30
Mar
ቤተ-ክርስቲያኒቱ ከህግ ውጭ ሲመተ ጵጵስና የሰጡና የተቀበሉ 26 የቀድሞ አባቶችን ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም ማውገዟ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የሦስት ጳጳሳትንና የ20 መነኮሳትን ውግዘት አንስቷል። ውግዘቱ የተነሳው ከዛሬ መጋቢት 21፤ 2015 ዓ.ም. ጀምሮ እንደሆነ ምልዓተ ጉባኤው አሳውቋል። ቅዱስ ሲኖዶስ በመግለጫው "ሦስቱም የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳት ማለትም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ እና ብፁዕ አቡነ ዜናማርቆስ ላይ የተላለፈው ውግዘት ከዛሬ መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ተነስቷል" ብሏል፡፡ በቀድሞ የሊቀ ጳጳስነት ማዕረጋቸው እንዲጠሩና ተመድበው ይሰሩበት በነበረው የስራ ኃላፊነታቸው እንዲቀጥሉም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ የየካቲት ስምንቱን ባለ10 ነጥብ ስምምነት እንቀበላለን ብለው ለቅዱስ ሲኖዶስ ደብዳቤ ያስገቡ 20 የቀድሞ አባቶች ውግዘትም…