ሁሉም ምርቶች መዳረሻቸዉ እየታወቀ አለመሆኑን ተናግሯል። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ የምርት ቅበላ፣ ክምችት እና የግብይት ሥርዓት አፈፃፀምን በተመለከተ የተከናወነ የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ላይ ማብራሪያ ጠይቋል። ከዉጪ ገበያዉ የሚመለሰዉን እና የማይወለዉን ምርት የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ሻጭ እና ገዥን የማገናኘት ሀላፊነት በግብይቱ ላይ እየታየ አይደለም ሲሉ የፌደራል ዋና ኦዲተር…