Journalism

ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው በ20 ሺሕ ብር ዋስትና እንዲፈታ ታዘዘ

ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው በ20 ሺሕ ብር ዋስትና እንዲፈታ ታዘዘ

የቀድሞው የ“አል አይን ኒውስ” ጋዜጠኛ እንዲሁም “አራት ኪሎ ሚዲያ” የተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ ብዙሃን አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና የኢትዮ ሰላም የበይነ መረብ ሚዲያ መስራች ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው ኹለቱም በ20,000 ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ታዟል፡፡ ውሳኔውን ያስተላለፈው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ነው። ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ሐሙስ ሚያዚያ 5/2015 ቂሊንጦ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ማክሲኮ ወደሚገኘው ፌደራል ፖሊስ በጸጥታ ኃይሎች መወሰዱን የሚታወስ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፤ ሚያዚያ 4/2015 ምሽት ላይ ባህርዳር ከሚገኘው "ሆምላንድ ሆቴል" በጸጥታ ኃይሎች መወሰዱን መዘገባችን ይታወሳል። ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ሲፒጂ ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን እያሰረች መሆኑን ጠቅሶ መንግሥት ያሰራቸው  ጋዜጠኞች እንዲፈታ መጠየቁ ይታወሳል።
Read More
ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና ቴዎድሮስ አስፋው ፍርድ ቤት ቀረቡ

ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና ቴዎድሮስ አስፋው ፍርድ ቤት ቀረቡ

ሕገመንግስቱንና ሕገመንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ ተንቀሳቅሰዋል በማለት ተጠርጥረው ከአራት ቀናት በፊት ታስረው የነበሩት ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻውና ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው ዛሬ ሚያዚያ 7 ቀን 2017 ዓም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው የምርመራ ጊዜ ተጠየቀባቸው። ፖሊስ ተጠርጣሪ ጋዜጠኞቹን ፍርድ ቤት አቅርቦ ጊዜ ቀጠሮ የጠየቀባቸው፣ ጋዜጠኛ ዳዊት አራት ኪሎ ሚዲያ፣ የሚባል የኦንላይን ሚዲያ ፈቃድ ሳይኖረው በመክፈት ሕገመንግስቱንና ሕገመንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ፣ ሕዝብን ከሕዝብ ጋር ለማጋጨትና አንዱን ሐይማኖት ከሌላው ጋር ለማጋጨት በሕገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ እንደደረሰበት ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል። በተመሳሳይ ሁኔታ ጋዜጠኛ ቴዎድሮስም ኢትዮ ሰላም የሚባል የኦንላይን ሚዲያ ፈቃድ ሳይኖረው በመክፈት ሲሰራ እንደነበርና ሁለቱንም ተጠርጣሪዎች እየመረመረ መሆኑን አስረድቶ ለተጨማሪ…
Read More
መንግስት የጋዜጠኞችን እስር እንዲያቆም ተጠየቀ

መንግስት የጋዜጠኞችን እስር እንዲያቆም ተጠየቀ

የኢትዮጵያ ብዙሀን መገናኛ ባለሙያዎች ማህበር በጋዜጠኞች እስር ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል። ማህበሩ እንዳለው ብዙሀን መገናኛ ባለሙያዎች ስህተት በሚሰሩበት ወቅት ደግሞ በህግ አግባብ መጠየቅ እንዳለባቸው እና የህግ የበላይነት መከበር እንዳለበት እንደሚያምን ገልጿል። ይሁንን " ከለውጡ በኋላ " በሀገራችን የመገናኛ ብዙኃን ነፃነት እንዲረጋገጥ ማህበራችን ብዙ ተስፋ አድርጎ የነበረ ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ ባለሙያዎች የሚሰሩበት አውድ እየጠበበ ጋዜጠኞች ስራቸውን በነፃነት እንዳይሰሩ በመንግስት የፀጥታ አካላት እየተሸማቀቁ እና እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን ማህበሩ በመግለጫው ላይ ጠቁሟል። የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማህበር መስራችና የስራ አስፈፃሚ አባል እንዲሁም የማህበሩ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻውን ጨምሮ አራጋው ሲሳይ ፣ ገነት አስማማው ፣ ጌትነት አሻግሬ ፣ በየነ ወልዴና ቴዎድሮስ አስፋው…
Read More
ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው መታሰሩ ተገለጸ

ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው መታሰሩ ተገለጸ

በበርካታ የኢትዮጵያ ብዙሃን መገናኛ ተቋማት በጋዜጠኝነት ሙያ ያገለገለው ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው በጽጥታ ሀይሎች መታሰሩን የስራ ባልደረቦቹ ለኢትዮ ነጋሪ ተናግረዋል ። ጋዜጠኛ ዳዊት ከሌሎች የስራ ባልደረቦቹ ጋር በመሆን አራት ኪሎ ሚዲያ የተሰኘ የድጅታል ሚዲያ አቋቁሞ በመስራት ላይ ይገኝ ነበር። ጋዜጠኛው ለስራ ወደ ባህርዳር ከተማ ባቀናበት ወቅት ዛሬ ሚያዝያ 4 ቀን 2015 ዓ.ም በጸጥታ ሀይሎች ተይዞ መወሰዱን ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የሙያ ባልደረቦቹ ነግረውናል። ይሁንና የአማራ ክልልም ይሁን የፌደራል መንግሥት በጋዜጠኛ ዳዊት እስር ጉዳይ እስካሁን ያሉት ነገር የለም። የሀገር መከላከያ ሰራዊት ህዝብ ግንኙነት ኮለኔል ጌትነት ስለ ጋዜጠኛው እስር እንደማያውቁ ተናግረዋል። ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፣ በኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት፣ ኢቢኤስ ቴሌቪዥን፣ ኢትዮ…
Read More
ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ የ2023 ‹‹የዓለም አቀፍ የጀግና ሴቶች ሽልማት›› አሸነፈች

ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ የ2023 ‹‹የዓለም አቀፍ የጀግና ሴቶች ሽልማት›› አሸነፈች

ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ የ2023 ‹‹የዓለም አቀፍ የጀግና ሴቶች ሽልማት›› አሸነፈች መምህርት፣ ጋዜጠኛና አክቲቪስት መዓዛ መሐመድ የ2023 የ‹‹ዓለም አቀፍ የጀግና ሴቶች ሽልማት (International Women of Courage/IWOC Awards)›› አሸናፊ ሆናለች፡፡  ‹‹ዓለም አቀፍ የጀግና ሴቶች ሽልማት›› በመላው ዓለም ከባድ አደጋዎችንና ፈተናዎችን ተቋቁመው ሰላም፣ ፍትህ፣ ሰብዓዊ መብቶች፣ የፆታ እኩልነት እና የሴቶች ተጠቃሚነት እንዲከበሩና እንዲሰፍኑ ልዩ ጥንካሬ፣ ጀግንነትና የአመራር ጥበብ ላሳዩ ሴቶች የሚበረከት ሽልማት ነው፡፡ ሽልማቱ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚዘጋጅ ሲሆን፣ ዘንድሮ ለ17ኛ ጊዜ የሚካሄድ ይሆናል፡፡ እስካሁን ድረስም ከ80 ሀገራት የተገኙ ከ180 በላይ ጀግና ሴቶችን እውቅና ሰጥቷል፡፡ በዘንድሮው ሽልማት ከአራት አህጉራት የተገኙ 11 ጀግና ሴቶች እና አንድ የሴቶች ቡድን እውቅና ይሰጣቸዋል፡፡    ለሽልማቱ የሚመረጡት ሴቶች…
Read More