Somali

ኢትዮጵያ በዓመት 111 ሚሊዮን ሊትር የሚያመርት የጋዝ ማጣሪያ አስመረቀች

ኢትዮጵያ በዓመት 111 ሚሊዮን ሊትር የሚያመርት የጋዝ ማጣሪያ አስመረቀች

በዓመት 111 ሚሊየን ሊትር የሚያመርተው የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት ተመርቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሶማሌ ክልል ካሉብ በዓመት 111 ሚሊየን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር መርቀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ እንዳሉት በሶማሌ ክልል ካሉብ በዓመት 111 ሚሊየን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር መርቀናል ብለዋል። በተመሳሳይ በዓመት 1 ነጥብ 33 ቢሊየን ሊትር የማምረት አቅም የሚኖረውን ሁለተኛውን የነዳጅ ማጣሪያ ስራ ማስጀመራቸውንም ገልጸዋል፡፡ ማጣሪያው ከፈሳሽ ተፈጥሮ ጋዝ ምርት ባሻገር በኃይል ማመንጫ ዘርፉም 1 ሺህ ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም በመያዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡ ከሁሉም በላይ ፕሮጀክቱ የጋዝ ማምረቻ ብቻ…
Read More
በሶማሊ ክልል ጎዴ የአፈር ማዳበሪያ እና ነዳጅ ማጣሪያ ግንባታ ተጀመረ

በሶማሊ ክልል ጎዴ የአፈር ማዳበሪያ እና ነዳጅ ማጣሪያ ግንባታ ተጀመረ

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የዩሪያ ማዳበሪያ እና ጌዴ ነዳጅ ማጣሪያ ግንባታን አስጀምረዋል። የዩሪያ አፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና ዳንጎቴ ግሩፕ ጋር በመተባበር ይገነባል ተብሏል። ጎልደን ኮንኮርድ ግሩፕ ደግሞ የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካን እንደሚገነባ ጠቅላይ ሚንስትሩ ገልጸዋል። የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ከሂላል የነዳጅ ስፍራ ድፍድፍ ነዳጅ በማውጣት፣ በማጣራትና በማጠራቀም በአመት 3.5 ሚሊዮን ቶን የማምረት አቅም አለውም ተብሏል። በሌላ በኩልም የማዳበሪያ ፋብሪካው ከካሉብ የጋዝ ስፍራ በማውጣት እና 108 ኪሎሜትር የማጓጓዣ ቱቦ በመጠቀም በአመት 3 ሚሊዮን ቶን አምርቶ ያቀርባል። ከአንድ ወር በፊት አሊኮ ዳንጎቴ ግሩፕ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ጋር የአፈር ማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክስ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡ ፕሮጀክቱ በዓመት እስከ ሦስት ሚሊዮን ሜትሪክ…
Read More
ኦብነግ ከሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተሳትፎ ራሱን አገለለ

ኦብነግ ከሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተሳትፎ ራሱን አገለለ

የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ከሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተሳትፎ እራሱን ማግለሉን አስታወቀ  የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ድርጅት አሳታፊነትና ግልጸኝነት ስላላየሁበት ከአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተሳታፊነት እራሴን አግልያለሁ ሲል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ በሱማሌ ክልል የገዢው ፓርቲ መዋቅር ተሳታፊዎችን የሚለይበትና የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ድምጽ የሚያፍንበት ህገ-ወጥ  አሰራር መዘርጋቱን የሚገልጸው ፓርቲው በዚህ ሂደት ውስጥ በምክክር መሳተፍ ረብ የለሽ ነው ሲልም ገልጿል፡፡ ይህ አግላይ አሰራር አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተቋቋመበትን አላማ የሚጥስ ነው ሲልም በምክክር ኮሚሽኑ ሂደት ላይ ጥያቄ አንስቷል፡፡ ፓርቲው ከሱማሌ ክልል ውጪ በአማራና ኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳሱ የታጠቁ ሃይሎች ባልተሳተፉበት ሁኔታ እንዴት የምክክር ሂደቱ ሊሳካ ይችላል ሲልም በጥያቄ መልስ አንስቷል፡፡ በቀጣይም ሁሉን አቀፍ የድርድር መድረክ እስካልተዘጋጀ…
Read More
ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ የቀረበባትን ክስ ውድቅ አደረገች

ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ የቀረበባትን ክስ ውድቅ አደረገች

ሶማሊላንድ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ልዩ ኃይሎች ድንበር አልፈው በሶሎ ግዛት ላስአኖድ ከተማ ጦርነት ውስጥ እየተሳተፉ ነው ስትል ክስ አቅርባ ነበር። በፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የሚመራው የሶማሌላንድ ካቢኔ ባወጣው መግለጫ ግጭት ባለባት ላስአኖድ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ኃይሎች በተጨማሪ የሶማሊያ እና የፑንትላንድ ወታደሮች ይገኛሉ ብሏል፡፡ ካቢኔው የሶማሌ ላንድን ዓለም አቀፋዊ ድንበር አልፈው ገብተዋል ያላቸው እነዚህ ኃይሎች ከአካባቢው እንዲወጡም አሳስቧል።  ለሶማሊላንድ ክስ ምላሽ የሰጠው የሶማሌ ክልል መንግስት በላሳኖድ ከተማ በሚካሄደው ጦርነት አንድም የሶማሌ ክልል ኃይል አባል የለም ያለ ሲሆን፣ መግለጫውንም ኃላፊነት የጎደለው ውንጀላ እንደሆነ ገልጿል፡፡ በጉዳዩ ላይ የተናገሩት የሶማሌ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ዐብዱልቃድር ረሺድ ‹‹እኛ የሌላ ሀገር ፖለቲካ ውስጥ እጅ…
Read More