Nileriver

የአሜሪካ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፎር ላንዳው አዲስ አበባ ገቡ

የአሜሪካ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፎር ላንዳው አዲስ አበባ ገቡ

ላዳው በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና ሌሎች የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ለመምከር ባደረጉት ጉዞ የአሜሪካ አፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰንን አስከትለው አዲስ አበባ ገብተዋል። የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የአሜሪካ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፎር ላንዳው እና የአሜሪካ አፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰን በኢትዮጵያ አየር ኃይል የተዘጋጀውን ዓለም አቀፍ የአቭዬሽን ኤክስፖ መጎብኘታቸውን የመከላከያ ሚኒስቴር በፌስቡክ ገጹ ከምስል ጋር አጋርቷል። ኢትዮጵያ እና ግብጽን ጨምሮ አራት የአፍሪካ ሀገራትን በመጎብኘት ላይ ያሉት ክርስቶፈር ላንዳው በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ላንዳው በዛሬው ዕለት የተመሰረተበትን 90ኛ ዓመት እያከበረ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር ሀይል አቪዬሽን ኤክስፖ ጎብኝተዋል ተብሏል፡፡ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአፍሪካ…
Read More
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለ3ኛ ጊዜ የህዳሴውን ግድብ ግንባታ ወጪ አሜሪካ መሸፈኗን ተናገሩ

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለ3ኛ ጊዜ የህዳሴውን ግድብ ግንባታ ወጪ አሜሪካ መሸፈኗን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን የመጡበትን አንደኛ ዓመት አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ወጪ በሀገራቸው መሸፈኑን ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ ስልጣን ላይ በቆዩባቸው ጊዜያት ስምንት ጦርነቶችን እንዳስቆሙ ገልጸው ኢትዮጵያ እና ግብጽም በህዳሴው ግድብ ምክንያት ሊያደርጉት የነበረውን ጦርነት ማስቆማቸውን ገልጸዋል። "ኢትዮጵያ በናይል ወንዝ ላይ በገነባችው ትልቅ ግድብ ምክንያት ግብጾች ተጎድተዋል፣ ውሀቸው ቀንሶባቸዋል፣ ናይል ግብጽ ውስጥ ያለ ነበር እሚመስለኝ፣ ወንዙ ይህን ጉዳይ መፍታት እፈልጋለሁ" ብለዋል ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ። "የግድቡን ግንባታ ወጪ ማን እንደሸፈነው ታውቃላችሁ? እኛው ነን" ያሉት ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢትዮጵያ እና ግብጽ መካከል ያለውን አለመግባባት የመፍታት እቅድ እንዳላቸውም ተናግረዋል። ስለ ኢትዮጵያ ህዳሴው ግድብ በተደጋጋሚ ሲናገሩ የሚሰሙት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዚህ በፊትም…
Read More
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሊጠናቀቅ ጥቂት ስራዎች ብቻ ቀርተውታል ተባለ

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሊጠናቀቅ ጥቂት ስራዎች ብቻ ቀርተውታል ተባለ

ከ13 ዓመት በፊት የተጀመረው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈፃፀም 95 በመቶ መድረሱን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባት ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ የግድቡ አጠቃላይ የሲቪል ስራው ግንባታ የደረሰበት ደረጃ 98 ነጥብ 9 በመቶ ተጠናቋል የተባለ ሲሆን የኤሌክትሮ መካኒካ ስራው ደውም በመጠናቀቅ ላይ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ በሚያመነጨው የኤሌክትሪክ ሀይል መጠን ከአፍሪካ ግዙፉ ፕሮጀክት የሆነው የህዳሴው ግድብ በአሁኑ ወቅት በሁለት ተርባይኖች 540 ሜጋ ዋት በማመንጨት ላይ ይገኛል፡፡ የጽህፈት ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀይሉ አብርሃም የግድቡ ግንባታ የተጀመረበትን 13ኛ ዓመት አስመልክቶ እንደተናገሩት አሁን ላይ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ እየተመረተ ያለው ኤሌትሪክ ኃይል በ2 ተርባይኖች 540 ሜጋ ዋት መሆኑን ያነሱ…
Read More
የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሲቪል ሥራ በተያዘው ዓመት እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሲቪል ሥራ በተያዘው ዓመት እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች እና ፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ከሁለት ወራት የእረፍት ጊዜ በኋላ ተከፍቷል፡፡ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ በምክር ቤቶቹ የመክፈቻ ንግግራቸው ላይ የመንግስትን የአንድ ዓመት የትኩረት መስኮች ይፋ አድርገዋል፡፡ ፕሬዝዳንቷ በንግግራቸው ላይ ያለፈው ዓመት የኢትዮጵያ ህዳሴው ግድብ ግድብ 4ኛ ዙር የውኃ ሙሌት መጠረናቀቁ ትልቁ ስኬት ነበር ብለዋል፡፡ 90 በመቶ ግንባታው የተጠናቀቀው የህዳሴው ግድብ የሲቪል ምህንድስና ስራ ሙሉ ለሙሉ በዚህ ዓመት እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል፡፡ ይህ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ብቻ የሚያመነጭ ግድብ ሳይሆን የቱሪዝምና የውሃ ሀብት፣ የአካባቢ ጥበቃ እና የሞራል ልዕልና ነው ብለዋል፡፡ ፕሬዝዳንቷ አክለውም መንግስት በተያዘው ዓመት የሕግ የበላይነትን ማስከበር፣ የኑሮ ውድነትን መቀነስ፣ የስራ እድል ፈጠራ ፣ የምግብ ዋስትና እና መልካም አስተዳድር ልዩ ትኩረት…
Read More
የሕዳሴው ግድብ አራተኛ ዙር የውሀ ሙሌት ተጠናቀቀ

የሕዳሴው ግድብ አራተኛ ዙር የውሀ ሙሌት ተጠናቀቀ

የግድቡ አራተኛ እና ና የመጨረሻ ሙሌት መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ  "የሕዳሴው ግድብን አራተኛና የመጨረሻ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ሳበስር በታላቅ ደስታ ነው፤  ኢትዮጵያውያን ተባብረን በመሥራታችን ፈጣሪ ረድቶናል። " በማለት የግድቡ የመጨረሻ ሙሌት መጠናቀቁን አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ "በገንዘባቸው፣ በዕውቀታቸው፣ በጉልበታቸውና በጸሎታቸው በስራው ውስጥ የተሳተፋችሁ ሁሉ  እንኳን ደስ አላችሁ፤ ይህ ኅብረታችን በሌሎች ጉዳዮቻችንም ሊደገም ይገባዋል" ብለዋል። ከ12 ዓመት በፊት የተጀመረው የታላቂ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አጠቃላይ ግንባታው 91 በመቶ ደርሷል ተብሏብ። ኢትዮጵያዊያን በሚያዋጡት ገንዘብ እነ በመንግስት ወጪ እየተገነባ ያለው ይህ ግድብ በ5ሺህ 200 ሜጋ ዋት ሀይል በማመንጨት ከአፍሪካ ትልቁ ፕሮጀክት ነው። የህዳሴው…
Read More