10
Feb
በደመቀ ከበደ በኢትዮጵያ የፈጠራና የባህል ኢኮኖሚ ላይ የተጋረጠው የ"ዲጂታል ይዘት ስርቆት" እና ችላ የመባሉ አስጊ ተፅዕኖዎች በአዲስ አበባ እምብርት ውስጥ ወጣት የሙዚቃ አቀናባሪዎች የሙዚቃ ገበያውን ዓለም ሊያነቃንቁ የሚችሉ ቅኝቶችን ሲያመርቱ ይውላሉ። ፊልም ሰሪዎቻችን የኢትዮጵያን ማንነትና ነፍስ የሚዘክሩ ታሪኮችን በካሜራቸው ይስላሉ። በከተማዋ በሚገኙ የሲኒማቶግራፊ ስቱዲዮዎች እና የዲጂታል አማራጮች ውስጥም የሀገር በቀል ታሪኮችን ከዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃ ጋር ያዋሃዱ የሚዲያ ስራዎች ለመፍጠር እየታተሩ ነው። በሽሮ ሜዳ የእጅ ባለሙያዎችም የዘመናት ቅርስ የሆነውን የጋሞን ጥበብና ድንቅ ድሮችን ወደ ዘመናዊ ገበያ እያመጡ ነው። በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ የሰርከስ ተሳታፊዎችና የውዝዋዜ ቡድኖች ጥንታዊ ትውፊትን ከዘመናዊ ፈጠራ ጋር አዋህደው ልምምዳቸውን ያደርጋሉ። ከሶፍትዌር አልሚዎችና ዲዛይነሮች እስከ ጸሐፍትና የሶሻል…