የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኮፐንሀገን ወደ አዲስ አበባ የካርጎ አገልግሎት ጀመረ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዴንማርክ ኮፐንሀገን ወደ አዲስ አበባ ሳምንታዊ የእቃ ጭነት አገልግሎት በረራ ጀመረ።
የእቃ ጭነት በረራው የሚደረገው በቅርቡ ከመንገደኛ ወደ እቃ ጭነት አገልግሎት በተቀየረው ቦይንግ 767-300F አውሮፕላን እንደሆነ ተገልጿል።
በዚህ ሳምንታዊ እያንዳንዱ በረራ እስከ 45 ቶን ያህል ጭነት እንደሚጓጓዝ አየር መንገዱ ለኢትዮ ነጋሪ ገልጿል።
ይህ አዲስ የእቃ ጭነት አገልግሎት በአውሮፓ እና በተቀረው ዓለም መካከል ያለውን የንግድ እንቅስቃሴ የሚያሳልጥ ይሆናል ተብሏል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመጪው ግንቦት ወር ጀምሮ ወደ ኮፐንሀገን የመንገደኛ በረራ አገልግሎት እጀምራለሁ ብሏል።
ይህ የመንገደኞች በረራ መጀመርም ተጨማሪ የካርጎ አገልግሎት አቅም ይፈጥርልኛል ብሏል።
ይህ በዚህ እንዳለ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኢንዶኔዢያ ዋና ከተማ ኩዋላላፑር ከተማ አዲስ በረራ እንደሚጀምር አስታውቋል።
አየር መንገዱ ከመጋቢት 24, 2023 ጀምሮ በሳምንት አራት ጊዜ ለመብረር ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል።