የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ከመጪው ወር ጀምሮ በመላው ኢትዮጵያ የምግብ እርዳታ አጀምራለሁ ብሏል፡፡
የአሜሪካ መንግስት የዓለም አቀፍ ልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) ካሳለፍነው ሰኔ ወር ጀምሮ በምግብ እርዳታ ስርቆት ምክንያት እርዳታ መስጠቱን ማቆሙ ይታወሳል፡፡
በለጋሾች የተገዛ የምግብ እርዳታ ለገበያ መቅረቡና ወደ ውጪ አገራት ጭምር መላኩን የጠቀሰው የተራድኦ ድርጅቱ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የእርዳታ ስርጭቱን በተመለከተ ተከታታይ ውይይት ማድረጉን ገልጿል።
በዚህም ባለፈው ወር በሀገሪቱ ለሚገኙ ስደተኞች የምግብ እርዳታ ማቅረብ የጀመረ ሲሆን ከመጪው ወር ጀምሮ ደግሞ በመላው ኢትዮጵያ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች እርዳታ ማቅረብ እንደሚጀምር ገልጿል።
ኢትዮጵያ የምግብ ድጋፍ ስርጭት ስርአቷን በመሰረታዊነት የሚያስተካክል ስራ መከወኗንና ለጋሽ ድርጅቶች እርዳታው ለተገቢው አካል መድረሱን እንዲከታተሉ መስማማቷን ድርጅቱ አስታውቋል።
ለጋሽ ድርጅቶች በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ጫና ሳይደረግባቸው እርዳታ ለሚገባው ወገን መድረሱን ማረጋገጥ እንዲችሉ መፍቀዷንም ነው የዩኤስኤይድ መግለጫ ያመላከተው።
በ30 ዓመታት ታይቶ አይታወቅም በተባለ ድርቅና በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በኢትዮጵያ ከ20 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።
ኢትዮጵያ ከሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ኤርትራ እና ሌሎች ሀገራት የተውጣጡ ከ850 ሺህ በላይ ስደተኞችን ያስጠለለች ሲሆን 100 ሺህ ሱዳናውያን ጦርነትን ሽሽት ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል።
የአለም ምግብ ፕሮግራምና የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ተራድኦ ድርጅት በእርዳታ ስርቆት ምክንያት ድጋፍ አቋርጠው መቆየታቸውም ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ሲነገር ቆይቷል።
የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚሊዮኖች ከፍተኛውን ሰብአዊ እርዳታ በማቅረብ ከሌሎች አገራት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መካከል ዋነኛው መሆኑ ይታወቃል።
ከአንድ ወር በፊት በኢትዮጵያ ለተጠለሉ ስደተኞች እርዳታ መሰጠት የጀመረ ሲሆን ኢትዮጵያ በእርዳታ ስርጭት እና መጋዝን ጉዳዮች ላይ ጣልቃ እንደማትገባ ከስምምነት ደርሳለች፡፡
በአማራ፣አፋር፣ ትግራይ እና ኦሮሚያ ክልሎች ባለው አለመረጋጋት ምክንያት ከመኖሪያ ቤታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች በየጊዜው እየጨመረ ይገኛል፡፡
በተለይም በአማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግስት የጸጽታ ሀይሎች መካከል አዲስ ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ ዜጎች ከመኖሪያ ቤታቸው በመፈናቀል ላይ ናቸው፡፡
በህዝብ ብዛት እና በቆዳ ስፋቱ ከሀገሪቱ ሁሉም ክልሎች ሁለተኛው የሆነው የአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት ከአምስት ወራት በፊት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆ ኢንተርኔትም ተቋርጧል፡፡
መንግስት በአማራ ክልል ያለው የጸጽታ ሁኔታ በመሻሻል ላይ ነው ቢልም አሁንም የክልሉ በርካታ ቦታዎች በፋኖ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ይገኛል፡፡
I needed to thank you for this excellent read!! I certainly enjoyed every little bit of it. I have got you saved as a favorite to check out new things you postÖ
I don’t even know the way I finished up right here, however I
believed this post used to be great. I do not know who you are but certainly you’re going to a famous blogger in case you aren’t already.
Cheers!