የኤርትራ የጦር ጀነራሎችና መኮንኖች ኢትዮጵያን ጎበኙ

የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት የጦር ጀነራሎች እና ከፍተኛ የጦር አመራር መኮንኖች በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገዋል።

ኤርትራ ወታደራዊ ልኡክ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ዓቅም እና እየተከናወኑ ያሉ የምርምር እና ልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና፤ ኢንስቲትዩቱ እያከናወናቸው ባሉ የቴክኖሎጂ ሥራዎች ዙሪያ ለቡድኑ አባላት ገለጻ ማድረጋቸውን ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል፡፡

የኤርትራ የጦር ጀነራሎች እና ከፍተኛ የጦሩ አመራሮች ቡድን አስተባባሪ ጀነራል አብርሃ ካሳ፤ በኢንስቲትዩቱ ያደረጉት ጉብኝት ለአገራቸው ብዙ ልምድ የቀሰሙበት መሆኑን መናገራቸው ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በቴክኖሎጂው ዘርፍም አብረው መስራት የሚያስችላቸው እድል ስለመኖሩም የተገነዘቡበት ጉብኝት መሆኑን መጠቆማቸውም ተመላክቷል፡፡

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ከ20 ዓመት በፊት ወደ ደም አፋሳሽ ጦርነት ገብተው ከሁለቱም ወገን 200 ሺህ ዜጎች ህይወታቸው አልፏል።

ሁለቱ ሀገራት ከአምስት ዓመት በፊት ከቆዩበት ሰላም እና ጦርነት አልባ ግንኙነት ወጥተው ወደ ሰላማዊ ግንኙነት ገብተዋል።

ህወሀት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሲጀመር የኤርትራ ጦር ወደ በመግባት ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጎን ሆኖ ሲዋጋ ቆይቷል።

የፌደራል መንግሥት እና ህወሀት በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በደቡብ አፍሪካ የሰላም ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ የኤርትራ ጦር ኢትዮጵያን ለቆ ወጥቷል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *