04
Mar
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ንጹሃን ዜጎች ግድያ እንደተፈጸመባቸው አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡ ኮሚሽኑ በሪፖርቱ ላይ እን ዳስታወቀው በዞኑ ያለው ሁኔታ ለተወሰኑ ጊዜያት እየተሻሻለ የነበረ ቢመስልም ከጥቅምት ወር 2018 ዓ.ም ጀምሮ ታጣቂ ቡድኑ በሽርካ፣ በጉና፣ በመርቲ፣ በአሰኮ እና በኦንቆሌ ዋቤ ወረዳዎች በሰዎች ላይ በፈጸማቸው ጥቃቶች በሰዎች ሕይወት፣ አካልና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ገልጿል፡፡ እንዲሁም ከዚሁ ጋር በተያያዘ በተፈጠሩ የደህንነት ሥጋቶች ምክንያት የነዋሪዎች መፈናቀል መከሰቱን ኢሰመኮ የደረሱትን ጥቆማዎችና አቤቱታዎች መሠረት በማድረግ የተጎጂ ቤተሰቦችን፣ ነዋሪዎችን እና የየአካባቢዎቹን የመንግሥት ኃላፊዎች በማነጋገር ባሰባሰባቸው መረጃዎች ማረጋገጡን አስታውቋል። የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (በተለምዶ “ኦነግ ሸኔ”) የካቲት 19 ቀን 2018 ዓ.ም. በዞኑ ሽርካ ወረዳ ጃዊ…