14
Nov
ከኤርትራ ጋር በትብብር ላይ የተመሰረተ፣ አዎንታዊ እና ገንቢ የረጅም ጊዜ ግንኙነትን ለመመስረት የሚያስችል አካሄድን ወይም ፖሊሲን ስንከተል ነበር ያሉት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ፖሊሲው አሁን "ሙሉ በሙሉ ከሽፏል" ብለዋል። ለፖሊሲው መክሸፍ "አጋጣሚውን መጠቀም አልተቻለም" ያሉትን የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን የኤርትራ አገዛዝ ተጠያቂ አድርገዋል። አገዛዙ በኢትዮጵያ ላይ እየተከተለ ባለው 'የተሳሳተ' ፖሊሲ ምክንያት ዘላቂ ግንኙነት ለመመስረት የተደረጉ ሙከራዎች ሁሉ ሙሉ በሙሉ መክሸፋቸውንም ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ትኩረቱን በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲና በአፍሪካ ቀንድ ዙሪያ ባሉ ወቅታዊ የፖለቲካና የደህንነት ሁነቶች ላይአድርጎ ትናንት ሐሙስ ህዳር 4 ቀን 2018 ዓ/ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ በተካሄደ የውይይት መድረክ ላይ የተናገሩት። በመድረኩ ሁነቶችን…