10
Jun
የገንዘብ ሚንስትር አሕመድ ሽዴ፣ ለ2018 በጀት ዓመት 1 ነጥብ 93 ትሪሊዮን ብር ወይም 14 ቢሊዮን ዶላር ረቂቅ የፌደራል በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል። ረቂቅ በጀቱ እየተጠናቀቀ ካለው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ31 በመቶ ብልጫ ያለው ነው። ከቀረበው ረቂቅ በጀቱ ውስጥ 1 ነጥብ 2 ትሪሊዮኑ ለመደበኛ ወጪ፣ 415 ቢሊዮኑ ለካፒታል ወጪ፣ 315 ቢሊዮኑ ለክልሎች ድጎማና 14 ቢሊዮኑ ለክልሎች የዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ እንዲውል መመደቡን ሚንስትሩ አብራርተዋል። ከጥቅል አገራዊ ምርት አንጻር 2 ነጥብ 2 በመቶ ያልተጣራ የበጀት ጉድለት ያጋጥማል ተብሎ እንደሚጠበቅና ኾኖም መንግሥት ጉድለቱን ለመሙላት ከብሄራዊ ባንክ ብድር እንደማይበደር ተገልጧል። ይህ በዚህ እንዳለ መንግስት ከያዘው በጀት አንድ ሶስተኛውን ለእዳ ክፍያ መያዙ…