Tourist

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሁለት የውጭ ዜጎችን ጨምሮ ሶስት ሰዎች ተገደሉ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሁለት የውጭ ዜጎችን ጨምሮ ሶስት ሰዎች ተገደሉ

የክልሉ ኮሙንኬሽን ቢሮ ባወጣው መግለጫ በደቡብ ኦሞ ሱሪ ወረዳ በጉብኝት ላይ የነበሩ ሁለት የውጭ ዜጎችን ጨምሮ ሶስት ሰዎች ተገድለዋል። የተገደሉት ሰዎች ሁለቱ የቱርክ ዜግነት አላቸው የተባለ ሲሆን ሾፌራቸው ደግሞ ኢትዮጵያዊ እንደሆነ ተገልጿል። ግድያው ትናንት ጠዋት 2:20 ላይ እንደተፈጸመ የተገለጸ ሲሆን የገዳዮቹ ማንነት የአርብቶ አደር ሽፍቶች መሆናቸውን የክልሉ መንግሥት አስታውቋል። ገዳዮቹን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል የክልሉ ጸጥታ ሀይል እርምጃ መውሰድ ጀምሯልም ተብሏል። ሽፍቶቹ ግድያውን የፈጸሙት ለዝርፊያ በሚል እንደሆነም የክልሉ ኮሙንኬሽን ቢሮ ባወጣው መግለጫ ላይ ጠቅሷል። በርካታ ሀገራት ዜጎቻቸው በኢትዮጵያ ጉብኝት እንዳያደርጉ የጉዞ እገዳ እና ማስጠንቀቂያዎችን ማውጣታቸው ይታወሳል። ለአብነትም ካናዳ እና ብሪታንያ ከወራት በፊት ዜጎቻቸውን ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ አልያም ከተጓዙ በሚል ልዩ…
Read More
ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ከውጭ ጎብኚዎች ሁለት ቢሊዮን ዶላር ማግኘቷ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ከውጭ ጎብኚዎች ሁለት ቢሊዮን ዶላር ማግኘቷ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ከውጭ ጎብኚዎች ሁለት ቢሊዮን ዶላር ማግኘቷ ተገለጸ ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ከሀገር ውስጥ ጎብኚዎች 44 ቢሊዮን ብር አግኝታለች። እንዲሁም ከውጭ ሀገራት ጎብኚዎች ደግሞ 2 ቢሊዮን ዶላር ማግኘቷ ተገልጿል ። የቱሪዝም ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በተያዘው በጀት ዓመት 6 ወራት ውስጥ ኢትዮጵያ በ504,840 በሚሆኑ የውጭ ቱሪስቶች ተጎብኝታለች። ከነዚህ ጎብኚዎችም ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷን ሚንስቴሩ ጠቅሷል። ቱሪስቶች፤ ለተለያዩ ዓለም አቀፍ ኮንፍረንሶች የተገኙ ተሳታፊዎችና የቢዝነስ ሰዎችም በዚህ ሪፖርት ተካተዋል። በአዲስ አበባ የቱሪስት ቆይታም በአማካይ ከ5 እስከ 6 ቀናት እንደሆነም በሪፖርቱ ተጠቅሷል። ከሀገር ውስጥ ጎብኝዎችም 44 ቢሊዮን ብር መገኘቱ የተገለጸ ሲሆን ይህም ሚኒስቴሩ ካስቀመጠው 32.9 ቢሊዮን ብር እቅድ…
Read More