Passportservice

ከ3 ሺህ በላይ የውጭ ዜጎች ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ ሲሉ መያዛቸው ተገለጸ

ከ3 ሺህ በላይ የውጭ ዜጎች ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ ሲሉ መያዛቸው ተገለጸ

የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት እንደገለጸው ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ወደ አገር ውስጥ ሊገቡ ሲሉ ከ3 ሺህ 400 በላይ የውጭ አገር ዜጎች መያዛቸውን ጠቁሟል፡፡ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት የሶት ወራት ሪፖርት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡ ዳይሬክተሯ በዚህ ጊዜ እንዳሉት ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ከ3 ሺህ 400 በላይ የውጭ አገር ዜጎች ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ ሲሉ መያዛቸውን ገልጸዋል፡፡ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ የነበሩት የውጭ ዜጎች ቪዛ ሳያገኙ ለመግባት ሲሞክሩ፣ ህገወጥ የጉዞ ሰነድ ይዞ መገኘት እና መሰል ህገወጥ ድርጊቶችን ለመፈጸም ሲሞክሩ እንደነበር ተገልጿል፡፡ እንዲሁም ከ1 ሺህ 500 በላይ ዜጎች ከሀገር ሊወጡ ሲሉ ተይዘዋል የተባለ ሲሆን ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ በሀገር ውስጥ ቆይተው…
Read More
ኢትዮጵያ ለ10 ዓመት የሚያገለግል አዲስ ፓስፖርት ይፋ አደረገች

ኢትዮጵያ ለ10 ዓመት የሚያገለግል አዲስ ፓስፖርት ይፋ አደረገች

ኢትዮጵያ አራት አይነት ፓስፖርቶችን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጋለች የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አዲስ ፓስፖርቶችን ይፋ አድርጓል። ዛሬ በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም ይፋ የተደረጉት ፓስፖርቶች አራት አይነት ሲሆኑ ከመደበኛ ፓስፖርት በተጨማሪ የዲፕሎማት፣ ውጭ ሀገራት እና የአገልግሎት ፓስፖርቶችም ይገኙበታል። ፓስፖርቶቹ በጃፓኑ ቶፓን የደህንነት ኩባንያ እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ኩባንያ ትብብር ስለመመረቱም ተገልጿል። 10 ዓመት እንዲያገለግል ተደርጎ የተሰራው ይህ ፓስፖርት በአዲስ አበባ በሚገኘው ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የተመረተ ነው። የፓስፖርቱ አገልግሎት ጊዜ 10 ዓመት መደረግ የዜጎችን ጊዜ፣ ገንዘብ እና ጉልበት እንደሚቆጥብ ተገልጿል። ይህ በዚህ እንዳለም በፓስፖርቱ ውስጥ ገጾች ላይ የኢትዮጵያን መልካም ገጽታዎች የሚያጎለብቱ እና ታሪካዊ ቅርጾችን ይዟልም ተብሏል። እንዲሁም ፓስፖርቱ የማይክሮ ችፕስ የተገጠመለት…
Read More
ኢትዮጵያ ከ14 ሺህ በላይ ለውጭ ሀገራት ዜጎች የመኖሪያ ፈቃድ ሰጠች

ኢትዮጵያ ከ14 ሺህ በላይ ለውጭ ሀገራት ዜጎች የመኖሪያ ፈቃድ ሰጠች

ሀገሪቱ ለ20 የውጭ ዜግነት ለነበራቸው ሰዎች የኢትዮጵየዊ ዜግነት ሰጥታለች ተብሏል የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት የተቋሙን የስድስት ወራት አፈጻጸም አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ዳይሬክተሯ በመግለጫቸው ላይ እንዳሉት ለ14 ሺህ 367 ለሚሆኑ የውጭ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የመኖሪያ ፍቃድ ተሰጥቷቸዋል ብለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ለ20 ግለሰቦች ደግሞ የኢትዮጵያዊ ዜግነት እንደተሰጣቸውም ወይዘሮ ሰላማዊት በመግለጫው ለይ ጠቅሰዋል። ተቋሙ ለዜጎች የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት የሠው ሀይሉን የማጠናከር፤ አሰራሩን በቴክኖሎጂ የማገዝ ስራ እንደሚሰራም ተገልጿል። በኢትዮጵያ ለጉብኝት ቱሪስት፣ ለኮንፍረንስና ለቢዝነስ የሚገቡትን ለማስተናገድ በ188 ሀገራት ቪዛ ኦን አራይቫል በመክፈት እየተሰራ መሆኑም ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ሚሊዮን በላይ ሰዎች በአየር ትራንስፖርት ወደ ኢትዮጵያ…
Read More
በኢትዮጵያ ፓስፖርት ቤት ለቤት ማደል ሊጀመር ነው ተባለ

በኢትዮጵያ ፓስፖርት ቤት ለቤት ማደል ሊጀመር ነው ተባለ

በኢትዮጵያ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ሰዎች ፓስፖርት ተሰጥቷል ተብሏል የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዓመታዊ አፈጻጸሙን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት እንዳሉት በ2016 አመት 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ፓስፖርት ለአመልካቾ መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡ ተቋሙ በታሪኩ ይህን መጠን ያለዉ ፓስፖርት ለአገልግሎት ፈላጊዎች ሲሰጥ የመጀመሪያዉ መሆኑን ዳይሬክተሯ ጠቅሰዋል። ይህ በዚህ እንዳለም ተቋሙ ከፓስፖርት እና ሌሎች አገልግሎት ክፍያዎች 14 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱንም ተናግረዋል። የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ጭምር ቅሬታ ሲቀርብበት ቢሰማም እንዲሁም ተገልጋዮች አሁንም ቅሬታ ማቅረባቸዉን ቢቀጥሉም ፤ ተቋሙ አሰራሮቼን እያስተካከልኩ እገኛለሁ ብሏል። ዋና ዳይሬክተሯ ፤ ከዚህ…
Read More