KRC

የቱርኩ ኬአርሲ ኩባንያ በኢትዮጵያ የአሳንስር ፋብሪካ ለመክፈት ተስማማ

የቱርኩ ኬአርሲ ኩባንያ በኢትዮጵያ የአሳንስር ፋብሪካ ለመክፈት ተስማማ

በኢትዮጵያ 10 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚያርፍ የአሳንሰር ማምረቻ ፋብሪካ ለመገንባት የሚያስችል የጋራ ኢንቨስትመንት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ስምምነት ተፈርሟል። ስምምነቱን የተፈራረሙት ሀገር በቀሉ ሞናጎ ኢሊቬተር እና የቱርኩ ኬ አር ሲ ኢሊቬተር መሆናቸው ተገልጿል። ሁለቱ ኩባንያዎች ላለፉት 5 ዓመታት በዘርፉ አብረው ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ በዱከም ከተማ ማምረቻ ፋብሪካ በጋራ ለመገንባት የሚያስችላቸውን ስምምነት ፈጽመዋል። የ"ሞናጎ" ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋሁን ኢሳያስ እንዳስታወቁት፣ ፕሮጀክቱ በዋናነት በሀገሪቱ በሚገኙ ህንጻዎች ላይ የሚታየውን የአሳንሰር ጥገና እና የመለዋወጫ አቅርቦት እጥረት ለመፍታት ያለመ ነው። በጨረታ የሚገዙ አሳንሰሮች ከሽያጭ በኋላ በቂ የጥገና አገልግሎት እና የመለዋወጫ አቅርቦት ስለማያገኙ በተደጋጋሚ ብልሽት እንደሚያጋጥማቸው ተመላክቷል። አዲሱ ስምምነት ይህንን ክፍተት እንደሚሞላው የጠቆሙት…
Read More