Remittance

ኢትዮጵያ 78 በመቶ የሬሚታንስ ገቢዋን እንደምታጣ ተገለጸ

ኢትዮጵያ 78 በመቶ የሬሚታንስ ገቢዋን እንደምታጣ ተገለጸ

ሀገሪቱ ከሬሚታንስ ገቢ 35 ቢሊዮን ዶላር ገቢ የማግኘት አቅም እንዳላት ተገልጿል ኢትዮጵያ ከውጭ ሀገራት በሕጋዊ መንገድ ከሚላክላት ገንዘብ (ሬሚታንስ) የምታገኘው ገቢ የሀገሪቱን አቅም 22 በመቶ ብቻ መሆኑ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ በተለያዩ ሀገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች ጋር በመወያየት ላይ ናቸው፡፡ ከዚህ በፊት በተባበሩት አረብ ኢምሬት እና ሳውዲ አረቢያ ከተሞች ከኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች ጋር የተወያዩት ፕሬዝዳንቱ አሁን ደግሞ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ከተማ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያይተዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ በዚህ ጊዜ እንዳሉት ኢትዮጵያ ከሬሚታንስ ገቢ እየተገኘች ያለው ገቢ 7.2 ቢሊየን ዶላር ብቻ ነዉ ብለዋል። አቶ አቤ ሳኖ እንዳስረዱት፣ አሁን ካለው የገንዘብ ፍሰት ቀሪው 78 በመቶ የሚሆነው ወደ ሀገር…
Read More
ንግድ ባንክ ለዲያስፖራዎች 50 ቢሊዮን ብር ብድር ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ገለጸ

ንግድ ባንክ ለዲያስፖራዎች 50 ቢሊዮን ብር ብድር ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ገለጸ

ንግድ ባንክ ለዲያስፖራው ማኀበረሰብ 50 ቢሊዮን ብር የብድር አገልግሎት አዘጋጅቼ እየጠበቀ መሆኑን አስታውቋል። የባንኩ የብድር አገልግሎቱ ለኢንቨስትመንት፣ ለመኖሪያ ቤትና አውቶሞቢል ግዥ የቀረበ ነው ተብሏል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚደንት አቶ አቤ ሳኖ ሰሞኑን በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን  የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይቱ ወቅት ፕሬዚደንቱ እንዳስታወቁት ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን  የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በአገር ውስጥ ለሚያካሄዱት የቢዝነስ እንቅስቃሴ፣ ለመኖሪያ ቤትና መሰል ፍላጎቶች የ50 ቢሊዮን ብር የብድር አገልገሎት ተመቻችቷል ብለዋል፡፡ የብድር አገልግሎቱ በተያዘው የ2024/25 በጀት ዓመት ተፈጻሚ እንደሚሆንም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡ ባንኩ አገልግሎቱን ለማግኘት ጥያቄ ለሚያቀርቡ የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ቀልጣፋና ምቹ አሰራር እንደሚተገብርም አቶ አቤ አስታውቀዋል፡፡ ሙሉ ለሙሉ የመንግስት…
Read More