ታላቁ የህዳሴ ግድብ በቀጣዮቹ ስድስት ወራት ውስጥ ይጠናቃል ተባለ

ከ15 ዓመት በፊት በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ግንባታው የተጀመረው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴው ግድብ በያዝነው ዓመት እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ላይ ናቸው።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ከህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባላት ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ውቅት እንዳሉት ህዳሴ ግድብን ከ6 ወር በኋላ እንመርቃለን ብለዋል፡፡

መንግስት ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ከግብፅ መንግስት ጋር በተለይም ከደህንነት መስሪያ ቤት ጋር ህዳሴን በተመለከተ ውይይት አድርገናል የተለያዩ ሃሳቦችም በህዳሴ ግድብ ዙሪያ አቅርበናል ብለዋል፡፡

መንግስት በህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ከግብፅ ጋር ለመነጋገርና ለመወያየት ዝግጁ ነው ሲሉ ጠቅሰዋል::

የግድቡ ግንባታ ከተጀመረ 15 ዓመታት ሊሞሉት አንድ ሳምንት ብቻ ቀርቶታል።

ከ14 ዓመት በፊት ለግንባታው መሰረት ድንጋይ ሲጣል 80 ቢሊዮን ብር ያስፈልገዋል ተብሎ የተጀመረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ፤ ግንባታው 97.6 በመቶ እንደደረሰና ጥቂት የማጠናቀቂያ ስራዎች ብቻ እንደቀሩት  የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ የፕሮጀክት ፅህፈት ቤት ተናግሯል፡፡

ህዝቡ እስካሁን ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ ለግድቡ ግንባታ በበጎ ፈቃደኝነት ያዋጣ ሲሆን በዚህ ዓመት 1.6 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በሚያመነጨው የኤሌክትሪክ ሀይል መጠን ከአፍሪካ ግዙፉ ፕሮጀክት የሆነው የህዳሴው ግድብ በአሁኑ ወቅት በሁለት ተርባይኖች 540 ሜጋ ዋት በማመንጨት ላይ ይገኛል፡፡

አሁን ላይ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ እየተመረተ ያለው ኤሌትሪክ ኃይል በ2 ተርባይኖች 540 ሜጋ ዋት ሲሆን ግድቡ ሲጠናቀቅ የሚያመርተው ኤሌክትሪክ ኃይል 5ሺ 150 ሜጋ ዋት ይደርሳል፡፡

አሁን ላይ ግድቡ የያዘው የውሃ መጠን 42 ቢሊዮን ሜትር ኪዉብ ሲሆን ግድቡ ሲጠናቀቅ የሚይዘው ውሃ መጠን ወደ 74 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ከፍ ይላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የህዳሴው ግድብ ግንባታው ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከ180 በላይ ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ሲሆን ቀሪ ግንባታውን ለማጠናቀቅ 80 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

የህዳሴው ግድብ በሚቀጥለው ዓመት ሙሉ ለሙሉ ይጠናቀቃል የተባለ ሲሆን አሁን ላይ ከ40 ቢሊዮን በላይ ሜትር ኪዩብ ውሀ በግድቡ ውስጥ ይገኛል ተብሏል።

በሀይል ማመንጨት ከአፍሪካ ትልቁ ግድብ የሆነው የሕዳሴው ግድብ በአጠቃላይ ሀይል የሚያመነጩ ሰባት ዩኒቶች ይኖሩታል ተብሏል።

ግብጽ እና ሱዳን ኢትዮጵያ በአባይ (ናይል) ወንዝ ላይ እየገነባችው ያለውን ግድብ የግድቡ ግንባታ ይፋ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ እየተቃወሙ ሲሆን ላለፉት 13 ዓመታት የተደረጉ የሶስትዮሽ ድርድር ያለ ውጤት ተጠናቀዋል፡፡

ግብጽ ለሶስትዮሽ ድርደሩ ኢትዮጵያን ተጠያቂ ስታደርግ ኢትዮጵያ በበኩሏ ግብጽ በቅኝ ግዛት ዘመን የነበሩ ውሎች እንዲቀጥሉ ስለምትፈልግ እንዳልተሳካ አሳውቃለች፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *