NDC

ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የምክክር ሂደቱ ላይ የተነሱበትን ቅሬታዎች ውድቅ አደረገ

ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የምክክር ሂደቱ ላይ የተነሱበትን ቅሬታዎች ውድቅ አደረገ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የምክክር ሂደቱን «ተዓማኒነት»፣ «አካታችነት»፣ «ገለልተኝነት» እና «ፍትሐዊነት» ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ ተደጋጋሚና የተደራጁ ጥፋቶች ተፈጽመዋል በሚል ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምላሽ ሰጥቷል። ኮሚሽኑ አብን ነሀሴ 08 ቀን 2019 ዓ.ም ላወጣው መግለጫ በሰጠው ምላሽ፣ ፓርቲው ሂደቱ «አካታች» እና «አሳታፊ» አይደለም በሚል ያቀረበውን መግለጫ መመርመሩንና ማጣራቱን ገልጾ፣ የፓርቲውን ድምዳሜ እንደማይቀበለው ይፋ አድርጓል። ፓርቲው ወደ ምክክሩ የገባው ችግሮች በኃይል ሳይሆን በውይይት፣ በጫና ሳይሆን በመደማመጥ፣ በአንድ ወገን የበላይነት ሳይሆን በጋራ መግባባት፣ እንዲሁም ሁሉም አሸናፊ በሚሆንበት ሰጥቶ የመቀበል መርህ እንደነበር በመግለጫው አስታውሷል። ሆኖም በሂደቱ ውስጥ ከተራ የአሰራር ግድፈት የተለየ ሁኔታ መመልከቱን የዘረዘረው አብን፣ ሂደቱን ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ ተዓማኒነትን፣ አካታችነትንና ፍትሐዊነትን…
Read More
ኢትዮጵያ በፕሬዝዳንት እንድትመራ ስምምነት ላይ መደረሱ ተገለጸ

ኢትዮጵያ በፕሬዝዳንት እንድትመራ ስምምነት ላይ መደረሱ ተገለጸ

ኢትዮጵያ በፕሬዚዳንት እንድትመራ በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ ተመካካሪዎች መግባባት መደረሳቸው ተሰምቷል። ይሁንና ፕሬዚዳንቱ በሕዝብ ይመረጥ ወይስ በፓርላማ በሚለው ጉዳይ ተመካካሪዎች ስምምነት ላይ አለመድረሳቸው ተገልጿል። ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ቀርቶ በፕሬዚዳንት እንድትመራ፣ የመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ፣ እንዲሁም የፖለቲካ ሥርዓት፣ የፖለቲካ ውክልናና የምርጫ ሥርዓት አጀንዳ ላይ የ500 ቡድን ተመካካሪዎች ሙሉ በሙሉ በምክረ-ሐሳብ ደረጃ መግባባት ላይ ደርሰዋል ተብሏል። በዚሁ አጀንዳ ላይ ተወያይ የነበሩ ተመካካሪዎች ለሪፖርተር በሰጡት አስተያየት፣ በቀረቡት አብዛኞቹ ምክረሐሳቦች መግባባት ላይ መደረሱን ሆኖም ያላግባቡና ወደ ቀጣይ የተሻገሩ ጉዳዮች መኖራቸውንም ገልጸዋል። በዚህም የ500 ቡድን ተመካካሪዎች የአገሪቱ አስተዳደር ሥርዓት ፓርላሜንታሪ ሆኖ እንዲቀጥል፣ የአገሪቱ መሪ ፕሬዚዳንት እንዲሆን፣ አዲሱ ተመራጭ ፕሬዚዳንትም የጠቅላይ ሚኒስትሩና የፕሬዚዳንቱ ሥልጣንና ተግባርን…
Read More