18
Sep
በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢኒስቲትዩት የተዘጋጀው፤ ከተሽከርካሪዎች የሚወጣን ጎጂ የካይ ጋዝ ልቀት ለመቆጣጠር የሚያገለግለው አስገዳጅ መመሪያ ከመስከረም 30 ቀን 2018 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል። ዋነኛ ዓላማው የትራንስፖርት ዘርፉ ለበካይ ጋዝ ልቀት የሁለት ሦስተኛ ድርሻ ያለው በመሆኑ በጎጂ በካይ ጋዞች ምክንያት የሚከሰትን የአየር ብክለት መቀነስ ሲሆን፤ አዲሱ መመሪያ ሙሉ ለሙሉ ሲተገበር ተሽከርካሪዎች ወደ አየር የሚለቁትን የበካይ ጋዝ መጠን የሚቆጣጠር መሳሪያ እንዲገጥሙ ይገደዳሉ ተብሏል። የተቋሙ የትራንስፖርት ዘርፍ የአየር ንብረት ክትትል እና ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ ግርማ ሳሙኤል፤ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ መመሪያው ከጸደቀበት መጋቢት 2017 ጀምሮ ውይይቶች ሲካሄዱበት እንደነበርም ተናግረዋል። በዚህም አስገዳጅ መመሪያው ከጸደቀ በኋላ ከታክሲ ማኅበራት፣ ከክልል ከተማ አስተዳደሮች…