03
Nov
አምስት ፓርቲዎች የመሰረቱት 'ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት' የተሰኘው ቅንጅት፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸሙት ጥቃቶች እንዲመረመሩ ለዓለማቀፉ ማሕበረሰብ ጥሪ አቅርቧል፡፡ ቅንጅቱ በቅርቡ በአርሲ የተፈጸመውን ግድያ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤“ በኢትዮጵያ የሚፈጸሙት ማንነትና ሃይማኖት ተኮር ጥቃቶች መንግሥታዊ መዋቅርን የተከተሉ፣ ሥርዓታዊና ተጨማሪ እጅ ያለበት ስለመኾኑ ምርመራ እንዲደረግ ” ጥሪውን አቅርቧል። ቅንጅቱ፤ “ጠያቂም ተጠያቂም ባለመኖሩ መግደል ቀላል ኾኗል” በሚል ያወጣው መግለጫ፤ “ እንዲህ ዓይነቱን ግዙፍ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት" በጽኑ እንደሚያወግዝ አስታውቆ፣ "እልቂት የየቀን ገጠመኙ ለኾነው የአካባቢው ማኅበረሰብም" ብርታትና መጽናናትን ተመኝቷል። መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት ፓርቲ (ኢሕአፓ)፣ እናት ፓርቲ፣ አዲሲ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አኢዴፓ) እና አማራ ግዮን ንቅናቄ ( አግን) የመሠረቱት ' ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት…