ሳፋሪ ኮም ከብሔራዊ ባንክ የሞባይል ገንዘብ ዝውውር ፈቃድ እንደሚሰጠው ገለጸ

ብሔራዊ ባንክ ለሳፋሪኮም የሞባይል ገንዘብ ዝውውር በቅርቡ ፈቃድ እንደሚሰጥ አስታውቋል

በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የግል የቴሌኮም አገልግሎት ፈቃድ ላገኘው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ገንዘብ ዝውውር አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያስችለውን ፈቃድ በቅርቡ እንደሚሰጥ ብሔራዊ ባንክ ገልጿል።

የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ መጋቢት እንዳሉት መንግስት የፋይናንስ ዘርፉን ለማዘመንና ለማጠናከር  የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ ነው።

ከባንክ ውጭ የሆኑ የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያዎችን፣ ፊንቴክና የክፍያ ኤጀንቶችን የመሳሰሉ ተቋማት በክፍያ አገልግሎት ዘርፉ እንዲሳተፉ መደረጉንም ጠቅሰዋል።

ባንክ ገዢው አቶ ማሞ አክለውም በአገሪቱ የመጀመሪያው የግል የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢነት ፈቃድ አግኝቶ ሥራ የጀመረው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያስችለውን ፍቃድ በቅርቡ እንደሚያገኝ ተናግረዋል።

ይህም ዋና መቀጨውን በኬንያ ያደረገው ሳፋሪኮም በስፋት የሚታወቅበትን የኤም-ፔሳ የሞባይል ገንዘብ ዝውውርና ከፍያ አገልግሎት በኢትዮጵያ እንዲያስተዋውቅ ያስችለዋል።

ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ ከአንድ ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎቱን የጀመረ ሲሆን እስከ ቀጣዩ ሚያዝያ ድረስም በ25 የኢትዮጵያ ከተሞች አገልግሎቴን አስፋፋለሁ ብሏል።

አሁን ላይ ሙሉ ለሙሉ የመንግስት ንብረት የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም ቡቴሌ ብር በኩል የማባይል ገንዘብ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *