በህገወጥ መንገድ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ዱባይ ሲልክ የነበረው ሰው በ20 ዓመት እስራት ተቀጣ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ወረዳ  ቢቂላ ከተማ ውስጥ ነዋሪ የሆነው ግለሠብ ከሚመለከተው አካል እውቅና ፈቃድ ሣያገኝ ሰዎችን ወደ ዱባይ የሚልከው ግለሠብ በእስራት መቀጣቱን ፖሊስ አስታዉቋል።

የምዕራብ አርሲ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ሐላፊ ዋና ኢንስፔክተር ከድር ጅቦ እንደተናገሩት ተከሣሽ ገመቹ  ሰይድ የተባለው ግለሠብ ከሚመለከተው አካል እውቅና ፈቃድ ሣይኖረው  በዶዶላ ወረዳ ቢቂላ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ሁለት ግለሠቦችን ከፍተኛ የስራ ልምድና ችሎታ  ስላላችሁ ስራ የማግኘት እድላችሁ ሰፊ ነው በማለት የማታለያ ቃል በመጠቀም ወደ ዱባይ እንደላካቸው ገልፀዋል።

ተከሣሹ የተለያዩ  አሣማኝና  ማታለያ ቃላቶችን በመጠቀም ከሁለቱ ግለሠቦች 250 ብር በአጠቃላይ 500 ሺህ ብር በመቀበል ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬት ዱባይ ከተማ የላካቸው መሆኑ ተገልጿል።

ወደ ዱባይ የተጓዙ ሑለቱ ግለሠቦችም ዱባይ ሲደርሱ  ቃል እንደተገባላቸው ስራ ሳያገኙ በመቆየት በዱባይ ፖሊስ በኩል በሕገወጥ መንገድ ወደ ሐገር ውስጥ በመግባት ወንጀል ለወራት ታስረው  ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱ መሆኑን ገልፀዋል።

የግል ተበዳዮችም ሀገር ውስጥ ከገቡ በኃላ ፣ የደረሠባቸውን በደልና እንግልት ለፖሊስ አመልክተው ተከሣሹ በቁጥጥር ስር ዉሏል።

ፖሊስም በቁጥጥር ስር በዋለው ግለሠብ ላይ ባደረገው የወንጀል ምርመራ በማስረጃ በማጠናከር የምርመራ መዝገቡን ለአቃቢ ሕግ የላከ ሲሆን አቃቢ ሕግም ከፖሊስ የቀረበው የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በሕገወጥ የሠዎች ዝውውር እና ድንበር የማሻገር እንዲሁም ከሚመለከተው አካል እውቅና እና ፈቃድ ሣያገኝ ሠዎችን ወደ ውጭ በመላክ ወንጀል ክስ መስርቶበታል፡፡

በአቃቢ ሕግ የተመሠረተውን ክስ ሲከታተል የቆየው የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥር 1 ቀን 2018 ዓም በዋለው ችሎት ተከሣሽ ገመቹ ሰይድ በተከሠሠበት ወንጀል ጥፋተኛ በመባሉ በ20 ዓመት እስራት ወስኖበታል ዚል የዞኑ ፖሊስ አስታውቋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *