05
Nov
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በስልክ መወያየታቸው ተገልጿል። “በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ያሉ የእርስ በርስ ግጭቶች እልባት እንዲያገኙ የፖለቲካ ውይይት ወሳኝነት አለው” ሲሉ አንቶኒ ብሊንከን ከጠ/ሚኒስትር አብይ ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት ወቅት መናገራቸው የመስሪያ ቤታቸው መግለጫ አመላክቷል። አሜሪካ “በአማራ ክልል በመካሄድ ላይ ያለው ግጭት ያሳስባታል” ሲሉ መናገራቸውን በመግለጫው ላይ ተገልጿል። አንቶኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር በስልክ ያወሩት በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ዙሪያ እንደነበር ጸ/ቤታቸው ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። አንቶኒ ብሊንከን “ኢትዮጵያ የሰላም ስምምነቱ ተግባራዊ እንዲደረግ ለምታደርገው ጥረት ሀገራቸው እገዛ ለማድረግ ዝግጁ ናት” ሲሉ መናገራቸውን መግለጫው ጠቁሟል። የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር…