04
Nov
የሀገር መከላከያ ሰራዊት አዛዥ ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በሰሜን እዝ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ለማሰብ በሚል በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ህወሀትን ተችተዋል። ፊልድ ማርሻል በዚህ ጊዜ እንዳሉት መከላከያ ሠራዊት ሕይወቱን ከሰጠለት ሕዝብ ውስጥ የወጡ ጥቂት ካሃዲዎች ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ከኋላው መውጋታቸው ሕመሙ ጥልቅ ነው ብለዋል። በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈፀመው ክህደት ወንድም ወንዱሙ ላይ የፈፀመው ክህደት በመሆኑ በታሪክ ልዩ እንደሚያደርገውም ጠቅሰዋል። የትግራይ ሕዝብ በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመውን ክህደት አይቀበለውም ያሉት አዛዡ የትግራይ ሕዝብ በልጆቹ ክህደት አፍሮ፣ ተመልሰን መቐለ ስንገባ አጨብጭቦ ተቀብሎን ነበር ሲሉም አክለዋል። ስለዚህ ክህደት እና አስነዋሪ ታሪክ ስናውራ ስለ ጥቂት የሕወሓት አመራሮች እንጂ ስለ ትግራይ ሕዝብ እንዳልሆነም ገልጸዋል። የህወሀት…