ኢትዮጵያ ከማልዴቪስ ጋር የአቪዬሽን ስምምነት ተፈራረመች

ኢትዮጵያና ማልዲቭስ የሁለትዮሽ የአየር አገልግሎት ስምምነት ተፈራርመዋል።

በኢትዮጵያ እና በማልዲቭስ ሲቪል አቪዬሽን ቦርድ መካከል ከሀምሌ 12-14 2018 በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

ውይይቱን ተከትሎም የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሐንስ አበራ እና የማልዲቭስ ሪፐብሊክ የቱሪዝምና ሲቪል አቪዬሽን ሚኒስትር መሀመድ አሚን የሁለትዮሽ አቪዬሽን ስምምነቱን ተፈራርመዋል።

በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሐንስ አበራ ጋር የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የኢኮኖሚ ሬጉሌሽን ዳይሬክተር አቶ ናርዶስ በድሉ፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የስትራቴጂክ አሊያንስ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የኢንተርናሽናል አሊያንስ ዳይሬክተር ተገኝተዋል።

ይህ ስምምነት በኢትዮጵያና በማልዲቭስ መካከል ቀጥተኛ የአየር ትስስር እንዲጀመር የሚያስችል ሲሆን ለኢትዮጵያ አየር መንገድ በአምስተኛ የአየር ነፃነት መብት ተጠቅሞ በማልዲቭስ በኩል ወደ ኮሎምቦ፣ ፐርዝ፣ ሲድኒ፣ ሲንጋፖር፣ ኳላላምፑር፣ ባንኮክ፣ ጃካርታ፣ ክራይስትቸርች፣ ኦክላንድ እና ዌሊንግተን የአየር አገልግሎት የማከናወን ዕድል የሚፈጥር ነው ተብሏል።

ይህም የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዘርፍ ዓለም አቀፍ ተደራሽነትን በማስፋት፣ የንግድ፣ የቱሪዝም እና የኢኮኖሚ ትስስርን የበለጠ ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል።

ስምምነቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል የንግድ፣ የቱሪዝም፣ የኢንቨስትመንት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማጠናከር በአቪዬሽን ዘርፍ የሚኖረውን ትብብር ወደ ከፍተኛ ደረጃ ያሳድጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት ጋር የአቪዬሽን ስምምነቶችን የምትፈጽም ሲሆን ይህም ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀጥታ እና ትራንዚት በረራዎችን ለማድረግ ጠቅመውታል።

ማልዴቪስ በዓለም ጎብኚዎች ተመራጭ ሀገር ስትሆን ቱሪዝም ደግሞ ዋነኛ የኢኮኖሚ ምንጭ ነው። የአሁኑ የአቪዬሽን ስምምነትም ለኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የበረራ እድል እንደሚከፍት ይጠበቃል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *