20
Nov
የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት እንደገለጸው ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ወደ አገር ውስጥ ሊገቡ ሲሉ ከ3 ሺህ 400 በላይ የውጭ አገር ዜጎች መያዛቸውን ጠቁሟል፡፡ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት የሶት ወራት ሪፖርት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡ ዳይሬክተሯ በዚህ ጊዜ እንዳሉት ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ከ3 ሺህ 400 በላይ የውጭ አገር ዜጎች ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ ሲሉ መያዛቸውን ገልጸዋል፡፡ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ የነበሩት የውጭ ዜጎች ቪዛ ሳያገኙ ለመግባት ሲሞክሩ፣ ህገወጥ የጉዞ ሰነድ ይዞ መገኘት እና መሰል ህገወጥ ድርጊቶችን ለመፈጸም ሲሞክሩ እንደነበር ተገልጿል፡፡ እንዲሁም ከ1 ሺህ 500 በላይ ዜጎች ከሀገር ሊወጡ ሲሉ ተይዘዋል የተባለ ሲሆን ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ በሀገር ውስጥ ቆይተው…