Africa

ኢትዮጵያ በውጭ ሀገራት የሚሰማሩ ስራ ተቋራጭ ድርጅቶችን የማሳደግ እቅድ እንዳላት ተገለጸ

ኢትዮጵያ በውጭ ሀገራት የሚሰማሩ ስራ ተቋራጭ ድርጅቶችን የማሳደግ እቅድ እንዳላት ተገለጸ

10 የስራ ተቋራጭ ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ውጪ ውጪ ባሉ ሀገራት መሰማራታቸውን የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚንስቴር አስታውቋል ሚንስቴሩ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የተሰማሩ የኢትዮጵያ ስራ ተቋራጭ ድርጅቶችን ቁጥር 20 የማድረስ እቅድ መያዙን ገልጿል። የሀገራቱን አስፈላጊ መስፈርት አሟልተውና በጨረታ አሸንፈው በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ በኮንስትራክሽን ሥራዎች ላይ የሚሳተፉ ተቋራጮችን ቁጥር ወደ 20 ከፍ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል። የሚንስትሩ ሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኢትዮጵያ በዴቻ፤ "ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የግንባታ ሥራ ለማከናወን ፈቃድ ተሰጥቷቸው በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የኮንትራት ሥራዎችን ወስደው በግንባታ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የግንባታ ስራ ተቋራጮች ቁጥር ከ10 አይበልጥም" ብለዋል፡፡ በመሆኑም ሚኒስቴሩ ይህን የግንባታ ሥራ ተቋራጮች…
Read More
አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ሁለት ቋሚ ወንበር እንዲኖራት አሜሪካ ጠየቀች

አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ሁለት ቋሚ ወንበር እንዲኖራት አሜሪካ ጠየቀች

አሜሪካ አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት ድጋፍ እንደምታደርግ ገልጻለች፡፡  በተመድ የአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ በምክር ቤቱ አፍሪካ ሁለት ቋሚ መቀመጫዎች እና ትናንሽ የደሴት ሀገራት አንድ ተለዋዋጭ ወንበር እንዲያገኙ ግፊት እያደረግን ነው ብለዋል፡፡   ጀርመን፣ ህንድ እና ጃፓን በምክር ቤቱ ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራቸው እየጠየቁ ከሚገኙ ሀገራት መካከል ናቸው፡፡ አምባሳደሯ አፍሪካ ቋሚ ውክልና እንዲኖራት አሜሪካ እንደምትደግፍ ቢናገሩም ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት አሁን ላይ ከሚገኙት አምስት አባል ሀገራት ውጪ እንዲሰጥ ዋሽንግተን ፍላጎት እንደሌላት ገልጸዋል፡፡   በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት ከፍተኛ ስልጣን ባለው የጸጥታው ምክር ቤት ውክልና እንዲኖራቸው መጠየቅ ከጀመሩ አመታት ተቆጥረዋል፡፡ ለበርካታ ጊዜያት በዚህ ጉዳይ ተደጋጋሚ ድርድር ቢደረገም ውጤታማ…
Read More
የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው።

የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው።

የደቡብ አሜሪካዋ ብራዚል ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ለይፋዊ ጉብኝት ወደ አፍሪካ እንደሚመጡ ተገልጻል። እንደ ብራዚል ዜና አገልግሎት ዘገባ ከሆነ ፕሬዝዳንት ዳ ሲልቫ የካቲት 9 ቀን 2016 ዓ.ም ወደ አዲስ አዲስ አበባ ይመጣሉ። ፕሬዝዳንት ዳ ሲልቫ በአዲስ አበባ ቆይታቸው በ37ኛው የአፍሪካ ህብረት መሪዎች ጉባኤ ላይ እንደሚሳተፉም ተገልጿል። ፕሬዝዳንት ዳ ሲልቫ ከአዲስ አበባ በተጨማሪም በግብጽ ጉብኝት እንደሚያደርጉም ተገልጿል። ከአፍሪካ በመቀጠል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጥቁር ህዝቦች የሚኖሩባት ብራዚል ከአፍሪካ ጋር የሚያስተሳስራት ብዙ ታሪክ አላት። ፕሬዝዳንቱ ዳ ሲልቫ ስለ ጉብኝታቸው እንዳሉት "ብራዚል ከአፍሪካ ጋር ያለባትን የታሪክ እዳ መክፈል ትፈልጋለች" ብለዋል። ለሁለተኛ ጊዜ ወደ አፍሪካ የሚጓዙት ፕሬዝዳንት ሲልቫ ከዚህ በፊት በአንጎላ፣ ኬፕ ቩርዴ እንዲሁም በሳኦቶሜ…
Read More