29
Sep
ብሔራዊ ባንክ አሁን ያለውን የዋጋ ግሽበት የመርገብ አዝማሚያ ለማስቀጠል እና የፋይናንስ ዘርፉን ጤናማነት ለመጠበቅ በመስከረም ወር ላይ ሊነሣ ይችላል ተብሎ የተገመተዉ የባንኮች ዓመታዊ የብድር ዕድገት ጣሪያን ሙሉ ለሙሉ ከማንሳት ይልቅ ገደቡ ለጊዜው ከ18 በመቶ ወደ 24 በመቶ ከፍ እንዲል ወስኗል፡፡ የባንኮች የብድር ዕድገት ገደብ መነሣት የብሔራዊ ባንክን የገንዘብ ፖሊሲ አቋም ለማመልከትና የገንዘብ ፖሊሲ መዋቅሩን የተሻለ ለማድረግ እንደሚረዳ ይታመናል ሲል ኮሚቴው አስረድቷል፡፡ ኮሚቴው በጉዳዩ ላይ በወደፊት ስብሰባዎቹ ገምግሞ የውሳኔ ሐሳብ አንደሚያቀርብም ጠቅሷል፡፡ የብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ተመን አሁን ባለበት 15 በመቶ እንዲቆይም ወስኗል፡፡ ብሔራዊ ባንክ ለሚሰጣቸው የተቀማጭ ሂሳብ አገልግሎት እና የብድር አገልግሎት የሚከፈሉ የወለድ ተመኖች ባሉበት እንዲቀጥሉ፤ እንዲሁም ባንኮች በብሔራዊ ባንክ የሚያስቀምጡት…