Maldevis

ኢትዮጵያ ከማልዴቪስ ጋር የአቪዬሽን ስምምነት ተፈራረመች

ኢትዮጵያ ከማልዴቪስ ጋር የአቪዬሽን ስምምነት ተፈራረመች

ኢትዮጵያና ማልዲቭስ የሁለትዮሽ የአየር አገልግሎት ስምምነት ተፈራርመዋል። በኢትዮጵያ እና በማልዲቭስ ሲቪል አቪዬሽን ቦርድ መካከል ከሀምሌ 12-14 2018 በአዲስ አበባ ተካሂዷል። ውይይቱን ተከትሎም የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሐንስ አበራ እና የማልዲቭስ ሪፐብሊክ የቱሪዝምና ሲቪል አቪዬሽን ሚኒስትር መሀመድ አሚን የሁለትዮሽ አቪዬሽን ስምምነቱን ተፈራርመዋል። በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሐንስ አበራ ጋር የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የኢኮኖሚ ሬጉሌሽን ዳይሬክተር አቶ ናርዶስ በድሉ፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የስትራቴጂክ አሊያንስ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የኢንተርናሽናል አሊያንስ ዳይሬክተር ተገኝተዋል። ይህ ስምምነት በኢትዮጵያና በማልዲቭስ መካከል ቀጥተኛ የአየር ትስስር እንዲጀመር የሚያስችል ሲሆን ለኢትዮጵያ አየር መንገድ በአምስተኛ የአየር ነፃነት መብት ተጠቅሞ በማልዲቭስ በኩል ወደ…
Read More