dpi

በኢትዮጵያ ዓመታዊ የድጅታል ገንዘብ ልውውጥ ከ18 ትሪሊዮን ብር በላይ ደረሰ

በኢትዮጵያ ዓመታዊ የድጅታል ገንዘብ ልውውጥ ከ18 ትሪሊዮን ብር በላይ ደረሰ

ብሔራዊ ባንክ እንዳስታወቀው በአንድ አመት ውስጥ በጂታል ክፍያ ስርአት 18 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር ዝውውር ተፈጽሟል። በኢትዮጵያ ዲጂታል ክፍያ ኮንፈረንስ 2.0. ላይ ለአምስት አመት የሚቆይ (2026-30) የብሔራዊ የዲጂታል ክፍያ ስትራቴጂ በብሔራዊ ባንክ ይፋ ሆኗል። የመጀመሪያው የ2021-24 ብሄራዊ የዲጂታል ክፍያ ስትራቴጂ ላይ ህግ ማውጣት፣ተቋማት አገልግሎቱን እንዲሰጡ ማስቻልና ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ እንዲሁም መሠረተ ልማት ዝርጋታ መከናወናቸው ተጠቁሟል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የክፍያ ስርአት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ዳምጠው ለቅዳሜ ገበያ እንደገለጹት በኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ ትልቁ ሚና የገንዘብ ዝውውር ፈጣን ቀልጣፋ ወጪ ቆጣቢ መሆን አለበት። ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የዲጂታል የክፍያ ስርአትን ማዘመን እና ለዚያ የሚያበቃ የድጅታል መሰረተ ልማት ግንባታ ጉልህ ሚና ይጫወታል። ባለፈው አንድ አመት…
Read More
ብሔራዊ ባንክ የባንክ አካውንት ከብሔራዊ መታወቂያ ጋር እንዲያስተሳስሩ አሳሰበ

ብሔራዊ ባንክ የባንክ አካውንት ከብሔራዊ መታወቂያ ጋር እንዲያስተሳስሩ አሳሰበ

ባንኮች የከፈቷቸውን አካውንቶች በሁለት ሳምንት ውስጥ ከብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ጋር የማስተሳሰር ሥራ እንዲያጠናቅቁ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል። ብሔራዊ ባንክ እና የብሔራዊ መታወቂያ በጋራ ባወጡት አዲስ የአተገባበር ሥርዓት መሰረት የፋይናንስ ተቋማት ብሄራዊ ኦፕሬተር በሆነው ኢት-ስዊች በኩል ከብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ጋር የማስተሳሰር ሥራ መስራት መጀመራቸው ተገልጿል። እስካሁን 10 የሚሆኑ የፋይናንስ ተቋማት ከብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ጋር የማስተሳሰሩን ሥራ ጨርሰዋል ሲባል ሌሎች ባንኮች በሙከራ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ይለበስ አዲስ ለኢትዮ ነጋሪ እንደገለጹት ይህ አሰራር ባንኮች አገልግሎታቸው ቀልጣፋ እንዲሆንና ማዕከላዊ የመረጃ አያያዝ እንዲኖር ያስችላል ሲሉ ገልጸዋል። አክለውም ትስስሩ ባንኮች ከደንበኞቻቸው ጋር ያላቸውን አገልግሎት ያሳልጥላቸዋል፤ ወጪንም ይቆጥብላቸዋል ብለዋል፡፡ የኢት-ስዊች ቺፍ ፖርት ፎልዮ ኦፊሰር…
Read More
ብሔራዊ መታወቂያ ተመዝጋቢዎችን ወደ 63 ሚሊዮን ለማድረስ መታቀዱ ተገለጸ

ብሔራዊ መታወቂያ ተመዝጋቢዎችን ወደ 63 ሚሊዮን ለማድረስ መታቀዱ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ሚያዝያ 2015 ላይ ነበር ብሔራዊ መታወቂያ በሙከራ ደረጃ መመዝገብ የጀመረችው፡፡ በ29 ከተሞች የተጀመረው ይህ ፕሮግራም ከታህሳስ 2014 ጀምሮ ከ70 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን በብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባ ለማካሄድ በይፋ ተጀምሯል፡፡ ኢትዮ ነጋሪ ይህ የብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባ ምን እንደሚመስል በሀገሪቱ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ነዋሪዎችን እና ጉዳዩ የሚመለከታቸውን አካላትን አነጋግሯል፡፡ አቶ አማረ አሰፋ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማ ነዋሪ ናቸው፡፡ አጣዬ ከተማ ከሀገሪቱ ዋና ከተማ አዲስ አበባ በ300 ኪሎ ሜትር በሰሜን ኢትዮጵያ በኩል የምትገኝ ከተማ ናት፡፡ የድጅታል መታወቂያ ካሳለፈነው ሚያዝያ ወር ጀምሮ መሰጠት መጀመሩን ገልጸው ከሁለት ወር በፊት የድጅታል አይዲው ታትሞ እጃቸው እንደገባ ነግረውናል፡፡ አሁን ላይ በአጣዬ ከተማ ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች…
Read More